የዕለቱ አጫጭር የዝውውር ወሬዎች

imageimage

የዕለተ ሰንበት የአውሮፓ አበይት ጋዜጦች በጀርባ ገፆቻቸው ላይ አይትመው ያወጧቸው የዝውውርና ሌሎች አጫጭር ጭምጭምታዎች…    

በ Mickyias B. Wordofa

እሁድ ታህሳስ 2 ቀን 2009 ዓ.ም

• ቼልሲዎች ከማንችስተር ሲቲ ጋር በኢትሀድ በነበራቸው ጨዋታ በፈጠሩት ያለፈው ሳምንት የሜዳ ላይ ጠብ ምክንያት ነጥብ ሊቀነስባቸው ይችላል፡፡ (ሰንዴይ ሚረር)

ምንጭ፦ ዘ ሰን


• የሲቲ የእግር ኳስ ዳይሬክተር ቲኪ ቤጊሪስትያን ጋቦናዊውን የዶርትሙንድ የፊት መስመር ተጫዋች ፔር ኤምሪክ ኦቦሚያንግን ለማስፈረም እየተከታተሉት ይገኛል፡፡ (ሰን ኦን ሰንዴይ) 


• አርሰናሎች በጥር የዝውውር መስኮት ለጀርመናዊው የዎልፍስበርግ የ 23 አመት አማካኝ ጁሊያን ድራክስለር 30 ሚሊየን ፓውንድ ሊያቀርቡ ነው፡፡


(ሰንዴይ ኤክስፕረስ) የቱርኩ ክለብ ቤሽኪታሽ ለ30 ዓመቱ የማንችስተር ሲቲ አምበል ቪንሰንት ኮምፓኒ ዝውውር 25 ሚ.ፓ ለማቅረብ ተዘጋጅቷል።

ምንጭ፦ ፋናቲክ


• የዌስትሀሙ አሠልጣኝ ስላቪያን ቢሊች የ27 አመቱን የሊቨርፑል አጥቂ ማስፈረም ይፈልጋሉ፡፡(ሰንዴይ ታይምስ)


• ዌስትሀም ከመውረድ ከተረፈ በቶሪኖ ክለብ በውሰት የተሰጠውን የሲቲና የእንግሊዝ በረኛ ጆይ ኸርትን ማስፈረም ይፈልጋል፡፡ (ሰንዴይ ቴሌግራፍ)


• አርሰናል ጨዋታ አቀጣጣዩ ሜሶት ኦዚል በዩናይትድ እንዳይወሰድበት ተፅእኖ ለማሳደር የማንችስተሩ ጄሲ ሊንጋርድ ላይ ፍላጉቱን አሳድሯል፡፡ (ሰን ኦን ሰንዴይ)


• የኤቨርተንና አየርላንድ አማካኝ ጄምስ ማካርቲ በ15 ሚሊዮን ፓውንድ የዝውውር ሂሳብ የዌስትብሮም ኢላማ ሆኗል፡፡ (ሜል ኦን ሰንዴይ)


• ሩሲያዊው የሲኤስኬ ሞስኮ ጨዋታ አቀጣጣይ አለን ዲዛጎቭ ከኤቨርተን ለመውጣት ጫፍ ላይ የሚገኘው የማካርቲ ምትክ እንዲሆን በጉዲሰን ፓርክ ታስቧል፡፡ (ሊቨርፑል ኤኮ)


• የ36 ዓመቱ የቼልሲው አምበል ጆን ቴሪ በአመት የ12 ሚሊዮን ፓውንድ ክፍያ የሚያስገኝለት ኮንትራት ሻንጋይ ሺንዋ ከተሰኘ የቻይና ክለብ ቀርቦለታል፡፡ (ሰን ኦን ሰንዴይ)


• አትሌቲኮ ማድሪዶች ዲያጎ ሲሞኔ በአመቱ መጨረሻ ጥሏቸው የሚሄድ ከሆነ የቶትነሀሙን አለቃ ማውሪሲዮ ፖቸቲኖን ለማስኮብለል እቅድ ይዘዋል፡፡ (ሰንዴይ ሚረር) 


• የ22 አመቱ የጋላታሳራይና የፖርቹጋሉ አማካኝ ብሩማ በቅድመ ውድድር ጊዜ ከሞሪንሆ ጋር ዝውውርን የተመለከተ ንግግር ማድረጉን ይፋ አድርጓል፡፡ (ፋናቲክ)


• አንድ ይፋ የተደረገ መረጃ እንዳሳየው 180 የሚሆኑ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ተጫዋቾች ከምስል መብት ግብር ጋር በተያያዘ የግብር አሰራሩን ማጭበርበራቸውንና መክፈል የነበረባቸውን ግብር አለመክፈላቸው ታውቋል፡፡(ሰንዴይ ታይምስ)


• የሲቲ የእግር ኳስ ዳይሬክተር ቲኪ ቤጊሪስትያን ጋቦናዊውን የዶርትሙንድ የፊት መስመር ተጫዋች ፔር ኤምሪክ ኦቦሚያንግን ለማስፈረም እየተከታተሉት ይገኛል፡፡ (ሰን ኦን ሰንዴይ)