Skip to content
Advertisements

ሉካዝ ፔሬዝ ማን ነው?

ወንድወሰን ጥበቡ | አርብ ነሀሴ 20 ቀን 2008 ዓ.ም

አርሰናል ሉካዝ ፔሬዝን ለማስፈረም ከጫፍ እንደደረሰ ከሃሙስ ዕለት አንስቶ ዘገባዎች እያመለከቱ ይገኛሉ። ኢትዮአዲስስፖርትም የዲፖርቲቮ ላካሮኛው አጥቂ ማነው የሚለውን በአጭሩ ዳሳለች።

አርሰን ቬንገር በዚህ ክረምት እየተከተሉት ባለው የዝውውር ፖሊሲ ከደጋፊውና ከሚዲያው ዘንድ በርከታ ትችት እንዲሰነዘርባቸው አድርጓል። ነገር ግን አሰልጠኙ 17 ሚ.ፓ ዋጋ ያለውን የዲፖርቲቮ ላካሮኛ የፊት ተጫዋች የሆነውን ሉከስ ፔሬዝን ወደለንደን ለማምጣት የሚችሉ ይመስላል።

ኤቨርተንም የውል ማፍረሻውን በመክፈል ተጫዋቹን ለማስፈረም ተቃርቦ የነበረ ቢሆንም ተጫዋቹ የሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎን ለማግኘት ኤመራትስን እንዲመርጥ ምክኒያት ሳይሆነው አልቀረም።

ይህ ተጫዋች ማን ነው? አጨዋወቱስ ምን ይመስለል? ለአርሰናል የሚመጥን ተጫዋችስ ነውን?

ግለዊ መረጃዎች

ዕድሜ: 27

የመጫወቻ ቦታ: ፊት

ክለብ: ዲፖርቲቮ ላካሮኛ

ዜግነት: ስፔናዊ

ታሪካዊ ዳራዎቹ

ሉካስ የተወለደው ምንም እንኳ ወደዚህ ከተማ መልሶ ለመምጣት በርካታ ውጣ ውረዶችን ቢያሳልፍም አሁን እየተጫዋተ የሚገኝበት ክለብ ዲፖርቲቮ ላካሮኛ ክለብ የሚገኝበት ኤ ኮሩና በተሰኘው ከተማ ነበር።

በ2007 አትሌቲኮ ማድሪድ ሲ ቡድን ውስጥ የሙከራ ጊዜን ከማሳለፉ በፊት በስፔን ዝቅተኛ ሊጎች ውስጥ ተጫውቶ አሰልፏል። በአትሌቲኮ ማድሪድ ተርሴራ ዲቪዚዮን ለሁለት የውድድር ዘመኖች በመጫወት ካሳለፈ በኋላ ሌላው የስፔን ክለብ ራዮ ቫልኬኖ ቢ ቡድንን ተቀላቅሏል።

አጥቂው በሴጉንዳ ዲቪዚዮን ባራዮ የመጀመሪያ ቡድን ውስጥ በጥቂት ጊዜያት ተሰልፎ በአምስት ጨዋታዎች አንድ ግብ ካስቆጠረ በኋላ ክለቡ በ2010/11 የውድድር ዘመን ላሊጋውን እንዲቀላቀል ማድረግ ችሏል።

ከዚያ በኋላም ሉካስ በ2011 ከኮንትራት ነፃ ሆኖ ከስፔን ውጪ በመውጣት ለዩክሬኑ ክለብ ካርፓቲ ሌቪቭ ፈርሞ የተጫወተ ሲሆን፣ ለአጭር ጊዜ ያህልም በዳይናሞ ኬቭ በውሠት አሳልፏል። ይሁን እንጂ በክለቡ አንድም ጨዋታ ላይ ባለመሰለፉ ወቅቱን “የህይወቴ መጥፎው የአራት ወር ጊዜ” ሲል ይገልፀዋል።
በ2013 ክረምት ስፔናዊው ተጫዋች 700,000 ዩሮ በሚጠጋ ዋጋ ለግሪኩ ክለብ ፓኦክ ለሶስት ዓመታት ቢፈርምም በቋሚነት ለክለቡ መሰለፍ የቻለው ግን ለአንድ የውድድር ዘመን ብቻ ነበር። በኋላም በ2014/15 የውድድር ዘመን ወደዲፖርቲቮ በውሰት አቅንቷል።

ለዲፖርቲቮ መሰለፍ በቻለባቸው 36 ጨወታዎች ላይም 17 ግቦችን አስቆጥሮ ክለቡ የውድድር ዘመኑን በ15 ደረጃ እንዲጨርስና በላ ሊጋው እንዲቆይ ማድረግ ችሏል። ሉካስ በውድድር ዘመኑ ከመረብ ያሳረፋቸው ግቦች ኬቨን ጋሜሮና ፈርናዶ ቶሬስ በድምሩ ካስቆጠሩት የላቀ ነበር።

የላ ሊጋው የውድድር ዘመን ከተጀመረ የተደረገው አንድ ጨዋታ ብቻ ቢሆንም ሉካስ ዲፖርቲቮ ኤባርን ባለፈው ሳምንት (አርብ) 2ለ1 ሲረታ የማሸነፊያዋን ግብ በፍፁም ቅጣት ምት ከማስቆጠሩም በለይ ክለቡ አቻ መሆን ያስቻለው ግብ እንዲቆጠር አመቻችቶ አቀብሏል።

የአጨዋወት ዘዴው

አርሰን ቬንገር በሉካስ የተማረኩት ባለው ሁለገብ አጨዋወቱ ነው። ስፔናዊው ተጫዋች በግሪኩ ክለብ ፓኦክ በግራ ክንፍ ይጫወት የነበረ ቢሆንም ነፃ ሚና ያለው ተደራቢ አጥቂ ሆኖ የሚጫወት ተጫዋችም ነው።
ይህን ቦታ በመጠቀምም ተጫዋቹ ዲፖርቲቮን ከመውረድ እንዲታደገው ያደረጉትን ግቦች እንዲያስቆጥር ትልቅ እድል ፈጥሮለታል።

ግቦችን ማስቆጠር አብይ ትኩረቱ ቢሆንም ኳሶችን በሚገባ የማቀበል አይንም ያለው ተጫዋች ነው። በዚህም ባለፈው የውድድር ዘመን ስምንት ግብ መሆን የቻሉ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል። ክንፍ ላይ እንዲጫወት ከተጠየቀም ከመስመር ቆርጦ ወደግብ ክልል የመግባት ብቃትም ያለው ተጫዋች ነው።

በአርሰናል እንዴት ሊዋሃድ ይችላል?

የአርሰናል ደጋፊዎች ተደጋጋሚ ጥያቄ አዲስ አጥቂ የማግኘት ነው። ምንም እንኳ አርሰናል በክረምቱ ዝውውር ስሙ ተያይዞ ከነበሩ ትልልቅ አጥቂዎች አንፃር ትልቅ ስም ባይኖረውም ይህንን የደጋፊውን ጥያቄ ሉከስ ሊያሟላ ይችላል።
አርሰን ቬንገር አሌክሲ ሳንቼዝን ማሳረፍ የሚያስፈልጋቸው አሊያም ጉዳት የሚገጥመው ከሆነ ሌላ የመጫወቻ አማራጭ ቢሰጡትም
ስፔናዊው ተጫዋች ግን በአርሰናል በክንፍ ከመጫወት ይልቅ በዲፖርቲቮ በተጫወተበት መንገድ የመጫወት ዕድሉ ሰፊ ነው።

አርሰናል ምን ያስፈልገዋል?

ሉካስ ክለቡ የሚፈልገው ዓይነት እንደኦሊቪየ ዥሩ በተከላካዮች ዒላማ ውስጥ ገብቶ የመጨረሻ አጥቂ መሆን የሚችል ተጫዋች አይደለም። በአየር ላይ ኳሶችም የተካነ አይደለም። ነገር ግን ኳስን በሚገባ ተቆጠጥሮ በመያዝ የፕሪሚየር ሊጉን ተጫዋቾች መፈተን የሚችል ተጫዋች ነው።

ከዩሮ 2016 በኋላ ዥሩ ወደአቋሙ እስኪመለስና ዳኒ ዌልቤክ የረጅም ጊዜ ጉዳት ላይ የሚገኝ በመሆኑ ለተወሰኑ ጊዜያት የመድፈኞቹን የአጥቂ ክፍል ከፊት ሆኖ መምራት ይችላል።

Advertisements
%d bloggers like this: