Skip to content
Advertisements

ሞሪንሆ  በማንቸስተር ዩናይትድ ላይ ያሳረፉት ተፅእኖ ከወዲሁ በግልፅ ታይቷል


ወንድወሰን ጥበቡ | ቅዳሜ ነሀሴ 21 ቀን 2008 ዓ.ም


ጆሴ ሞሪንሆ ልዊ ቫን ኻልን ተክተው የማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ሆነው ከተሾሙበት ጊዜ አንስቶ ከወዲሁ ለውጦች መታየት ጀምረዋል።

ስፖርታዊ መረጃዎችን በቁጥር በመተንተን የሚታወቀው ሁስኮርድ ድረገፅ ሞሪንሆ ከወዲሁ ማምጣት የቻሉትን ለውጥ በዝርዝር ተንትኖ አስቀምጦታል። 

ማንችስተር ዩናይትድ በዚህ የውድድር ዘመን በፕሪሚየር ሊጉ ማድረግ የቻለው ሁለት ጨዋታዎችን ብቻ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ሰር አሌክስ ፈረጉሰን በ2013 ማንችስተር ዩናይትድን ለቀው ስራ ካቆሙበት ጊዜ አንስቶ ዴቪድ ሞይስ እና ልዊ ቫን ኻል ለሶስት ዓመታት ያህል ማድርግ የተሳናቸውን ነገር ሞሪንሆ ከወዲሁ ማሳከት ችለዋል።

“ባለፉት ሁለት ወይም ሶስት ዓመታት በፊት ከነበረው ልዩነቶች መኖራቸውን ማንም ሰው ሊመለከተው የሚችል ይመስለኛል።” ሲሉ ሞሪንሆ ዩናይትድ ባለፈው ሳምንት ሳውዝሃምፕተንን 2ለ0 በሆነ ውጤት ከረታ በኋላ ከጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል።

ሞሪንሆ ከሚዲያው ጋር ያላቸው ተቃርኖ ከዚህ ቀደም ከነበረው የአሰልጣኝነታቸው ዘመን ጋር ተመሳሳይ ነው። ይህም በክረምቱ የዩናይትድ የአምሯዊ ዝግጁነት ለውጥ እንዲያመጣ የራሱን እገዛ ማድረግ ችሏል።

ዴቪድ ሞይስ ግን በስራቸው ላይ ያሏቸውን የበላይነት ማሳየት ተስኗቸው ነበር። ቫን ኸልም ቢሆን አራተኝነት በማሰብ እና ባገኙት ደረጀም መደሰት ላይ አተኩረዋል። በአንፃሩ ሞሪንሆ ግን ብዙ ነገር እንዲጠበቅባቸው ለማሳየት ሙከራ አላደረጉም። ይልቁንስ የተሳሳተ ግምት የሚሰጥባቸውን በስራቸው ማሳፈረ ጀመሩ እንጂ።

ዩናይትድ ከሜዳው ውጪ ቦርንማውዝን በሜዳው ደግሞ ሳውዛምፕተንን ብቻ አሸንፎ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ባለፈው የውድድር ዘመን ከእነዚህ ክለቦች ጋር ባደረገው ጨዋታ ሽንፈት ገጥሞታል። ዩናይትድ በቀድሞው ዘመን ሁለቱን የሰሜን ጠረፍ ክለቦች በቀላሉ ድል የማድረግ ልምድ የነበረው በመሆኑም ሁለቱን ክለቦች ዳግም ወዳማሸነፍ መመለሱ በኦልትራፎርድ ብሩህ ተስፋ ያለው አየር እንዲነፍስ ማድረግ ችሏል።

ሞሪንሆ የዩናይትድ አጥቂዎችን እግረ ሙቅ መፍታት ብቻ ሳይሆን በተከላካዩና በአጥቂው መካከል ያለው የኳስ ቅብብል የተሻለ እንዲሆን ማድረግ ችለዋል። ባለፈው የውድድር ዘመን ኳስና መረብን ለማገናኘት ማንችስተር ዩናይትድ ካደረገው (436) የኳስ ቅብብሎሽ በበለጠ አስቶንቪላ (638) እና ስዋንሲ (443) ብቻ ኳስን ተቀባብለዋል። ይሁን እንጂ በዚህ የውድድር ዘመን የትኛውም ቡድን የሞሪንሆው ቡድን ካደረገው ያነሰ ቅብብል (194) ማድረግ አልቻለም።

ዩናይትድ ባለፈው የውድድር ዘመን በየጨዋታው በአማካኝ ካደረገው (3.8) ዒለማውን የጠበቀ ሙከራ ከወዲሁ በእጥፍ የላቀ (6) ሙከራዎችን አድርጓል። ባለፈው የውድድር ዘመን በየጨዋታው በአማካኝ ከነበረው የግብ ዕድሎችን የመፍጠር (8.2) ሂደት ጋር የዘንድሮው (8.5) ሲነፃፀርም የዘንድሮው ብልጫ አለው። የተፈጠሩ ዕድሎችን ወደግብ በመቀየርም (በ21%) ብልጫ አለው።
ባለፈው የውድድር ዘመን በማጥቃቱ ሚና በእጅጉ ጥሩ ያልነበረ ቢሆንም ባለፈው የውድድር ዘመን ጅማሮ የትኛውም ክለብ ከማንችስተር ያነሰ ግብ (35) አላስተናገደም። ቫን ኻል አጥብቀው እንደመመሪያ በሚወስዱት ኳስን ተቆጣጥሮ የመጫወት የጨዋታ ዘዴም አማካኝ የኳስ ቁጥጥራቸው 55.9% ነበር። በሊጉም ከፍተኛ ከሆኑት በሁለተኛ ደረጃ የሚገኝ ክለብ ነበር። ክለቦችን አፍነው ነጥብው ይዘው እንዲወጡ ያስቻላቸውም ይኸው ነበር። ነገር ግን የቆሙ ኳሶችን የመቆጣጠር ብቃታቸው ግን አናሳ ነበር።

ባለፈው የውድድር ዘመን ከአደገኛ ሁኔታ ላይ ግብ በማስተናገድ ከዩናይትድ (36.4) በተሻለ መቀመጥ የቻለው ስዋንሲ (40%) ብቻ ነው። ለዚህም ነው ሞሪንሆ 30 ሚ.ፓ ወጪ በማድረግ ኤሪክ ቤሊን ከቪላሪያል የመጀመሪያ ፈርሚ ማድረጋቸው። ከሞሪንሆ የክረምት ዝውውር አራት ፈርሚ ተጫወቾች መካከል አንዱ የሆነው ቤሊ ባለፈው የውድድር ዘመን ከአምስቱ የአውሮፓ ከፍተኛ ሊጎች ውስጥ ካሉና በሁስኮርድ ድረገፅ ከፍተኛ ደረጃ ከተሰጣቸው ተጫዋቾች መካከል አንዱ አልነበረም። ይሁን እንጂ ቤሊ በውድድር ዘመኑ ላይ የነበረው ብቃት ግን ትልቅ ከመሆኑም በላይ በመከላከል ላይ ያለው አካላዊ ብቃትም ከወዲሁ ከዩናይትዱ ታሪካዊ ተጫዋች ኒማኒያ ቪዲች ጋር እንዲነፃፀር አስችሎታል።

ከቤሊ በሁለቱም አቅጣጫ የሚገኙት የመስመር ተከላካዮች፣ አንቶኒዮ ቫሌንሺያ እና ሉኬ ሻውም ቢሆኑ በእኩል ደረጃ ብቃታቸውን ማሳየት እየቻሉ ይገኛሉ። ብዙ ፈተና ገና የሚጠብቃቸው ቢሆንም ሁለቱም ተጫዋቾች በሁዋን ማታ እና አንቶኒ ማርሻል አማካኝነት በሚያገኙት ክፍተት ወደፊት ጠልቀው የመጫወት ዕድል አግኝተዋል። በእርግጥም ከቫሌንሺያ እና ሻው (3) በበለጠ የተሳካ ኳስ ወደፊት መግፋት የቻለው ፓውል ፓግባ (9) ብቻ ነው። የማንችስተር ዩናይትድ የክንፍ ክፍልም በቁጥራዊ መረጃ ስሌት መሰረት ከወዲሁ ከቡድኑ ጠንካራ የሚባል ነው።

ባለፈው የውድድር ዘመን በልዊ ቫን ኻል የዩናይትድ የመስመር ተከላካይ የተጫዋቾች አማካኝ የኳስ ቁጥጥር ከሜዳው አጋማሽ የማለፍ ዕድሉ እምብዛም ነበር። ነገር ግን ሞሪንሆ ይህን የተጫዋቾች ክፍል ከወዲሁ እስከተቃራኒ የግብ ክልል ድረስ ጠልቆ የመጫወት ትልቅ ኃላፊነት ሰጥተውታል። ለዚህም ማሳያ ከሳውዝሃምፕተን ጋር በተደረገው ጨዋታ የሾው አማካኝ የኳስ ቁጥጥር እንደኹዋን ማታና ዋይኒ ሩኒ ካሉ ተጫዋቾችም የላቀ ነበር። እንዲሁም ቫሌንሺያ በቦርንማውዙ ጨዋታ ላይ የነበረው የኳስ ቁጥጥር ከዩናይትድ አራት የፊት ተጫዋቾች ጋር እኩል በሚባል ደረጃ ላይ ነበር።

ባለፈው የውድድር ዘመን ዩናይትድ በከፍትኛ ሁኔታ ድል ባደረገባቸው ጨወታዎች እንኳ ሁለቱ የመስመር ተከላካዮች ወደሁለቱ የመስመር አማካኞች ጨርሶ የመጠጋት ስራ መስራት አልቻሉም ነበር። አልፎ አልፎ ጠልቆ የመጫወት ሚና ሲኖራቸው እንኳ ከአማከኞቹ ጋር በዘዴ የቦታ ለውጥ በማድረግ ብቻ ነበር።

ሌላው የማንችስተር ዩናይትድ አስገራሚ አብዮት የተፈጠረው ሞሪንሆ ፖግባን በተጠቀሙበትና ለሩኒ በሰጡ ሚና የጎላበት የመሃል አማካኝ ስፍራ ላይ ነው። ፖግባ ወደፊት ገፍቶ የመሄድ ፈቃድ የተሰጠው በመሆኑ በሳውዝሃምፕተኑ ጨዋታ ላይ ድንቅ ብቃቱን አውጥቶ የመጫወት ዕድል እንዲያገኝ ሆኗል፤ በሁስኮር ደረገፅ የነጥብ አሰጣጥ መስፈርት መሰረትም 8.85 ነጥብ በማግኘት የጨዋታው ኮከብ መሆን ችሏል። በእርግጥ ሞሪንሆ ይህን አሁን እየተጠቀሙ ያሉበትን የ4-2-3-1 አሰላለፍ ወደፊትም የሚጠቀሙበት ከሆነ ፖግባ በተሻሉ ቡድኖች ላይ ይህን ዓይነት ነፃነት ሊየገኝ የሚችልበት ዕድሉ አናሳ ነው።

ሞሪንሆ ፖግባን ማዳ አካሎ እንዲጫወት ዕድል የሚፈጥርለትን ሶስት ዓማካኞችን በመሀል ስፍራ ላይ የመጠቅም ባህላቸውን መልሰው የሚጀምሩ ከሆም ሩኒን በቦታው ላይ ዋጋ ሳያስከፍለው አይቀርም። ከወዲሁም የዩናይትዱ አምበል ለወደፊቱ የመሃል ስፍራ እንደማይኖረው በግልፅ ታይቷል።

ሞሪንሆ ከዩናይትድ የመጀመሪያዎቹ ሁለት ጨዋታዎች ሁሉንም አዎንታዊ ነገሮች ቢወስዱም ገና ቀሪ በቡድኑ ላይ የሚያክሉበት ነገር አላቸው። ይህን አስመልክተውም ሲናገሩ “አሁን ባለንበት ሂደት በጫወታዎቻችን ላይ ለውጦችን ማሳየታችን ጠቃሚው ነገር ነው። ምንም እንኳ እስካሁን ድረስ ድንቅ ነን ብሎ ማንም መናገር ባይችልም አሁን ግን ለውጦቹን ማሳየት እየቻልን እንገኛለን። ነገር ግን ድንቅ እንደምንሆን ተስፋ አለኝ።” ሲሉ ተናግረዋል።

ማንችስተር ዩናይትድ በሞሪንሆ ምን ያህል እንደተጓዘ ለማሳየት ትልቅ ፈተና ሊሆን የሚችለው ከብሄራዊ ቡድኖች የጨዋታ እረፍት በኋላ የመጀመሪያቸው የሚሆነውን የማንችስተር ደርቢ ሲያደርጉ ነው። ይሁን እንጂ ከወዲሁ የታየው ምልክት ግን አዎንታዊ ነው። ሞሪንሆ እንዲሆን የሚያስቡት ከፍተኛ ደረጃ ከደረሰ ደግሞ በግንቦት ወር በእጃቸው ለሚያስገቡት የፕሪሚየር ሊጉ ዋንጫ ተፎካካሪነት መብቃታቸው ጥርጥር የለውም።

Advertisements
%d bloggers like this: