Skip to content
Advertisements

በዝውውር መስኮቱ ሁለት የመጨረሻ ቀናት የትኛው ተጫዋች ወዴት ያቀና ይሆን?

ወንድወሰን ጥበቡ | ማክሰኞ ነሃሴ 24 ቀን 2008 ዓ.ም


የአውሮፓ ዝውውር መስኮት ረቡዕ ከዕኩለ ለሊት በኋላ 8፡00 ሰዓት ላይ ከመዘጋቱ በፊት የትኛው ተጫዋች ወዴት ይዛወር ይሆን?

ትልልቅ ስም ያለቸው ተጫዋቾች በመጨረሻው የዝውውር ቀናት ሊዛወሩባቸው የሚችሉ ክለቦች በጭምጭምታ ደረጃ በመዘገብ ላይ ይገኛሉ።

በስካይ ስፖርት የዝውውር ዘገባ መረጃ መሰረትም በመጨረሻዎቹ ሰዓታት ሊሳኩ ይችላሉ የተባሉ ዝውውሮችን ልናስቀኛችሁ ወደድን።

ጀክ ዊልሼር


በዚህ የውድድር ዘመን በሁለት ጨዋታዎች ላይ ብቻ እንዲሰለፍ ገደብ የተጣለበት ዊልሼር ቋሚ ተሰላፊነት እንዲያገኝ በማሰብ አርሰናል በውሰት ሊለቀው በዝግጅት ላይ ይገኛል።
የተጫዋቹን ግልጋሎት ለማግኘት ጁቬንትስ ከዌስትሃምና ከቦርንማውዝ ቀድሞ ተቀምጧል።

ሙሳ ሲሶኮ


ሲሶኮ ኒውካሰል ከፕሪሚየር ሊጉ ከወረደም በኋላ በዩሮ 2016 ያሳየውን ድንቅ ብቃት ተከትሎ የበርካታ ክለቦችን ቀልብ በመሣቡ ሴንት ጀምስ ፓርክን የመልቀቅ ዕድሉ በእጅጉ ሰፊ የሆነ መስሏል። ነገር ግን ትክክለኛ ፈላጊው ክለብ ግን ገና በመጠበቅ ላይ ይገኛል።

አርሰናል፣ ፒኤስጂና ሪያል ማድሪድ ፈላጊዎቹ እንደሆኑ ቢዘገብም፣ ኤቨርተን ግን የተጫዋቹ ማረፊያ የመሆን ዕድሉ ከፍ ያለ እንደሆን ታምኗል።

ማሪዮ ባላቶሊ


ተፈላጊነትን ግምት ውስጥ ካሥገባን የባላቶሊ ሁኔታ መፍትሄ ለመስጠት በእጅጉ አስቸጋሪ ሆኖ ይገኛል። ሊቨርፑልም ከፍተኛ ተከፋይ ከሆኑ ተጫዋቾቹ መካከል አንዱ የሆነውን ከክለቡ የመቀነስ ውጥን አለው።

ባለፈው የውድድር ዘመን ለኤሲ ሚላን ተሰልፎ በተጫወተባቸው 20 የሴሪ ኣው ጨዋታ አንድ ግብ ብቻ ከመረብ ላይ ማሳረፍ የቻለው ጣሊያናዊው ተጫዋች ገና በ26 ዓመቱ የተፈለገውን ያህል ክፍያ የሚያቀርቡ ክለቦችን ቀልብ መሳብ ተግዳሮት ሆኖበት ይገኛል። የፈረንሳዩ ክለብ ኒስ እንዲሁም የጣሊያኑ ክለብ ፓሌርሞ በአሁኑ ጊዜ የተጫዋቹን ግልጋሎት የሚሹ ክለቦች ናቸው።

ሳዲዮ በራሂኖ


ለበርካታ ዓመታት አሁን የሚገኝበትን ክለብ ለመልቀቅ ቁጥራቸው ከፍተኛ ከሆኑ ክለቦች ጋር ስሙ የተያያዘ ሌላ በዝውውር ጎዳና ላይ የሚገኝ ሌላኛው ተጫዋች ነው። በሳምንቱ መጨረሻም በቶኒ ፑሊስ በተቀያሪ ወንበር ላይ እንዲቀመጥ መደረጉ ተጫዋቹ ዌስትብሮምን እንደሚለቅ ማሳያ ሆኖ ቀርቧል።

ናሰር ቻድሊ ከቶተንሃም በክለቡ መድረስም ተጫዋቹ ክለቡን የመልቀቅ ማረጋገጫ ሆኖል። የ23 ዓመቱን ተጫዋች ወደክለቡ ለማምጣትም ስቶክ የተሻለ ዕድል ያለው ክለብ ነው።

ኻመስ ሮድሪጌዝ


ሮድሪጊዝ በ71 ሚ.ፓ ለሪያል ማድሪድ ሲፈርም የ10 ቁጥር መለያን እንደሚያገኝ ታምኖ ነበር። ክለቡም የዚነዲን ዚዳን ዓይነት አዕምሯዊ ዝግጁነት ያለው ተጫዋች እንዳመጣም ተስፋ ጥሎበት ነበር። ይሁን እንጂ የ25 ዓመቱ ተጫዋች የልጅነት ጀግናውን ብቃት ለመድገም ተቸግሯል። ጉዳት ታክሎበትም በዚህ የውድድር ዘመን በሶስት ጨዋታዎች ላይ ተቀያሪ ወንበር ላይ ተቀምጧል።

ቼልሲ የተጫዋቹን አቅምና ጥቅም ለማግኘት የተሻለ ዕድል ያለው ክለብ ነው። የዛኑ ያህል በማድሪድ የመቆየት ዕድሉም ከፍ ያለ ነው።

ዊልፍሬድ ቦኔ


አብዛኛው የክረምቱ የኤቨርተን የዝውውር ጭምጭምታ ትኩረቱን ያደረገው ብቃት ያለው አጥቂያቸው ተጫዋች ሮሜሉ ሉካኩ ክለቡን ይለቃል በሚል ላይ ነበር። ነገር ግን ቶፊሶቹ ሉካኩን በክለቡ ማቆየት ብቻ ሳይሆን በፊት በኩል ፉክክር እንዲገጥመው ማድረግም ፈልገዋል።

በመሆኑም በአጥቂ ስፍራው ላይ ዊልፍሬድ ቦኔን የማካል ከፍተኛ ፍላጎት አላቸው።

Advertisements
%d bloggers like this: