Skip to content
Advertisements

በተጫዋችነት ህይወታቸው ለዝውውር ከፍተኛ ወጪ የተደረገባቸው 10 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተጫዋቾች

ወንድወሰን ጥበቡ | አርብ ነሃሴ 27 ቀን 2008 ዓ.ምበክረምቱ የዝውውር መስኮት ወቅት አስራሶስት የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች የክለባቸውን የዝውውር ክብረወሰን ሰብረዋል። በአጠቃላይ በሊጉ የዝውውር እንቅሳቃሴ ከ1 ቢሊየን ፓውንድ በላይ መዋዕለ ንዋይ ፈሰስ ተደርጓል። በተጫዋቾች የዝውውር ዋጋ ላይ ሰባት ዜሮዎች ያሉት ቁጥርን ማስፈርም የተለመደ ነገር ሆኗል።

የእንግሊዙ ጋዜጣ ስፖርትስ ሜል እግር ኳስ ተጫዋቾች በተጫዋችነት ህይወታቸው ላይ የተከፈላቸው ድምር ክፍያን በማስላት ከእንድ እስከአስር ባለው ደረጃ የተቀመጡ ተጫዋቾችን በሚከተለው መልኩ ዘርዝሯል።

በዝርዝሩ ሁለት ስፔናውያን፣ ሁለት ብራዚላውያን፣ አንድ ስዊድናዊ፣ አንድ ጀርመናዊ እና ቺሊያዊ ሲካተቱ፣ ከእነዚህ መካከል ሶስቱ የእያንዳንዳቸው ድምር ዋጋ ከ100 ሚሊዮን ፓውንድ የበለጠ ነው።

እስከ10 ባለው ደረጃ የተቀመጡ ተጫዋቾች ላይ ወጪ የተደርገ ድምር ዋጋም 802.5 ሚሊዮን ፓውንድ ነው።

10) መሱት ኦዚል (አርሰናል) – 58.7 ሚ.ፓ


በ2013 ክረምት ከሪያል ማድሪድ ወደኤመራትስ በ42.5 ሚ.ፓ  ከተዛወረ ወዲህ ብልጭ ጥፍት የሚል ብቃት ማሳየት የቻለ ተጫዋች ነው። 

9) ሴስክ ፋብሪጋዝ (ቼልሲ) – 60 ሚ.ፓ


ስፔናዊው ተጫዋች ከአርሰናል ወደባርሴሎና እንዲሁም ከባርሳ ወደቼልሲ ባደረጋቸው  ሁለትም ዝውውሮች በተመሳሳዩ 30 ሚ.ፓ ተከፍሎበታል።

በእንዚህ ክለቦች ውስጥ ተጫዋቹ አምስት የሊግ ዋንጫዎችን አንስቷል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ሁለት ጊዜ የአውሮፓ ዋንጫንና አንድ የዓለም ዋንጫን ማንሳትም ችለዋል።

8) ኹዋን ማታ (ማንችስተር ዩናይትድ) – 60.6 ሚ.ፓ


ማታ በ2011 እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከደረሠበት ጊዜ አንስቶ ትልቅ ተፅዕኖ መፍጠር ችሏል። ከቫሊንሺያ ስታምፎርድ ብሪጅ የደረሰውም በ23.5 ሚ.ፓ ነው።

በማንችስተር ዩናይትድም ለሶስት ዓመታት ከግማሽ የውድድር ዘመን አሳልፏል።

ሞሪንሆ በተጫዋቹ ላይ ያላቸው ፍላጎት ቀዝቃዛ ቢሆንም፣ ዩናይትድ የተጫዋቹን ግልጋሎት ለማግኘት 37.1 ሚ.ፓ ወጪ አድርጓል።

7) አሌክሲ ሳንቼዝ (አርሰናል) – 62.5 ሚ.ፓ


ቺሊያዊ ተጫዋች ከሁለት ዓመት በፊት ከባርሴሎና ሰሜን ለንደን ከደረሰ ጊዜ አንስቶ በ96 ጨዋታዎች ላይ 43 ግቦችን ማሳረፍ ችሏል።

ከዚያ በፊት ከዩዴኔዚ ወደኑካምፕ ሲዛወር ካቶሎንያውያኑን 30 ሚ.ፓ አስወጥቷቸዋል። ነገር ግን የጣሊይኑ ክለብ ከሃገሩ የደቡብ አሜሪካ ክለብ ከሆነው ኮርቤሎርዋ በ2007 ሲያዛውረው 2.5 ሚ.ፓ ወጪ አድርጎበታል።

6) ክርስቲያን ቤንቴኬ (ክሪስታል ፓላስ) – 71.8 ሚ.ፓ


አስቶንቪል ቤንቴኬን ከቤልጂየሙ ክለብ ጌንክ ሲያመስመጣ 7 ሚ.ፓ ከፍሎበታል። በሚድላንድ የማይረሱ ግቦች የተቆጠረበት ሊቨርፑልም ተጫዋቹን ወደክለቡ ወስዶታል።

ይሁን እንጂ ቤልጂየማዊው ተጫዋች በአስቶንቪላ ያደረገውን በመርሲሳይድ መድገም አልቻለም። ነገር ግን አለን ፓርዲው በተጫዋቹ ብቃታ ላይ እምነት በማሳደራቸው 32 ሚ.ፓ ወጪ አድርገው ወደሴልኸረስት ፓርክ ስታዲየም ወስደውታል።

5) ዊልያን (ቼልሲ) – 73 ሚ.ፓ


ብራዚላዊው ተጫዋች ከዩክሬን ወደሩሲያ ከዚያም ዋደእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሲዛወር ሶስት ትልልቅ ስምምነቶችን አድርጓል።

በአንዚ ማካቻካላ እና ሻካታር ዶኖቴስክ ካሳለፈ በኋላ ቼልሲን 32 ሚ.ፖ ወጪ አስወጥቶታል።
በደጋፊው ዘንድም የተወደደ እንዲሆንም አድርጎታል።

4) ኬቨን ደብሩይን (ማንችስተር ሲቲ) – 79.7 ሚ.ፓ


ቼልሲ ደ ብሩይን በ6.7 ሚ.ፓ ወደክለቡ ሲያመጣው ዕድሜው 20 ነበር። ነገር ግን በምዕራብ ለንደኑ ክለብ የጨዋታ ዕድል ማግኘት አልቻለም። በመሆኑም በ2015 ወደ ዎልፍስበርግ በ18 ሚ.ፓ አቅንቷል።

በሚያስገርም ሁኔታ ግን ከአንድ ዓመት በኋላ በ55 ሚ.ፓ መልሶ ወደእንግሊዝ መጥቷል።

3) ፖል ፖግባ (ማንችስተር ዩናይትድ) – 100 ሚ.ፓ


ፖግባ በጁቬንቱስ በፍጥነት በተከታታይ አራት የሴሪ ኣ ዋንጫዎችን ካነሳ በኋላ እንዲሁም በፈረሳይ ብሄራዊ ቡድን ውስጥ ጉልህ ድርሻ ያለው ተጫዋች ከሆነ በኋላ ዩናይትድ የዓለም የዝውውር ክበረወሰን በሆነ ዋጋ ካዝናውን ሰብሮ የቀድሞ ተጫዋቹን ከአዲስ የፀጉር አቆራረጡ ጋር ወደፕሪሚየር ሊጉ አምጥቶታል።

2) ዴቪድ ልዊዝ (ቼልሲ) – 101 ሚሊዮን ፓውንድ


እውነተኛው ብራዚላዊ ግንብ የምንጊዜውን የዓለማችን ውዱ (በ50 ሚ.ፓ) ተከላካይ ነው።  ተከላካይ የሚለው ቃል የሚስተካከለው ከሆነ። 

ይህ ድንቅ እግር ኳስ ተጫዋች በመጨረሻው የዝውውር መስኮት ቀን በአስገራሚ ሁኔታ በ34 ሚ.ፓ በድጋሚ ወደቼልሲ ተመልሷል።

1) ዝላታን ኢብራሂሞቪች (ማንችስተር ዩናይትድ) – 133.2 ሚ.ፓ


ያለጥርጥር ቁጥር 1 ነው።

ረጅሙ ስዊድናዊ አጥቂ ከማልሞ ወደአያክስ 5 ሚ.ፓ፣ ከሆላንዱ ክለብ ወደጁቬንቱስ 12 ሚ.ፓ፣ ከአሮጌቷ ወደኢንተር 20 ሚ.ፓ፣ ከኢንተር ወደባርሳ 56.5 ሚ.ፓ፣ ከኑካምፕ ወደኤሲሚላንን 24 ሚ.ፓ እንዲሁም ከሮሶነሪዎቹ ወደፒኤስጂ 15.7 ሚ.ፖ ወጪ የተደረገበት የዓለማችን ውዱ ተጫዋች ነው።

ኢብራሂሞቪች በእግር ኳስ ህይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ያለምንም ወጪ በሳምንት 260,000 ፓውንድ ወደሚከፈለው ክለብ ያመራው በዚህ ክረምት ብቻ ነው።

ከዚህ በታች ያሉት ተጫዋቾች ከ50 ሚ.ፓ በላይ ወጪ የተደረገባቸው ቢሆንም፣ ከላይ ባለው ዝርዝር ውስጥ ግን መግባት አልቻሉም።

አልቫሮ ኔግሬዶ (ሚድልስቦሮ) – 58.5 ሚሊዮን ፖውንድ
ሂነሪክ ሚኪታሪያን (ማንችስተር ዩናይትድ) – 54 ሚ.ፓ
ኒኮላስ ኦታሜንዲ (ማንችስተር ሲቲ) – 51.5 ሚ.ፓ
ሳዲዮ ማኔ (ሊቨርፑል) – 51.1 ሚ.ፓ
ጆን ስቶንስ (ማንችስተር ሲቲ) – 50.2 ሚ.ፓ
አንዲ ካሮል (ዌስት ሃም) – 50 ሚ.ፖ

Advertisements
%d bloggers like this: