ዩጋንዳዊው ያስር ሙግርዋ ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ለመዘዋወር እየተነጋገረ ይገኛል

By Eyob Dadi


ዩጋንዳዊው የአጥቂ አማካይ ያስር ሙግርዋ ወደ ኢትዮጵያው ቅ/ጊዮርጊስ ለመዘዋወር ንግግር ላይ እንደሚገኝ ታውቋል።

ተጨዋቹ በነሀሴ 2015 መጨረሻ ላይ ለደ/አፍሪካው የአብሳ ፕሪምየርሺፕ ተሳታፊው የስዌቶው ኦርላንዶ ፓይሬትስ ለ 3 አመት መፈረም ችሎ ነበር።

በኮንትራቱም ላይ እስከ 2018 ድረስ ከ ደ/አፍሪካው ቡድን ጋር እንደሚቆይ ተጠቅሷል።

ነገርግን በአንድ አመት የደ/አፍሪካ ቆይታው በቂ የመሰለፍ እድልን ማግኘት ሳይችል ቀርቷል።

ክለቡ ከወር በፊት በቅድመ ልምምድ ወቅትም ከቡድኑ ሊለቁ የሚችሉት 6 የተጨዋቾች ዝርዝር ውስጥ ስሙ ተካቶ ነበር።

በዚህ ምክንያት የ 23 አመቱ  ተጨዋች በቅርቡም ከክለቡ ጋር በጋራ ስምምነት እንደተለያዩ ተሰምቷል።

የአጥቂ አማካዩ ለኢትዮአዲስ ስፓርት እንዳረጋገጠው ከሆነም  ወደ ኢትዮጵያው ሻምፕዮን ቅ/ጊዮርጊስ ለማቅናት ንግግር ላይ እንደሚገኝ አሳውቋል።ዝውውሩንም ለማጠናቀቅ መቃረቡ ታውቋል።

የዩጋንዳ ብ/ቡድን አሰልጣኝ ሙሉቲን ‘ሚቾ’በጥር 2014 ላይ ለተጨዋቹ የብሄራዊ ቡድኑ ጥሪ አድርጎለት ነበር።

Advertisements