Skip to content
Advertisements

የቅዳሜ ከሰዓት ልዩ የሀገር ውስጥ እና ውጭ እግር ኳሳዊ ዜናዎች [በኢትዮአዲስ ስፖርት]


image
ፈይሰል ሀይሌ

ቅዳሜ ጷግሜ 5 ፨ ለኢትዮአዲስ ስፖርት በፈይሰል ሀይሌ 
  ከእለቱ ዜናዎቻችን መካከል
ከውጭ ፡- በዛሬ የሀገር ውስጥ እና የውጭ የእግር ኳሳዊ ዜናዎቻችን በርከት ያሉ አርሰናል ፣ ማንዩናይትድ ፣ ቼልሲ፣ ሊቨርፑል ፣ ባርሴሎና እና ሪያል ማድሪድ ላይ ያተኮሩ ትኩስ እና ወቅታዊ እንዲሁም ያልተሰሙ የክለቦቹን ዜናዎች የያዝን ሲሆን የሀገር ወስጥ እግር ኳሳዊ ወሬዎች ፣ ቁጥራዊ መረጃዎች ፣  ይህንን ያውቁ ኖሯልም እንደተለመደው አሰናድተናል፡፡

image የሀገር ውስጥ ዜና
ታዳጊ ብሄራዊ ቡድኑ የፊታችን ማክሰኞ ወደ ባማኮ ያቀናል

⚽ የ2017 ከ17 አመት በታች የአፍሪካ ዋንጫን ደሴቲቷ ኀገር ማዳጋስካር ከመጋቢት 24 እስከ ሚያዝያ 8 ታስደተናግዳለች 8 ሀገራት በ2 ምድቦች ተከፍለው በሚያደርጉት በዚህ የአፍሪካ ዋንጫ ላይም የኢትዮጵያ ታዳጊ ብሄራዊ ቡድን ለውድድሩ ለማለፍ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ይገኛል፡፡ የግብጽ አቻውን በደርሶ መልስ 5-2 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ከቀሩት 16 ሀገራት 1 የሆነው ቀይ ቀበሮው ከአንድ ሳምንት በዋላ በመጨረሻው የውድድሩ ማጣሪያ የማሊ አቻውን ባማኮ ላይ ይገጥማል፡፡ ሰለዚህ ውድድር ዝግጅት ሲባልም በቀድሞ የመብራት ሀይል ዋና እና የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ምክትል አሰልጣኝ አጥናፉ አለሙ የሚመራው ታዳጊ ብሄራዊ ቡድኑ መቀመጫውን ሴንትራል ሆቴል በማድረግ በውቢቷ ሀዋሳ ላይ ከትሞ ለአንድ ሳምንት ልምምዱን ሲያከናውን የቆየ ሲሆን የፊታችን ማክሰኞም ወሳኙን የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ለማድረግ ወደ ማሊ ባማኮ እንደሚያቀና ተነግሯል፡፡

ጌታነህ ከበደ በደደቢት በ2 አመት ውስጥ እስከ 3 ሚሊየን ብር በደሞዝ ያገኛል

⚽ ያልታሰበው እና ያልተጠበቀው ዝውውር ባሳለፍነው ሀሙስ ረፋድ ተከናውኗል፡፡ ከኮንትራት ነጻ የነበረውን የአፍሪካ ዋንጫው የብሄራዊ ቡድኑ ከፍተኛ ግብ አግቢን ለማስፈረም የለጉ ሀያላን የሆኑት ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና ፍላጎት ማሳየታቸው እና ለድርድር መቀመጣቸው ከዚህ ቀደም በስፋት ቢነገርም የዋልያዎቹ ፊት አውራሪ ጌታነህ ከበደ ሰበሮም ምርጫውን ደደቢት አድርጓል፡፡ ጌታነህ ከበደ በደደቢት እግር ኳስ ክለብ ለ2 አመት የሚያቆውን ፊርማ ባሳለፍነው ሀሙስ የፈረመ ቢሆንም በእለቱ ስለ ዝውውር ሂሳቡ ከተጫዋቹም ሆነ ከክለቡ የተነገረ ምንም አይነት ማረጋገጫ አልነበረም ፡፡ ነገር ግን አፈትልከው በወጡ መረጃዎች መሰረት የቀድሞ የቤድቬትስ እና ፕሪቶሪያ ዩኒቨርስቲ አጥቂ በደደቢት በ2 አመት ቆይታው በወር 125 ሺ ብር ተከፋይ ይሆናል፡፡ ይህም ማለት በ2 አመት ውስጥ ደደቢት ለብሄራዊ ቡድኑ ፊት አውራሪ 3 ሚሊየን ብር ይከፍላል፡፡

image

ኢትዮ አዲስ ስፖርት መልካም አዲስ አመት ትመኛለች 

⚽ ከተመሰረተች 2 አመት ያስቆጠረችው እና ሀገራችን ውስጥ ካሉ የኦንላይን ሚዲያ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ስፖርታዊ ዜናዎችን በድረገጽ በመልቀቅ ቀዳሚዋና ተመራጯ ኢትዮአዲስ ስፖርት መልካም አዲስ አመት ትላለች ፡፡ መጪው አመት የስኬት የፍቅር የመዋደድን እና የሰላም እንዲሆንላቹም የድረገጹ አዘጋጆች በሙሉ ይመኛሉ፡፡ በ2009 ከዘንድሮ በተሻለ እና ባማረ አቀራረብ እንደምንመጣ ከወዲሁ ቃል እንገባለን፡፡ የእርሶ ተቀዳሚ ምርጫ የሆነችው ድህረ ገጻችንም በቀጣይ አመት ምን ትጨምር ምን ትቀንስ ምንስ ታሻሽል የሚለውን ከእናንተ የተከበራቹ ተከታታዮቻችን አስተያየት እንጠብቃለን፡፡ 
 

image

image ዜና ማንችስተር ዩናይትድ
ሆዜ ሞሪንሆ ከደርቢው ፍልሚያ በዋላ ፔፕ ጋርድዮላን ወይን የመጋበዝ እቅድ አላቸው

⚽ የአለማችን 190 ሀገራት ታላቁን የእንግሊዝ ደርቢ በቴሌቭዥን ከ75.000 በላይ ታዳሚያን ደግሞ በኦልድትራፎርድ  የማንዩናይትድ እና የሲቲን ትልቁን የደርቢ ጨዋታ ይመለከታሉ፡፡ ያለፉትን 3 የደርቢ ጨዋታዎች ሽንፈት ያልቀመሱት ቀያዮቹ ሰይጣኖች ለነገው ጨዋታም ካሪንግተን ከትመው ልምምዳቸውን በዝግ ሲያደርጉ ስንብተዋል፡፡ ሆዜ ሞሪንሆ እና ፔፕ ጋርድዮላ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ታሪክ ይገናኛሉ፡፡ ባላንጣ እንደሆኑ የተነገረላቸው ሁለቱ ውጤታማ አሰልጣኞች በሊጉ ጅማሮ ያደረጓቸውን 3 የሊጉ ጨዋታዎች ድል በማድረግ በ100% አሸናፊነታቸው ዘልቀዋል፡፡ እንደ ዘሰን ዘገባ ከሆነ ደግሞ ሆዜ ሞሪንሆ ከፔፕ ጋርዲዮላ ጋር ያላቸውን ቅራኔ ጋብ በማድረግ ከዛሬ ከሰአቱ የደርቢ ጨዋታ በዋላ በማንችስተር ከተማ ከጋርድዮላ ጋር ወይን የመጠጣት እቅድ እንዳላቸው ያስነበበ ሲሆን ፔፕ ጋርዲዮላም ከሆዜ ሞሪንሆ ጋር ወይን እየጠጡ ቢጨዋወቱ ችግር እንደሌለባቸው በትላንትናው ጋዜጣዊ መግለጫቸው ላይ ይፋ አድረገዋል፡፡

image

ዩናይትዶች በ2017 ታላቅ ዝውውር የማድረግ እቅድ አላቸው

⚽ በዝውውር ገበያው ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ስኬታማ ዝውውሮችን በማድረግ ከሚጠቀሱ ክለቦች መሀል ግንባር ቀደም የሆኑት ማንዩናይትዶች ከወዲሁ በቀጣይ አመት ለሚከፈተው የክረምቱ የተጫዋቾች ዝውውር መስኮት አንቶንዮ ግሪዝማንን ተቀዳሚ የዝውውር ኢላማቸው ማድረጋቸውን ተነባቢው ማንችስተር ኢቪኒንንግ ኒውስ አስነብቧል፡፡ ፈረንሳዊውን አንቶንዮ ግሪዝማንን  የዋይኒ ሮኒ ተተኪ ለማድረግ መቁረጣቸው የተነገረላቸው ቀያይ ሰይጣኖቹ ለተጫዋቹ የተቀመጠውን 100 ሚሊየን ዩሮ ውል ማፍረሻ ከፍሎ ለማስፈረም እንደማይቸገሩ በፖል ፖግባ ዝውውር ማሳያ እንደሆነ ዘገባው አክሎ ገልጽዋል፡፡   

የዩናይትዱ ተከላካይ በጥር ክለቡን ይለቃል 

⚽ በዘመነ ሊዊ ቫን ሀል ዩናይትድን ከቶሪኖ ተቀላቅሎ በዩናይትድ በተሰለፈባቸው የመጀመሪያ ሳምንታት ጨዋታዎች አስደናቂ የሚባል ብቃትን በማሳየት የ2015 የወርሀ ነሀሴ ኮከብ ተጫዋች ለመባል በቅቶ በበርካቶቸ ተስፋ ተጥሎበት የነበረው ጣሊያናዊው ተከላካይ ማቲዮ ዳርሚየን ከዩናይትድ ጋር ያለው እህል ውሀ ሊያከትም መቃረቡ ተሰምቷል፡፡ እንደ ቱቱ ስፖርት ዘገባ ከሆነ ዩናይትዶች የቀኝ መስመር ተከላካዩን በወርሀ ጥር ለመልቀቅ እንደተሰናዱ እና ሆዜ ሞሪንሆም በቀኝ ተከላካይ ቦታ ላይ ተቀዳሚ ምርጫቸው ኢኳዶራዊው አንቶንዮ ቫለንስያ እንደሆነ የጣሊያኑ ጋዜጣ ዘግቧል፡፡ 

ማስታወቂያ
ተወዳጁን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ እንዲሁም ጣፋጩን ላሊጋ ጨምሮ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ እና ኢሮፓ ሊግ ውድድሮችን መሸብኝ በር ይዘጋብኛል ሳይሉ ቤቶ ፈልሰስ ብለው በነጻነት የእግር ኳስ ውድድሮቹን  መመልከት ይሻሉ ? እንግዲያስ በ 0912210642 በመደወል ብሩክ ዲሽን ያናግሩ በተመጣጣኝ ዋጋ የሚወዱትን እግር ኳስ ዘና ብለው እንዲመለከቱ መፍትሄውን ይሰጦታል፡፡
image ዜና አርሰናል
“ጃክ ዊልሻየር በአርሰናል የእግር ኳስ ህይወቱን እንዲያገባድድ እፈልጋለው” አርሰን ዌንገር 

⚽ የ24 አመቱ እንግሊዛዊ አማካይ ጃክ ዊልሻየር ከከባድ ጉዳት ጋር ያሳለፍነውን የውድድር አመት ቢያሳልፍም በዘንድሮ የውድድር ዘመን ከጉዳት ነጻ ሆኖ ለ1 አመት በሚዘልቅ የውሰት ውል ኤዲ ሀው ለሚሰለጥነው በርን ማውዝን ተቀላቅሏል፡፡ የመድፈኞቹ አለቃ አርሰን ዌንገርም የውሰት ውሉን አስመልክቶ በትላንቱ ጋዜጣዊ መግለጫቸው ላይ እንደተናገሩት ከሆነ ጃክ ዊልሻየር መጫወት እንደሚፈልግ እና በወሰት ለሌሎች ክለቦች እንደሰጠው ስለ ጠየቀኝ ነው ለበርንማውዝ አሳልፌ የሰጠውት እርሱ ልዩ ኳሊቲ ካላቸው ወርልድ ክላስ  ተጫዋቾች መሀል አንዱ ነው፡፡ በቀጣይ ወደ አርሰናል ተመልሶ በቀድሞ ድንቅ አቋሙ ክለቡን እንደሚያገልግል አስባለው በአርሰናልም የእግር ኳስ ህይወቱን እንዲያገባድድ እፈልጋለው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

image

አሮን አሌክስ ኢዮቢ ሲመለስ ራምሴ እያገገመ ነው 

⚽ በሊጉ የመጀመሪያ ጨዋታ በኤሜሬትስ መድፈኞቹ ከሊቨርፑል አቻቸው ጋር ባደረጉት የሊጉ ፍልምያ ላይ ጉዳት ደርሶባቸው ከሜዳ ተቀይረው ከወጡት ተጫዋቾች መሀል አሌክስ ኢዮቢ እና አሮን ራምሴ ከጉዳታቸው በማገገም ላይ ይገኛሉ፡፡ አርሰን ዌንገር በትላንትናው ጋዜጣዊ መግለጫቸው ላይ  እንዳረጋገጡት አሌክስ ኢዮቢ ከጉዳቱ ሙሉ በሙሉ ያገገመ ሲሆን አሮን ራምሴ ሙሉ በሙሉ ከጉዳቱ ባለማገገሙ በሊጉ ዛሬ አመሻሽ ከሳውዝ አምፕተን እና የፊታችን ማክሰኞ በፓርክ ደ ፓሪስ አርሰናል ከ ፔይዤ ጋር ከሚያደርገው ጨዋታ ውጪ መሆኑን ይፋ ያደረጉ ሲሆን ለአለም ዋንጫ ማጣሪያ ሀገራቸውን ለማገልገል ወደ ደቡብ አሜሪካ ያቀኑት አሌክሲስ ሳንቼዝ እና ዴቪድ ኦስፒና ወደ ኮልኔይ የተመለሱ ሲሆን ምን አልባትም አርሰን ዌንገር አሌክሲስ ሳንቼዝ ቡድኑን ዘግይቶ መቀላቀሉን ተከትሎ ልምምድ በደንብ ባለመስራቱ ተቀያሪ አድርገው ወደ ሜዳ ያስገቡታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ማስታወቂያ
ተወዳጁን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ እንዲሁም ጣፋጩን ላሊጋ ጨምሮ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ እና ኢሮፓ ሊግ ውድድሮችን መሸብኝ በር ይዘጋብኛል ሳይሉ ቤቶ ፈልሰስ ብለው በነጻነት የእግር ኳስ ውድድሮቹን  መመልከት ይሻሉ ? እንግዲያስ በ 0912210642 በመደወል ብሩክ ዲሽን ያናግሩ በተመጣጣኝ ዋጋ የሚወዱትን እግር ኳስ ዘና ብለው እንዲመለከቱ መፍትሄውን ይሰጦታል፡፡
image ዜና ሊቨርፑል
አንፊልድ ከማስፋፊያው  በዋላ ከ54.000 ሺ በላይ ደጋፊዎችን ማስተናገድ ይችላል

⚽ የአንፊልድ የማስፋፊያ ስራ ተገባዷል ከዚህ ቀደም 45.362 ደጋፊዎችን ብቻ ያስተናግድ የነበረው ስቴዲየም የማስተናገድ አቅሙን ከፍ በማድረግ 8 ሺ በላይ አዲስ መቀመጫ ወንበሮችን በመግጠጠም 54 ሺ ደጋፊዎችን በማስተናገድ የሊጉ 6ተኛ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተመልካች ማስተናገድ የሚችል ስቴዲየም መሆን ችሏል፡፡ ዛሬ ምሽት ሊቨርፑል እና ሌስተር ሲቲ በሚያደርጉት የሊጉ 4ተኛ ሳምንት ጨዋታ የአመቱ የመጀመሪያውን የሜዳ ጨዋታ የሚያስተናግደው አንፊልድ ሮድ 5000 ቶን በሚመዝን ብረት እና 1.8 ሜትር እርዘመት ያላቸው ጡቦች እድሳት እና ማስፋፋያ ተደርጎለታል፡፡  አንፊልድ ሮድ ከዚህ ቀደም በተመልካች የማስተናገድ አቅም ይበልጡት ከነበሩት ሴንት ጀምስ ፓርክ እና ስቴዲየም ኦፍ ላይት ከፍ ብሎ የተቀመጠ ሲሆን ከኢትሀድ ፣ ከኦሎምፒክ እንዲሁም ኤሜሬትስ ስቴዲየሞች ደግሞ ዝቅ ብሎ 6ኛ ደረጃን ይዟል፡፡ በእንግሊዝ በርካታ ተመልካቾችን በመያዝ ዌምብሌይ በ90.000 ቀዳሚው ሲሆን በ2ኛ ደረጃ ላይ ኦልድትራፎርድ በ75.653 ተመልካቾችን በመያዝ ተቀምጧል፡፡

image

image ዜና ቼልሲ
ፈረንሳዊው አጥቂ ወደ ቼልሲ ተመልሷል

⚽ ፈረንሳዊው የኦሎምፒክ ደማርሴ የቀድሞ አጥቂ ከ2 አመት በፊት ከኪውፒአር ወደ ቼልሲ በዘመነ ሆዜ ሞሪንሆ አመራር ሰማያዊዎቹን ቢቀላቀልም ነገሮቹ ሁሉ በለንደን በስኬት የታጀቡ አልሆኑም የ2014/15 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን ከቼልሲ ጋር ከፍ ቢያደርግም የቋሚ ተሰላፊነት እድልን በተደጋጋሚ በቼልሲ ቤት ማግኘት ባለመቻሉ በዘንድሮ የውድድር ዘመን ወደ ክርስታል ፓላስ በውሰት ውል ቢያቀናም እዛም ሄዶ አልቀናውም ፡፡ በዚህ ሳምንት ከቡድኑ ጋር ልምምድ ጀምሮ በሳምንቱ መጨረሻ ክርስታል ፓላስ እና ሚድልስቦሮ በሚያደርጉት ጨዋታ ተሰላፊ ይሆናል ተብሎ ቢጠበቅም ልምምድ ላይ በገጠመው የቁርጭምጭሚት ጉዳት ምክንያት ለ2 ወራት ከሜዳ እንደሚርቅ ተነግሯል፡፡ ይህንን ተከትሎም ፈረንሳዊው አጥቂ ወደ እናት ክለቡ ቼልሲ መመለሱን የክርስታል ፓላሱ አለቃ አለን ፓርዲው ማረጋገጫ ሰጥተዋል፡፡

ሀዛርድ የቀድሞ የክለብ ጓደኛው ወደ ቼልሲ መመለሱ አስደስቶታል

⚽ ድራማዊ ከሆነ ትዕይንት በዋላ ሰማያዊዎቹን ዳግም የተቀላቀለው ብራዚላዊው የመሀል ተከላካይ ዴቪድ ሊዊዝ ወደ ቼልሲ መመለሱ እንዳስደሰተው ቤልጄማዊው የወርሀ ነሀሴ የሊጉ ኮከብ ተጫዋች ኤዲን ሃዛርድ ተናግሯል፡፡ በሰማያዊዎቹ ቤት ኢሮፓ ሊግ ቻምፒየንሰ ሊግ እና ኤፍ ኤካፕን በጋራ ከዴቪድ ሊዊዝ ጋር ያነሳው የ26 አመቱ ጥበበኛ እንደተናገረው ከሆነ ቼልሲን ለቆ ወደ ፓሪስ ሲያቀና መሄዴ ነው ሲሊኝ በእጅጉ ተከፍቼ ነበር ፡፡ ሆኖም ታላቅ ወንድሜ ዳግም ወደ ክለባችን ተመልሶ መምጣቱ በእጅጉ ተደስቻለው ሲል የዴቪድ ሊዊስ ወደ ቼልሲ መመለስ እንዳስፈነደቀው ኤደን ሃዛርድ ተናግሯል፡፡

image

image ዜና ሪያል ማድሪድ
ዚዳን ለ3ቱ ተጫዋቾች እረፍት ሰጥቷል

⚽ የስፔን ላሊጋ ከ10 ቀናት የኢንተርነሽናል ብሬክ እረፍት በዋላ ትላንት ምሽት ሪያል ሶሴይዳድ እና ኤስፓኞል ባደረጉት ጨዋታ ቀጥሎ ውሏል፡፡  ዛሬ ከሰአትም የ2015/16 የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ አሸናፊዎቹ ሪያል ማድሪዶች በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ 15ኛ ደረጃ የተቀመጠውን ኦሳሱናን ይገጥማሉ፡፡ ጨዋታውን ተከትሎ የሪያል ማድሪ አለቃ ዚነዲን ዚዳን ይፋ እንዳደረገው ከሆነ ከደቡብ አሜሪካ ሀገራት የአለም ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታቸውን አድረገው የተመለሱት ብራዚላዊያኑ ማርሴሎ እና ካዝሚሮ እንደሁም ኮሎምቢያዊው ኮከብ ሀሜዝ ሮድሪጌዝ በዚህ ጨዋታ ላይ የመሰለፍ እድላቸው ጠባብ መሆኑን ይፋ ያደረገ ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ ተጫዋቾቹ ከአድካሚ ጉዞ በዋላ ኪውዳድ መድረሳቸው ሲሆን በጨዋታው ላይም እረፍት እንደሚሰጣቸው ፈረንሳዊው አሰልጣኝ ፍንጭ ሰጥቷል፡፡ 

image

image ዜና ባርሴሎና
ጀርመናዊው የጎል ዘብ ጉዳት ገጥሞታል 

⚽ የክላውዲዮ ብራቮን ወደ ሲቲ ማምራት ተከትሎ የባርሴሎና ቁጥር 1 ተመራጭ ግብ ጠባቂ የነበረው ጀርናዊው ቴር ስቴገን በትላንትናው እለት በልምምድ ሜዳ ላይ ጉዳት ገጥሞታል፡፡ የቀድሞ የቦርሲያ ሞንቼግላርብሀ ግብ ዘብ የሆነው የ24 አመቱ ቴር ስቴገን መጠነኛ የሆነ የጡንቻ ጉዳቱን ተከትሎ ባርሴሎና በቀጣይ በላሊጋው እና በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ በሚያደርጋቸው 3 ጨዋታዎች ላይ ተሰላፊ እንደማይሆን የባርሴሎናው ልሳን ስፖርት የዘገበ ሲሆን መስከረም 11 ባርሴሎና እና አትሌቲኮ ማድሪድ በሚያደርጉት ጨዋታ ላይ ከጉዳቱ አገግሞ እንደሚደርስ ጋዜጣው አክሎ የገለጸ ሲሆን አዲሱ የባርሴሎና ፈራሚ ሆላንዳዊው ጃስፐር ሲለሰን ቦታውን ተከቶ ቀሪ ጨዋታዎች ላይ ተሰላፊ እንደሚሆን ጋዜጣ ጨምሮ ገልጽዋል፡፡
   

image

                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                       

ሱዋሬዝ 100ኛ ጨዋታውን ያለማድግ ፈተና ተጋርጦበታል  

⚽ ማራቶን ከተሰኘው የደቡብ አሜሪካ ሀገራት የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ በዋላ ዘግይቶ ባርሴሎናን የተቀላቀለው ሊዊስ ሱዋሬዝ በዛሬ ምሽቱ የዲፖርቲቮ አላቬስ ጨዋታ ቋሚ ሆኖ ላይ የመሰለፉ እድል ጠባብ መሆኑን ስፖርት አስነብቧል፡፡ ሀገሩ ኡራጋይ 2 የማጣሪያ ጨዋታ በዋላ ወደ ባርሴሎና የተመለሰው የ2015/16 የላሊጋው ኮከብ ግብ አስቆጣሪ ከፍተኛ የሆነ የድካም ስሜት ላይ በመሆኑ ምክንያት በዛሬ ምሽቱ ጨዋታ ላይ ተቀያሪ ወንበር ላይ ተቀምጦ ጨዋታውን የሚጀምር ሲሆን አዲስ ፈራሚው አልካስርን ጨምሮ ኔይማር እና ሜሲ የፊት መስመሩን ይመሩታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ሱዋሬዝ የዛሬው ጨዋታ ተሰላፊ ከሆነ በባርሴሎና ቆይታው 100ኛ ጨዋታው ሆኖ ይመዘገብለታል፡፡ 

  ቁጥራዊ እውነታዎች
 
➡ በሳምንቱ አጋማሽ ኖቲንግሀም ፎረስትን የተቀላቀለው የቀድሞ የአርሰናል አጥቂ ዴንማርካዊው ኒኮላስ ቤንዴትነር በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ታሪክ የመድፈኞቹ ተጫዋች ሆኖ ሀትሪክ መስራት የቻለ አራተኛው ተጫዋች ነው፡፡ ከአወዘጋቢው ዴንማርካዊ አጥቂ በተመሳሳይ ጅሩድ ሄነሪ እና ዌልቤክ በቻምፒየንስ ሊጉ ለመድፈኞቹ ሀትሪክ መስራት የቻሉ ብቸኞቹ ተጫዋች ናቸው፡፡ 

➡ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ታሪክ 5 ተጫዋቾች ብቻ ለሁለቱ የማንችስተር ከተማ ክለቦች ዩናይትድ እና ሲቲ ተጫውተው ማሳለፍ ችለዋል፡፡ እነርሱም አንዲ ኮል ፣ ካንቸልስኪ ፣ ፒተር ሽማይክል፣ ሀርግሬቭስ እና ካርሎስ ቴቬዝ ናቸው፡፡ 

➡ ብራዚላዊው የ24 አመቱ አጥቂ ኔይማር ዳ ሲልቫ ለብሄራዊ  ቡድኑ ባደረጋቸው 72 ጨዋታዎች 48 ግቦችን ማስቆጠር ችሏል፡፡ ሊዮኔል ሜሲ ፣ ቴሪ ዳንኤል ሄነሪ እና ዝላታን ኢብራሂሞቪች በጋራ በ24 አመታቸው ያስቆሩት ግብ መጠን 48 ነው፡፡

➡ የመድፈኞቹ ኮከብ ሚሶት ኦዚል ባሳለፍነው የውድድር ዘመን አርሰናሎች በሊጉ ላስቆጠሯቸው 25 ግቦች የእርሱ እጅ አለበት ይህም በመድፈኞቹ ቤት ጀርመናዊውን አማካይ ቀዳሚ ተጫዋች ያደርገዋል፡፡

➡ በ2016/17 የውድድር ዘመን በ3 ሳምንት የውድድር ሂደት በርካታ የግብ እድሎችን የፈጠሩ ተጫዋቾች
በ1ኛ ሳምንት  የሳውዝ አምፕተኑ ዱሳን ታዲች (6)
በ2ኛ ሳምንት የቶትንሀም ሆትስፐሩ ኤሪክ ላሜላ (5)
በ3ኛ ሳምንት የክርስራል ፓላሱ ጄሰን ፑንቸን (6)

ማስታወቂያ
ተወዳጁን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ እንዲሁም ጣፋጩን ላሊጋ ጨምሮ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ እና ኢሮፓ ሊግ ውድድሮችን መሸብኝ በር ይዘጋብኛል ሳይሉ ቤቶ ፈልሰስ ብለው በነጻነት የእግር ኳስ ውድድሮቹን  መመልከት ይሻሉ ? እንግዲያስ በ 0912210642 በመደወል ብሩክ ዲሽን ያናግሩ በተመጣጣኝ ዋጋ የሚወዱትን እግር ኳስ ዘና ብለው እንዲመለከቱ መፍትሄውን ይሰጦታል፡፡
ይህን ያውቁ ኖሯል ?

➡ እንደ እ.ኤ.አ በ2007 በአርጀንቲና አፓርቹራ ሊግ የአሁኑ የአርሰናል ኮከብ አሌክሲስ ሳንቼዝ እና በጉልበት ጉዳት ምክንያት የቀደሞ የጎል ጀግናነቱን ያጣው ራዳሚል ፋልካኦ ለሊቨርፕሌት ይጫወቱ ነበር፡፡ አስገራሚው ነገር በወቅቱ የሊቨርፕሌት አሰልጣኝ የነበረው የአሁኑ የአትሌቲኮ ማድሪድ አሰልጣኝ ዲያጎ ሲሞኔ ነበር፡፡

➡ የሪያል ማድሪዶቹ ሉካ ሞድሪች እና ኢስኮ የሎስ ብላንኮን ማሊያ ከማጥለቃቸው በፊት ከቀድሞ በነበሩባቸው ክለቦች የስፔኑን ባርሴሎና ሲደግፉ እና ሲያደንቁ ነበር፡፡ ሁለቱ አማካዪች ለባርሴሎናም ያላቸውን ፍቅር ለመግለጽ መለያውን በማድረግ በተደጋጋሚ ፎቶዎችን ይነሱ ነበር፡፡ 

➡ የቦርሲያ ዶርትመንዱ አማካይ ስፍራ ተጫዋች ማርኮ ሩስ ከ2 አመታት በፊት መኪና እንዳያሽከርከር እና 570 ሺ ዩሮ መቀጮ እንዲከፍል  በጀርመን ትራፊክ ጽህፈት ቤት ቅጣት ተጥሎበት የነበረ ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ ያለመንጃ ፍቃድ መኪና ሲያሽከረክር መገኘቱ ነው፡፡ ከሁለት አመት ቅጣት በዋላ ተጫዋቹ ቅጣቱን ጨርሶ መኪና ማሽከርከር ጀምሯል፡፡
 
➡ አርጀንቲናዊው የቀድሞ የኢንተርሚላን አጥቂ ዲያጎ ሚሊቶ የሚላን ደርቢ (በደርቢ ዴላ ማዶዲኒያ) ላይ ሀትሪክ መስራት ብቸኛው ተጫዋች ነው፡፡ በዚህ ደርቢ ጨዋታ ላይ ከእርሱ በፊትም ሆነ ከእርሱ በዋላ ሀትሪክ የሰራ ተጫዋች የለም፡፡

➡ የአሁኑ የአርሰናል አለቃ አርሰን ዌንገር ከ1987 እስከ 1994 የፈረንሳዩን ሞናኮ ያሰለጥኑ በነበረ ወቅት ተቀያሪ ወንበር ላይ ተቀምጠው ቡድናቸው ሞኖክነ እየመሩ ሲጋራ አጭሰዋል፡፡

ከዜናዎቹ ጋር ፈይሰል ሀይሌ ነበርኩ መልካም የአዲስ አመት ዋዜማ ይሁንላቹ መጪው አመት የፍቅር የሰላም የጤና እና የብልጽግና እንዲሆንላቹ ኢትዮአዲስ ስፖርት ትመኛለች፡፡

Advertisements