Skip to content
Advertisements

ቼልሲ ከ ሊቨርፑል፣ የሳምንቱ ታላቅ ጨዋታ ቅድመ ትንታኔ

ወንድወሰን ጥበቡ | መስከረም 4፣ 2008 ዓ.ም


ቼልሲ በፕሪሚየር ሊጉ ለመጀመሪያ ጊዜ ከባድ ተቀናቃኙን ሊቨርፑልን አርብ ምሽት ይገጥማል። ኢትዮአዲስስፖርትም እንደተለመደው የሳምንቱን ታልቅ ጨዋታ ቅድመ ትንታኔ በሚከተለው መልኩ አቅርባለች።

ሊቨርፑል አርሰናልን 4ለ3 በመርታት፣ በበርንሌይ 2ለ0 በመሸነፍ እንዲሁም ሌስተርን 4ለ1 በመርታት የፕሪሚየር ሊጉን ጅማሮውን አንዴብልጭ መልሶ ደግሞ ጥፍት በሚል ብቃት ጀምሯል።

የየርገን ክሎፑ ቡድን በዚህ የውድድር ዘመን ከወዲሁ በሁሉም ጨቃታዎች ላይ 14 ግቦችን ከመረብ ላይ አሳርፏል። ከሊቨርፑል በላይ ግቦችን (21) ማስቆጠር የቻለው ማንችስተር ሲቲ ብቻ ነው።

የክለቦቹ ዜናዎች

ዴቪድ ለዊዝ ከፒኤስጂ ቼልሲን በ34 ሚ.ፓ መልሶ ከተቀላቀለ በኋላ በዚህ ጨዋታ የመጀመሪያ ጨዋታውን የሚያደርግ ይሆናል።

በዚሁ መሰረት ብራዚላዊው ተከላካይ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ከስዋንሲ ጋር በተደረገ ጨዋታ ላይ የቁርጭምጭሚት ጉዳት የገጠመውን ጆን ቴሪን ተክቶ የሚገባም ይሆናል።

የሊቨርፑሉ ተከላካይ ደያን ሎቭረን በአይኑ ላይ በገጠመው ጉዳት የተነሳ ሊቨርፑል ሌስተርን 4ለ1 የረታበት ጨዋታ ካለፈው በኋላ አገግሞ በዚህ ጨዋታ ላይ እንደሚሰለፍ ይጠበቃል።

ከብራዚል ወደክለቡ ሲመለስ ረጅም የሆነ የበረራ ጊዜን ያሳለፈው እና በሌስተሩ ጨዋታ ላይ እንዲያርፍ የተደረገው ፊሊፔ ኮቲኒሆም በዚህ ጨዋታ ላይ የመጀመሪያ ተሰላፊነት ዕድልን ሊያገኝ የሚችል ተጫዋች ነው።

ግምታዊ አሰላለፎች

የሁለቱ ክለቦች የእርስበርስ ግንኙነት እውነታዎች

 • ቼልሲ ሊቨርፑልን በስታንፎርድብሪጅ በገጠመባቸው ያለፉት ዘጠኝ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው ሁለት ጨዋታዎች ላይ ብቻ ነው። (ድል2፣ አቻ3፣ ሽን4)
 •  ይህ በሁለቱ ክለቦች መከካል የሚደረግ 175ኛ ጨወታ ሲሆን ሊቨርፑል 75 ጊዜ ሲያሸንፍ ቼልሲ 61 ጊዜ ማሸነፍ ችሏል፤ በ38 ጨዋታ ላይ ደግሞ አቻ ተለያይተዋል።

ቼልሲ

 • ቼልሲ ከባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ወዲህ በፕሪሚየር ለመጀመሪያ ጊዜ በሜዳው ሶስት ተከታታይ ድሎችን ማግኘት ችሏል።
 • ከፕሪሚየር ሊጉ የወረደው አስቶንቪላ ብቻ በ2015-16 የውድድር ዘመን ቼልሲ በሜዳው ማሸነፍ ከቻለው አምስት ጨዋታዎች ያነሱ የጨዋታ ድሎችን አስመዝግቧል።
 • ሰማያዊዎቹ በውድድር ዘመኑ የመጀመሪያዎቹ አራት ጨዋታዎች ላይ ቢያንስ ሁለት ግቦችን ማስቆጠር ችለዋል።
 • ዲያጎ ኮስታ ከወዲሁ ለአራት ጊዜያት ያህል ኳስና መረብን ማገናኘት የቻለ ሲሆን፣ ባለፈው የውድድር ዘመን ግን እስከገና ደረስ ይህን ያህል ግብ ማስቆጠር አልተቻለም ነበር።
 • አንቶኒዮ ኮንቴ በአሰልጣኝነት ዘመናቸው በሜዳቸው ያለፉትን የመጨረሻ 21 ጨዋታዎችን ሲያሸንፉ ለመጨረሻ ጊዜ ጁቬንቱስ በሳምፕዶሪያ በጥር ወር 2013 ከተሸነፈ ወዲህም በ30 ጨዋታዎች ላይ ሽንፈት አልገጠማቸውም።

ሊቨርፑል

 • ሊቨርፑል ባለፉት 17 ጨዋታዎች 31 ነጥቦችን ሰብስበዋል። በዚህ የሚበለጠው በማንችስተር ዩናይትድ (34ነጥብ) ብቻ ነው።
 • ቀዮቹ በ2016 በፕሪሚየር ሊጉ ከየትኛውም ክለብ በላቀ 50 ግቦችን ከመረብ ላይ ማሳረፍ ችለዋል። በስምንት ጨዋታዎች ላይም ሶስትና ከዚያ በላይ ግቦችን ከመረብ አሳርፈዋል።
 • ይሁን እንጂ በዚሁ ዓመት ግብ ሳይቆጠርበት መውጣት የቻለው በየካቲት ወር ከአስቶንቪላ ጋር ባደረግው ጨዋታ ብቻ ነው።
 • ከግንቦት 2005 ወዲህም ለማጀመሪያ ጊዜ በ2016 በ9 ጨወታዎች ላይ ግብ እየተቆጠረባቸው ዘልቀዋል።

 • አሰልጣኞቹ ምን አሉ?

  የቼልሲው አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ “ዴቪድ ልዊዝ ለመጀመሪያ ጊዜ ለእኛ ይጫወታል። በዚህም በራስ መተማመን ይሰማናል።

  “ጥሩ ብቃቱን እንደሚያሳየንም እንጠብቃለን። ዴቪድ ጥሩ ተጫዋች እንደሆነ እናውቃለን። ጥሩ ብቃቱን ያሳየን ዘንድም በጥሩ ብቃቱ ላይ እንዲገኝ እንሰራለን።

  “በእሱ እተማመናለሁ። በልምምድ ወቅት እሱ ጥሩ ተጫዋች ነው። ጥሩ ነገሮችንም ከእሱ ተመልክቻለሁ።”

  የሊቨርፑሉ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ስለቼልሲው ዲያጎ ኮስታ “እሱ በሜዳ ላይ እውነተኛ ተፋላሚ ነው። ሁልጊዜም እካላዊ ብቃቱን ይጠቀማል። ይህ ደግሞ ምርጥ ነገሩ ነው። በስዋንሲው ጨዋታ ላይም የማይቀመስ ሆኖ ነበር።

  “ከዓለማችን ትልቅ ብቃት ካላቸው ተጫዋቾች መካከል አንዱ ነው። የእግር ኳስ ደጋፊዎችም ስላንተ ሊናገሩት የሚገባው ነገር ይህ ነው።

  “ባለፈው የውድድር ዘመን የቼልሲ ዘመን አልነበረም። አሁን ግን ወደብቃታቸው ተመልሰዋል። ስለዚህ ለእውነተኛ ፍልሚያ መዘጋጀት ግድ ይለናል።

  Advertisements
  %d bloggers like this: