Skip to content
Advertisements

በአርሰናል የግብ ዕድሎችን የሚፈጥር አዲስ ተጫዋች መጥቷል

ወንድወሰን ጥበቡ | ሰኞ መስከረም 9፣ 2008 ዓ.ም


ባለፉት የውድድር ዘመኖች ለክለቡ በርካታ የግብ ዕድሎችን በመፍጠር መሱት ኦዚል ከአርሰናል ተጫዋቾች ሁሉ የላቀ ተጫዋች ነበር።

ይሁን እንጂ ለመድፈኞቹ ከአራት የውድድር ዘመኖች በኋላ ጀርመናዊው ተጫዋች በዚህ የውድድር ዘመን ካስቆጠራት ብቸኛ ግብ በስተቀር የግብ ዕድል በመፍጠር ምንም ዓይነት ቀጥተኛ ተፅእኖ መፍጠር አልቻለም።

ይሁን እንጂ መልካም አጋጣሚ ሆኖ አርሰን ቬንገር አሁንም የግብ ዕድልን የሚፈጥር ልዩነት ፈጣሪ ተጫዋች አላጡም። እሱም አሌክስ ኢዎቢ ነው።

የ20 ዓመቱ ናይጄሪያዊ ተጫዋች በ2016 የቀን ቀመር በሊጉ ላይ ከየትኛውም የአርሰናል ተጫዋች በላቀ አምስት ግብ መሆን የቻሉ ኳሶችን በማመቻቸት የክለቡ ቁልፍ ተጫዋች ነበር። ምንም እንኳ የክንፍ ተጫዋቹ መጫወት የቻለው በሶስት የሊግ ጨዋታዎች ላይ ብቻ ቢሆንም ከአምስቱ ሶስቱን ያቀበለው በዚህ የውድድር ዘመን ላይ ነበር።

Advertisements
%d bloggers like this: