Skip to content
Advertisements

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የዕጣ አወጣጥ ስነ ስርዓት የቀጥታ ስርጭት

የ2009 የውድድር አመት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የዕጣ አወጣጥ ስነስርዓት በካፒታል ሆቴል እየተካሄደ ይገኛል፡፡
ፕሬዝዳንት ጁነዲን የመግቢያ ንግግር እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

==>  የክብር እንግዳ የሆኑት አቶ ሃይለማርያም አስራት(የቀድሞ የብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ፣ ኢንተርናሽናል ዳኛና አሰልጣኝ) ፣ ንጉሴ ገብሬ (የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋችና አምበል) ፣ አስቻለው ደሴ ( የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች) ናቸው፡፡

==>  ከሊግ ኮሚቴ የተወከሉት ስለዕጣ አወጣጥ ስርአቱ ገለፃ እያደረጉ ነው፡፡

==>  በዚህም መሰረት ሁለት የዕጣ ሰዓቶች የተዘጋጁ ሲሆን በአንደኛው የክለቦቹ ስም ዝርዝር በሁለተኛው ደሞ፡ከአንድ እስከ 16 ቁጥር የተፃፈባቸው ዕጣዎች ይገኛሉ፡፡

==>  በዕጣው መሰረት ወላይታ ድቻ በመጀመሪያ ጨዋታው መከላከያን ያስተናግዳል

==>  ሲዳማ ቡና ፋሲል ከነማን በሜዳው የሚገጥም ይሆናል፡፡

==>    ሻምፒዮኑ ቅዱስ ጊዮርጊስ በሜዳው ከአርባምንጭ ከነማ ጋር  የመጀመሪያ ጨዋታውን ያደርጋል

==>  አዲስ መጪው ጅማ አባቡና በሜዳው ኢትዮ ኤሌክትሪክን ያስተናግዳል

==> አዳማ ከነማድሬዳዋ ከነማ ጋር አዳማ ላይ ይጫወታሉ

==> ሃዋሳ ከነማአዲስ አበባ ከተማ ጋር ሃዋሳ ላይ ለመጫወት ተደልድለዋል

==> ወልዲያ ከነማ በሜዳው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ይገጥማል

==> ኢትዮጵያ ቡናደደቢት ጋር የውድድር አመቱን መክፈቻ ያደርጋሉ

የመጀመሪያው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በዚህ መልኩ የሚጀመር ሲሆን ቀጣይ ጨዋታዎችን በድረ ገፃችን ላይ የምናሳውቅ ይሆናል

Advertisements
%d bloggers like this: