Skip to content
Advertisements

አፍሪካ:-የጋና ብ/ቡድን አሰልጣኝ አቭራም ግራንት ለ 3 ወራት ደሞዝ እንዳላገኙ ታውቋል

By Eyob Dadi


አፍሪካ ውስጥ ከተጨዋቾች ጥቅማጥቅም እና ከአሰልጣኞች ደሞዝ ጋር የሚፈጠሩ ውዝግቦች የተለመዱ ናቸው።

የጋናው አሰልጣኝ አቭራም ግራንትም ላለፉት 3 ወራት ደሞዝ ሳይከፈላቸው እየሰሩ እንዳለ ነው የተሰማው።

ምክንያቱ ደግሞ የአሰልጣኙን ደሞዝ ለመክፈል የተስማማው የጋና
 ብሄራዊ የፔትሮሊየም ኮርፖሬሽን ክፍያው ለመክፈል ባለመቻሉ ነው።

አንዳንድ ዘገባዎች ተቋሙ ለአሰልጣኙ ደሞዝ መክፈል ያቆመው በአገሪቷ ስፓርት ሚኒስቴር ትእዛዝ እንደሆነ ይጠቅሳሉ።

ጋና ለአለም ዋንጫ ማጣሪያ ከዩጋንዳ ጋር ጥቅምት 7 የምትጫወት ሲሆን የአሰልጣኙ የደሞዝ ውዝግብ ውጤቱ ላይ ተጽእኖ እንዳይፈጥር ተሰግቷል።

አቭራም ግራንት ኮንትራታቸው ከ 2017 የአፍሪካ ዋንጫ በኋላ የሚያበቃ ሲሆን ከ ብ/ቡድኑ ጋር የመቀጠላቸው ነገር የታወቀ ነገር የለም።

Advertisements
%d bloggers like this: