Advertisements
ትኩስ ዜናዎች

ጆርዳን 2016: – በጆርዳኑ የሴቶች U17 የአለም ዋንጫ የአፍሪካ ተወካዮች ጅማሪያቸው አላማረም

By Eyob Dadi


በጆርዳን አዘጋጅነት ሰዎስተኛ ቀኑ ላይ የደረሰው የፊፋ  የሴቶች U 17 የአለም ዋንጫ የአፍሪካ ተወካዮች አጀማመራቸው መልካም አልሆነም።

አፍሪካን የወከሉት ካሜሮን፣ናይጄሪያና ጋና ሽንፈት አጋጥሟቸዋል።

በተለይም ትናንት በተደረጉት ጨዋታዎች ጋና  በጃፓን  5-0 በሆነ ሰፊ ውጤት ተሸንፋለች።

በዛርቃ ፕሪንስ መሀመድ ኢንተርናሽናል ስታድየም የተደረገው የጃፓን እና የጋና ጨዋታ በጃፓኖቹ ሙሉ የጨዋታ የበላይት ታይቶበታል።

ጋና ከዚህ ቀደም በዚህ ውድድር ላይ ከአፍሪካ ግማሽ ፍጻሜ የገባች ብቸኛዋ አገር እንደሆነች ይታወሳል።

ሌላኛዎቹ የአፍሪካ ተወካዮች ናይጄሪያ በ ብራዚል  1-0 ስትሸነፍ፣ካሜሮን በበኩሏ በካናዳ 3-2 በሆነ ውጤት በመሸነፍ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን አጠናቀዋል።

Advertisements
About ዕዮብ ዳዲ (1422 Articles)
ይህን ጽሁፍ ያዘጋጀሁላችሁ የኢትዮአዲስ ስፓርት ድረገጽ አዘጋጅ እና የስፓርት ፀሀፊ ዕዮብ ዳዲ ነኝ።
%d bloggers like this: