Skip to content
Advertisements

በእግር ኳሱ አለም ምን አልባትም እስካሁን ያልሰሟቸው 20 አስገራሚ እውነታዎች (ክፍል 1)

picsart_10-20-02-41-20

ለኢትዮአዲስ ስፖርት በፈይሰል ኃይሌ ፧ ሀሙስ ጥቅምት 10 2009

ኢትዮአዲስ ስፖርት በምርጥ 20 መሰናዶዋ ለዛሬ በእግር ኳሱ አለም 20 የእግር ኳሱ አስገራሚ እውነታዎችን በክፍል 1 ከታች እንደሚከተለው አዘጋጅታለች ፡፡

➡ 1. በአለማችን የመጀመሪያውን የጨዋታ የቀጥታ ስርጭትን በቴሌቭዥን በማሳየት ለአለም በማስተዋወቅ እንግሊዝን የሚቀድማት የለም የሀያል ሊግ ባለቤት የሆነቸው ብሪታንያ እንደ ኤሮፒያን አቆጣጠር በ1937 በሀይበሪ ስቴዴየም አርሰናል ያደረገውን ጨዋታ በቀጥታ ለእንግሊዛዊያን ማስተላለፍ ችላለች፡፡

➡ 2. አለምን በብቃቱ በግርምት ለበርካታ ጊዜያት አፍ ማስያዝ የቻለው ብራዚላዊው ጥበበኛ ሮናልዲንሆ ጎቾ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚዲያዎችን ትኩረት ማግኘት የቻለው በታዳጊ ውድድሮች ላይ ክለቡ ተጋጣሚውን 23-0 ሲረታ 23ቱንም ግቦች ራሱ በማስቆጠር ነበር፡፡

➡ 3. አርጀንቲናዊው አማካይ ጃቪየር ዛኔቲ በጣሊያን ሴሪያ የረጅም አመታት የእግር ኳስ ቆይታው 548 ጨዋታዎችን ያደረገ ሲሆን በእነዚህም ጨዋታዎች ላይ አንድም ቀይ ካርድ ተመልክቶ አያውቅም፡፡ ልክ እንደ እርሱ ሁሉ የቀድሞ የማን ዩናይትድ ህያው ተጫዋች ሪያን ጊግስ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በርካታ ጨዋታዎችን ያደረገ ሲሆን 1ድም ቀይ ካርድ ግን አልተመለከተም፡፡

➡ 4. የካሪየሰ ሊቨርፑልን መቀላቀል ተከትሎ የቋሚ ተሰላፊነት እድል ጀንበር እየጠለቀችበት የሚገኘው ቤልጄማዊው የጎል ዘብ ሲሞን ሚኞሌት 5 ቋንቋዎችን አቀላጥፎ መናገር ይችላል፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን ግብ ጠባቂው የፖለቲካል ሳይንስ የዲግሪ ምሩቅም ጭምር ነው፡፡

➡ 5. በአለም ዋንጫ ውድድሮች ላይ እንደ አውሮፓ እና ላቲን አሜሪካ ሀገራት ዋንጫውን የወሰደ አህጉር የለም ሁለቱ አህጉሮች በውድድሩ ላይ ንግስናቸውን ከደፈ የሰነበቱ ሲሆን በተለይም አውሮፓ በ1930 እና በ1950 ከተደረጉት የአለም ዋንጫ ውድድሮች ውጪ በ18 ውድድሮች ላይ ተወካዮቿ የፍጻሜው ተፋላሚዎች ነበሩ፡፡
➡ 6. በእግር ኳስ ህግ አንድ ጨዋታ ላይ አንድ ተጋጣሚ ከ5 ተጫዋቾች በላይ ከሜዳ በቀይ ከተሰናበቱበት ጨዋታው በፎርፎ የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡ ይህ ህግ ግን በፓራጓይ የሚሰራ አይመስልም ስፖርቲቮ አሚሊያኖ እና ጄኔራል ካባሊየሮ ባደረጉት ጨዋታ ከ2ቱ ቡድኖች 20 ተጫዋቾች ከሜዳ በቀይ ካርድ ተሰናብተዋል፡፡

➡ 7. ብራዚላዊው አጥቂ ሮናልዶ ሊውስ ናዛሪዮ ዲሊማ በእግር ኳስ ህይወቱ በብሄራዊ ቡድን ደረጃ ሁሉንም ድሎች ቢያሳካም በማድሪድ ኢንተር ሚላን ኤስ ሚላን ፔይዤ እና ባርሴሎና ቆይታው ግን የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ማሳካት አልቻልም፡፡ ልክ እንደ ሮናልዶ ሁሉ ዝላታን ኢብራሂሞቪችም የቻምፒየንስ ሊግ ስኬትን አላጣጣመም

➡ 8. እግር ኳስን ይወዳሉ መጫወቱስ ላይ እንዴት ኖት ? የሚጫወቱበት ኳስስ የት ሀገር እንደተሰራ ግንዛቤ አሎት ? አስገራሚው ነገር የአለማችን እግር ኳስ ተጫዋቾች የሚጫወቱባቸው 80% የሚሆኑት ኳሶች የሚመረቱት በፓኪስታን ነው፡፡ ይህች ሀገር ኳስ አምራች ብትሆንም በርካታ አመታት በትላልቅ ውድድሮች ላይ ተሳታፊ ሆና አታውቅም፡፡

➡ 9. በአለም እግር ኳስ ታሪክ እንደ ስታድ ኦሎምፒክ ለሚረን የተሰኘው ክለብ ያህል በርካታ ግቦች የተቆጠሩበት ክለብ ማግኘት ይዳግታል፡፡ የማዳጋስካሩ ክለብ በ1 ጨዋታ ላይ 149-0 በሆነ ውጤት የተሸነፈ ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ ተጫዋቾቹ በዳኛው ውሳኔ መበሳጨታቸውን ተከትሎ ራሳቸው ላይ ባስቆጠሩት ግብ ነው፡፡

➡ 10. የአለማችን ፈጣን ግብ 1998 ሲሆን የተቆጠረችው ያስቆጠራትም ኡራጋዊው ሪካርዶ ኦሊቬራ ነው፡፡ ይህ ኡራጋዊ አጥቂ ኳስ እና መረብን ለማገናኘት 2.8 ሰከንድ ብቻ ነበር የፈጀበት፡፡ ይህንን ተከትሎም ግቧ እስካሁን ድረስ የአለማችን ፈጣኗ ግብ ሆኖ ተመዝግባለች፡፡

picsart_10-20-02-34-55

➡ 11. የኮትዲቯሩን አሴጅ አቢጃን የተሰኘ ክለብ እናስተዋውቃቹ ይህ የአፍሪካ ሀያል ክለብ በአለም እግር ኳስ ላይ ለረጅም ጊዜያት ሳይረታ የቆየ ሀያል ክለብ ነው ምን አልባትም ይህንን ሀያልነት በቀጣይ ጌዜ በእኛ ትውልድ አንመለከተው ይሆናል፡፡ ይህ ክለብ ከ1989-1994 ያደረጋቸውን የእግር ኳስ ውድድሮች ላይ ሽንፈት የሚባል ነገር ያልቀመሰ ሲሆን የጨዋታዎቹ ብዛት ደግሞ 108 ነው፡፡

➡ 12. በእግር ኳሱ አለም እስካሁን ድረስ በአንድ ፕሮፌሽናል ጨዋታ ላይ በርካታ ግቦችን በማስቆጠር ፈረንሳዊውን ስቴፋን ስታኒስን የሚያህል ተጫዋች የለም፡፡ ፊት አውራሪው እንደ ኤሮፒያን አቆጣጠር 1942 ክለቡ ሬሴንግ ሌንስን በረታበት ጨዋታ ላይ ከተቆጠሩት ግቦች መሀል 16 ከመረብ ማገናኘት የቻለ ሲሆን እስካሁን ድረስም የሱን ያህል ግብ በአንድ ጨዋታ ያስቆጠረ ተጫዋች የለም

➡ 13. ጀርመናዊው የባየር ሙኒክ ግብ ጠባቂ ማኑኤል ኑኤር በ2013 በዲዝኒ አማካኝነት ተሰርቶ የቀረበው ሞንስተርስ ዩኒቨርሲቲ የተሰኘ የካርቶን ፊልም ላይ ተውኗል፡፡ አስደማሚው ግብ ጠባቂ ፍራንክ ማካይ የተባለ ገጸ ባህሪን ወክሎ በድምጹ የተወነ ሲሆን ፊልሙም በወቅቱ በጀርመን የፊልም ደረጃ ላይ በቀዳሚነት ተቀምጦ ነበር፡፡

➡ 14. የኤደን ሀዛርድ ውሻ ስም ሊዮ ነው የጋሪ ካሂልም ውሻ ስም ሊዮ ሲሆን ሌላኛው የስፔናዊ አጥቂ ፈርናንዶ ቶረስ ውሻ ስምም ሊዮ ነው፡፡ ሊዮ ማለት በስፔን የሜሴ ቅጽል ስም ሲሆን በላቲን ግን ሊዮ ማለት አንበሳ እንደማለት ነው የቼልሲ ተጫዋቾችም የውሻቸውን ስም በላቲን ወርድ በመጠቀም አንበሳ ሲሉ ሰይመዋል፡፡

➡ 15. አሁን አሁን በሀገረ አሜሪካ ተወዳጅነት እያተረፈ የመጣው እግር ኳስ በአሜሪካ መጠሪያ ስሙ ሶከር ሲሆን ሁሉም አሜሪካዊያን በሚባል መልኩ ፉትቦል የምትለውን የእንግሊዛዊያን ቃል አይጠቀሙም፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን በ1994 በአሜሪካ ተካሂዶ ስለነበረው የአለም ዋንጫ ውድድር በርካታ አሜሪካዊያን ውድድሩ በሀገራቸው መካሄዱን እንኳ አያውቁም ነበር፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ለእግር ኳስ ያላቸው አናሳ መሆኑን ተከትሎ ነው፡፡

➡ 16. ሪዮ ማቩባ የተሰኘው እግር ኳሰኛ መታወቂያው እና ፓስፖርቱ ላይ የትውልድ ስፍራ የሚለው ቦታ ላይ የሰፈረው ውቅያኖስ ነው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ተጫዋቹ ወላጅ እናቱ ስትወልደው ባህር ላይ ስለነበር ነው፡፡

➡ 17. በአለማችን የሚገኙ 27 ክለቦች 1 ቅጽል ስም ይጠቀማሉ ይህም ስም ቢጫ ሰርጓጆቹ ሲሆን በይብለጥ ግን በዚህ የቅጥል ስም ስያሜ ታዋቂነትን ያተረፈው የስፔኑ ክለብ ቪያሪያል ነው፡፡

➡ 18. ደንዲ ዩናይትድ የተባለ ክለብ ያውቃሉ ፡ ካላወቁት ካሁኑ በደንብ ይወቁተ ይህ ክለብ ባርሴሎናን 4 ጊዜያት ያህል አግኝቶት 4ቱንም ጊዜ ማሸነፍ የቻለ ሲሆን 100% የአሸነፊነት ስኬትን ባርሴሎና ላይ መቀዳጀት ችሏል፡፡

➡ 19. እግር ኳስን አንግሊዛዊያን መመስረታቸውን ደጋግመው ቢናገሩም መዛግብት እንደሚያመለክቱት ግን እግር ኳስ ምስረታውን ያደረገው በቻይና ሲሆን ወቅቱም ከክርስቶስ ልደት በፊት 476 ነው፡፡

➡ 20. የሪያል ማድሪዱ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች ክሮሺያዊው ሉካ ሞድሪች እና የቀድሞው የሚድልስቦሮ እና ኒውካስል አጥቂ ማርክ ቪዱካ የአክስታማቾች ልጆች ናቸው፡፡

Advertisements

መንሀጁል ሀያቲ View All

የኢትዮአዲስ ስፖርት የስፖርት ዜናዎች ፀሀፊ

%d bloggers like this: