Skip to content
Advertisements

የሳምንቱ ታላቅ ጨዋታ፡- ኢትዮጵያ ቡና ከ ደደቢት

images.jpg

By Eyob Dadi

የ 2009 አ.ም የኢትዮጵያ ፕሪምየርሊግ ከ አራት ወር በላይ እረፍት በኋላ ቅዳሜ እና እሁድ በሚደረጉ ጨዋታዎች ይጀመራል፡፡

ሁለት ጊዜ ፕሮግራም ከተያዘለት እለት የተራዘመው የዘንድሮው የአገሪቷ ታላቁ ሊግ ጨዋታ ቅዳሜ ተጀምሮ እስከ ሰኔ ወር ድረስ እንደሚካሄድ ይጠበቃል፡፡

ቅዳሜ በአአ ስታድየም የአምናው ሻምፕዮን ቅ/ጊዮርጊስ ከደቡቡ ተወካይ አርባምንጭ ከተማ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ውድድሩ ይጀመራል፡፡ሻምፕዮኖቹ ዋንጫ ባነሱበት  2008ቱ የፕ/ሊግ ውድድር ላይ በሜዳቸው ከአርባምንጭ ጋር ያደረጉት የ 22ኛ ሳምንት ጨዋታ በደጉ ደበበ ጎል ጎል በአቻ ውጤት አጠናቀዋል፡፡በእለቱ ለአርባምንጭ ጎሉን ያስቆጠረው የቡድኑ የአመቱ ኮከብ ጎል አስቆጣሪ ሆኖ ያጠናቀቀው ተሾመ ታደሰ ነበር፡፡

ሁለቱ ቡድኖች ቅዳሜ 10፤00 ላይ በአአ ስታድየም በሚያደርጉት ጨዋታ የ 2009 አ.ም የኢትዮያ ፕሪምየርሊግ መክፈቻ ጨዋታ ይሆናል፡፡

የሳምንቱ ታላቅ ጨዋታ እንደሚሆን የሚጠበቀው ግን ኢትዮጵያ ቡና ከ ደደቢት ጋር የሚያደርገው የ እሁዱ የ አአ ስታድየም ጨዋታ ነው፡፡ሁለቱ ቡድኖች ቡድናቸውን በአዳዲስ ተጨዋቾች ካጠናከሩ በኋላ የሚያደርጉት የአመቱ የመጀመሪያ ጨዋታ ከፍተኛ ፉክክር እንደሚደረግበት ይጠበቃል፡፡

ሳሙኤል ሳኑሚ የቀድሞ ቡድኑን የሚገጥምበት እንዲሁም ጌታነህ ከበደ ከደ/አፍሪካ ቆይታ በኋላ በድጋሚ የቀድሞ ቡድኑን ተቀላቅሎ የመጀመሪያ ጨዋታውን የሚያደርግበት እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡

ኢትዮጵያ ቡና ሳሙኤል ሳኑሚን በማስፈረሙ የነበረበት የአጥቂ ክፍተት እንደሚደፍነው ሲገመት ደደቢት በበኩሉ ጌታነህ ከበደን ወደ ቡድኑ በመመለሱ ከዳዊት ፈቃዱ(አቡቲ) ጋር በ2005 ላይ ታይቶ የነበረው አስደናቂ ጥምረት በድጋሚ ለመፍጠር ጥረት ያደርጋል፡፡

የሁለቱ ቡድኖች የመጨረሻ ጨዋታ ሚያዚያ 30 ላይ ያደረጉት የአአ ስታድየም ጨዋታ በኢትዮጵያ ቡና ከሙሉ የጨዋታ ብልጫ ጋር 3-0 አሸናፊነት ሲጠናቀቅ የቡድኑ አጥቂ ሳዲቅ ሴቾ ሀትሪክ ሰርቶ እንደነበር ይታወሳል፡፡ኢትዮ ቡናም በ 2008 ካሳያቸው ድንቅ እንቅስቃሴዎቹ ውስጥ ዋናኛው እንደነበር ይታወቃል፡፡

ታህሳስ 11 ላይ አድርገውት ነበረው የ2008 ቱ የመጀመሪያ ጨዋታቸው ላይ ግን አሸናፊ መሆን የቻሉት ደደቢቶች ነበሩ፡፡ሄኖክ እና ሽመክት ጉግሳ ለደደቢት ያቡን ዊልያም ደግሞ ለኢትዮ ቡና የጎል አስቆጣሪዎቹ ነበሩ፡፡

የሁለቱ ቡድኖች የእሁዱ ጨዋታስ በማን አሸናፊነት ይጠናቀቅ ይሆን?

ሌሎች እሁድ የሚደረጉ ጨዋታዎች

አዳማ ከተማ ከ ድሬደዋ ከተማ

ሲዳማ ቡና ከፋሲል ከተማ

ወላይታ ድቻ ከ መከላከያ

ወልዲያ ከተማ ከ ኢት ንግድ ባንክ

ሀዋሳ ከተማ ከ አአ ከተማ

ጅማ አባቡና ከ ኢት ኤሌክትሪክ

የሚያደርጉት ጨዋታ ይሆናል፡፡

 

Advertisements
%d bloggers like this: