Skip to content
Advertisements

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 3ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዳሰሳ

picsart_11-24-10-56-21


ፈይሰል ሀይሌ

ሀሙስ  ህዳር 15 ¦ 2009  ለኢትዮ አዲስ ስፖርት በፈይሰል ሀይሌ የቀረበ

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 3ኛ ሳምንት በሳምንቱ መጨረሻ ቅዳሜ እና እሁድ  በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ቀጥሎ ይካሄዳል፡፡ ኢትዮአዲስ ስፖርትም የሳምንቱን መጨረሻ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ  ጨዋታዎች ከታች እንደሚከተለው በስፋት ተመልክታለች፡፡ የጨዋታዎቹን መርሀ ግብሮች ቦታ እና ሰአትም ተካቷል፡፡

መከላከያ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ 

➡ በሊጉ አስፈሪ ግስጋሴን እያደረጉ የሚገኙት ፈረሰኞቹ የፊታችን  መከላከያን በአዲስ አበባ ስቴዲየም ይገጥማሉ ፡፡ ለአራት ተከታታይ አመታት ሊጉን ለማሸነፍ እየታተሩ የሚገኙት የአምናው የሊጉ ዋንጫ አሸናፊዎቹ ቅዱስ ጊዮርጊሶች ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ደደቢትን 2-0 በመርታት በግብ ክፍያ ሊጉን በብቸኝነት መምራት  ጅመረዋል፡፡ ሳላዲን ሰይድ ፣ አስቻለው ታመነ ፣ ዘካሪያስ ቱጂ እና ራምኬል ሎክ በጉዳት ምክንያት ባሳለፍነው ሳምንት ማሰለፍ ያልቻሉት ፈረሰኞቹ በቀጣዩ የሊግ ጨዋታ ላይ ሳላዲን ሰይድ ከጉዳቱ አግገሞ ይመለስላቸዋል ተብሏል፡፡ በ2 የሊግ ጨዋታዎች 3 ነጥብ መሰብሰብ ያቃታቸው መከላካያዎች በዚህ የሊግ ጨዋታ የፈረሰኞቹ ፈተና እንደሚሆኑ የሚጠበቅ ሲሆን አንድ ጨዋታ በቅጣት ያመለጠው አወል አብደላም በዚህ ጨዋታ ይሰለፋል፡፡

picsart_11-24-11-05-01

ኢትዮጵያ ቡና ከ ፋሲል ከነማ

➡ ቡናማዎቹ በውድድር አመቱ መልካም ጅማሮን አላደረጉም በሊጉ ካደረጉት 2 ጨዋታዎች ማግኘት ከነበረባቸው 6 ነጥቦች ማሳካት የቻሉት 1ዱን ብቻ ነው፡፡ በደደቢት 3-0 ተረትተው ከመከላኪያ 2-2 አቻ የተለያዩት ኢትዮጵያ ቡናዎች በሊጉ 3ኛ ሳምንት የሊጉን አዲስ መጪ ፋሲል ከነማን ይገጥማሉ፡፡ በቅጣት ምክንያት የሊጉ 2ኛ ሳምንት ጨዋታ ያመለጠው ቤኒናዊው ግብ ጠባቂ ሀሪሰን ሆሱ በዚህ ጨዋታ ቅጣቱን ጨርሶ የሚገባ ይሆናል፡፡ አጼዎቹ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን በአዲስ አበባ ስቴዲየም ለማድረግ ተሰናድተዋል፡፡ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ በፋሲል ስቴዲየም ከወላይታ ድቻ ጋር ጨዋታቸውን ለማድረግ ቀነ ቀጠሮ ይዘው የነበሩት ፋሲሎች ከጸጥታ ጋር ተያይዞ የጨዋታው ቀን መራዘሙን ተከትሎ የሊጉን 2ኛ ሳምንት ጨዋታ አላደረጉም፡፡ ላልተወሰነ ወቅትም በሜዳቸው ፋሲል ስቴዲየም የሚያደርጓቸወው የሊጉ ጨዋታዎች የሚያል     ፏቸው ይሆናል፡፡ ሁለቱ ተጋጣሚዎች በደቡብ ሲቲካፕ ላይ ተገናኝተው ኢትዮጵያ ቡና 4-1 ማሸነፊ ይታወሳል፡፡

ኢትዮኤሌክትሪክ ከ አዲስ አበባ ከነማ  

➡ የአዲስ አበባ ሲቲ ካፕ አሸናፊዎቹ ኢትዮአሌክትሪኮች ከ2 የሜዳ ውጪ ጨዋታዎች በዋላ በሜዳቸው የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ለማድረግ ተሰናድተዋል፡፡ ወደ ጅማ አቅንተው ከጅማ አባ ቡና 0-0 እንዲሁም ወደ ድሬ ተጉዘው በድሬዳዋ ከተማ 2-1 የተረቱት  በብርሀኑ ባዩ የሚመሩት አሌክትሪኮች  በ2 ጨዋታዎች 4 ነጥቦችን መሰብሰብ የቻለውን አዲስ አበባ ከነማን ይገጥማሉ፡፡ ከአምናው በተሻለ በዘንድሮው የውድድር ዘመን ጥሩ የሚባል መነቃቃት ላይ የሚገኙት አሌክትሪኮች የሲቲ ካፑን ዋንጫ ከፍ ማድረጋቸውን ተከትሎ በበርካቶች ዘንድ በያዝነው አመት በሊጉ የተሻለ እንደሚጓዙ ተገምቶላቸዋል፡፡ በሊጉ 1ኛ ሳምንት ወደ አዋሳ አቅንተው አዋሳ ከነማን 2-0 በማሸነፍ 3 ነጥቦችን ከደቡብ ይዘው የተመለሱት አዲስ አበባ ከነማዎች 2ኛ ጨዋታቸውን ከጅማ አባቡና 0-0 በሆነ ውጤት ያጠናቀቁ ሲሆን በሊጉ ባለፉት 2 ጨዋታዎች  ሽንፈትን ካላስተናገዱ በጣት የሚቆጠሩ ክለቦች መሀል ይገኙበታል፡፡

ሲዳማ ቡና ከ ድሬዳዋ ከነማ 

➡  ሲዳማ ቡናዎች ፋሲል ከነማን በሊጉ ጅማሮ ቢረቱም ወደ አዳማ አቅንተው ግን ሽንፈትን አስተናግደው ተመልሰዋል፡፡ በሊጉ 3ኛ ሳምንት በይርጋለም ድሬዳዋ ከነማን ይገጥማሉ፡፡ ዘላለም ሽፈራው ሞሪንሆ በሊጉ ራሱን በሚገባ ወዳሳየበት ቤት በሊጉ 3ኛ ሳምንት ይመለሳል፡፡ የቀድሞ የሲዳማ ቡና አሰልጣኝ በሊጉ ጅማሮ ወደ አዳማ አቅንቶ ሽንፈት ቢያስተናግድም በድሬዳዋ ስቴዲየም ኤሌክትሪክን በገጠመበት ጨዋታ ግን ድል ማድረግ ችሏል፡፡ ባሳለፍነው አመት 2ቱ ክለቦች በሊጉ 2ኛ ዙር ባደረጉት ጨዋታ ላይ 0-0 በሆነ ውጤት መለያየታቸው ይታወሳል፡፡

picsart_10-19-10-57-33

ወላይታ ዲቻ ከ አዳማ ከነማ 

➡ ከፋሲል ከነማ ጋር ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ የተራዘመባቸው ወላይታ ዲቻዎች በሊጉ ሶስተኛ ሳምንት በሜዳቸው  ሶዶ አዳማ ከነማን ይገጥማሉ፡፡ በሶደ በሊጉ መጀመሪያ መከላኪያን በመርታት 3 ነጥብ መሰብሰብ የቻሉት ወላይታ ድቻዎች  በውድድር አመቱ የተሻለ ለመጓዝ ተስፋን ሰንቀዋል፡፡ ከሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮጊርጊስ በግብ ከፍያ አንሰው 2ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡት አዳማ ከነማዎች አሁንም በሊጉ ተፎካካሪነታቸው ለመቀጠል እና ቀጣይ ሳምንት ከመሪው ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር በአዳማ ከተማ ላለባቸው ጨዋታ ስንቅ ይሆናቸው ዘንድ ወላይታ ድቻን ለመርታት መቁረጣቸው ተሰምቷል፡፡

ወልዲያ ከነማ ከ ደደቢት   

➡ አዲስ መጪዎቹ ወልዲያ ከነማዎች ወርሀ ጥር እስኪመጣ በአዲሱ ስቴዲየማቸው የሊግ ጨዋታዎችን አያደርጉም፡፡ በዚህም ምክንያት መልከ ቆና ላይ አሁንም የሊግ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡ በ2007 በሊጉ የፈጸሙትን ስህተት ላለመድገም ከወዲሁ መታታር የጀመሩት የአማራ ክልል ተወካዮቹ 4 ነጥቦችን ሰብብሰበው ከመሪዎቹ ጆሮ ስር እየተነፈሱ ይገኛሉ፡፡ የፊታችን እሁድ በ9 ሰአትም ደደቢትን ይገጥማሉ፡፡ ኢትዮጵያ ቡናን 3-0 ባሸነፉ በሳምንቱ በፈረሰኞቹ 2-0 የተረቱት ሰማያዊዎቹ የሊጉ ተፊካካሪነታውን ለማስቀጠል የግድ ከዚህ ጨዋታ 3 ነጥቦችን ይዘው መመለስ የግድ ይላቸዋል፡፡ በ9 ቁጥሩ ጌታነህ ከበደ ላይም ተስፋን ሰንቀዋል፡፡

ጅማ አባቡና  ከ ንግድ ባንክ   

➡ በቡናዋ ታዋቂ የሆነቸው ጅማ እሁድ ከሰአት 2ኛ የሊግ ጨዋታውን በሜዳው ጅማ ስቴዲየም በሚያደርገው ጅማ አባቡና ከንግድ ባንክ በሚያደርገው የሊግ ጨዋታ ትደምቃለች፡፡ የአምናው የሱፐር ሊግ ክስተት ጅማ አባቡና በሊጉ ጅማሮ ነገሮች አልጋ በአልጋ ባይሆኑለትም እስካሁን ባደረጋቸው 2 የሊጉ ጨዋታዎች ሽንፈትን አልቀመሰም፡፡ መረቡን ሳያስደፍር ያደረጋቸውን 2 ጨዋታዎች በተመሳሳይ 0-0 በሆነ ውጤት አጠናቋል፡፡ የእሁድ ከሰአት ተጋጣሚው ንግድ ባንክ በሊጉ የመጀመሪያ ሳምንት ወደ ወልዲያ አቅንቶ 1-0 ሽንፈትን ያስተናገደ ሲሆን በሊጉ 2ኛ ሳምንት ጨዋታውን ከአዋሳ ከነማ ጋር ለማድረግ ቀነ ቀጠሮ ይዞ የነበረ ሲሆን  በአዋሳ ከነማው ግብ ጠባቂ ክብረአብ ዳዊት ህልፈት ምክንያት ጨዋታው ላልተወሰነ ጊዜ መተላለፉ ይታወሳል፡፡

  ሀዋሳ ከነማ  ከ አርባምንጭ    

➡ መጥፊ ሊባል ከሚችል ሳምንት በዋላ ሀዋሳ ወደ እግር ኳስ እንቅስቃሴዋ ተመልሳለች፡፡ በአሰቃቂው አደጋ ምክንያት ከባለቤቱ እና ከ2 ሴት ህጻናት ልጆቹ ጋር በእሳት ቃጠሎ ህይወቱን ያጣው ክብረአብ ዳዊት በሀዋሳ ይዘከርበታል ተብሎ በሚጠበቀው የሀዋሳ ከነማ እና የአርባ ምንጭ ከነማ ጨዋታ የፊታችን እሁድ በ9 ሰአት በአዋሳው አርቴፊሻል ሳር ለበስ ስቴዲየም ይካሄዳል፡፡ በሊጉ ጅማሮ በአዲስ አበባ ከነማ 2-0 ተረትተው 2ኛ የሊግ ጨዋታቸውን በሀዘን ምክንያት ያስተላለፉት ሀዋሳ ከነማዎች ለዚህ ጨዋታ ትልቅ ትርጉም ሰጥተው እንደሚገቡ ከወደ ደቡብ ዋና ከተማ እየተሰማ ይገኛል፡፡ አርባምንጭ ከነማዎች በሊጉ ማግኘት ከነበረባቸው 6 ነጥብ ማግኘት የቻሉት  ብቻ ሲሆን በሊጉም 3 ተቆጥሮባቸው ምንም ግብ ተጋጣሚያቸው ላይ ማሳረፍ አልቻሉም፡፡

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 3ኛ ሳምንት መርሀ ግብር

ቅዳሜ ህዳር 16

➡  ኢትዮጵያ ቡና 11፡30 ፋሲል ከነማ  (አዲስ አበባ ስቴዲየም)

እሁድ ህዳር 17

➡ ኢትዮ ኤሌክትሪክ 9፡00 አ.አ ከነማ (አዲስ አበባ ስቴዲየም)

➡ ቅ.ጊዮርጊስ 11፡30 መከላኪያ  (አዲስ አበባ ስቴዲየም)

➡ ጅማ አባቡና 9፡00 ኢ.ንግድ ባንክ  (ጅማ ስቴዲየም)

➡ ሲዳማ ቡና 9፡00 ድሬዳዋ ከነማ  (ይርጋለም ስቴዲየም)

➡ ወልዲያ ከነማ 9፡00 ደደቢት     (ወልዲያ ስቴዲየም)

➡ ሀዋሳ ከነማ 9፡00 አርባምንጭ   (ሀዋሳ ስቴዲየም)

➡ ወላይታ ድቻ 9፡00 አዳማ ከተማ  (ሶዶ ስቴዲየም)

Advertisements

መንሀጁል ሀያቲ View All

የኢትዮአዲስ ስፖርት የስፖርት ዜናዎች ፀሀፊ

%d bloggers like this: