በምህረት ተስፋዬ

አሰልጣኝ አርሰን ቬንገር ዛሬ ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ቆይታ በጉልበት ጉዳት ለ7ወራት ከሜዳ ርቆ የቆየው ዳኒ ዌልቤክ ከአንድ ሳምንት ቡሀላ ከዋና ቡድኑ ጋር ልምምድ እንደሚጀምር ገልፀዋል።

image

ተጨዋቹ ልምምድ እንደሚጀመር ነገር ግን ከረጅም ጊዜ ቡሀላ በመሆኑ በተሟላ የአካል ብቃት ላይ ለመገኘት ጊዜ ያስፈልገዋል ሲሉ አሰልጣኙ አክለው ገልፀዋል። ገለፃቸው ተጨዋቹን በቶሎ ወደ መጀመሪያ አሰላለፍ እንደማያስገቡት ፍንጭ የሰጠ ነው። ያም ተጫዋቹ ቀስ በቀስ ወደ ትክክለኛ አቋሙ እንዲመጣ እና ለሌላ ጉዳት  እንዳይዳረግ የሚወሰድ እርምጃ ነው። የዚህ አይነት እርምጃዎች በዘመናዊ እግርኳስ እየተለመደ የመጣ ተግባር ነው።
ከዚ ቀደም በጉልበት ጉዳት ለ10 ወራቶች ከሜዳ እርቆ የነበረ ሲሆን ወደ ሜዳ  ከተመለሰ ከ3 ወር ቡሃላ May 2016 በሌላኛው እግሩ ባጋጠመው የጉልበት ጉዳት ለ7 ወራት ከሜዳ እርቆ ቆይቷል ። በዛም ፈረንሳይ አዘጋጅታ በነበረው የአውሮፓ ዋንጫ ሀገሩ እንግሊዝን ሳይወክል ቀርቷል።
ዳኒ ዌልቤክ 2014 ከማንችስተር ዪናይትድ አርሰናልን በተቀላቀለበት የውድድር  አመት 34 ጨዋታዎችን ማድረግ ችሏል።  በ2015/16 የውድድር አመት በአጠቃላይ ሁሉንም ውድድሮች ጨምሮ  መጫወት የቻለው 15 ጨዋታዎችን ብቻ ነበር። ምንም እንኩዋን ተጫዋቹ 72 ጨዋታዎች በጉዳት ቢያመልጡትም ከጉዳት ነፃ ሆኖ በተሰለፈባቸው ጨዋታዎች ወሳኝ ጎሎችን ለክለቡ ማስቆጠር ችሏል።

image

የተጫዋቹ በወሳኝ ግዜ ከጉዳት መመለስ ለክለቡ መልካም አጋጣሚ ሲሆን ክለቡም ዋንጫውን ለማንሳት በሚያደርገው ፉክክር ተጫዋቹ የላቀ አስተዋጽኦ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

Advertisements