Skip to content
Advertisements

የእለተ ቅዳሜ አመሻሽ የአውሮፓ ጋዜጦች የዝውውር እንዲሁም ሌሎች አስደንጋጭና አዝናኝ ወሬዎች

ታህሳስ 08, 2009| በሚኪያስ በ. ወርዶፋ

የፓሪስ ሴንጀርሜኑ ጣሊያናዊ የ 24 ዓመት አጥቂ ማርኮ ቫራቲ በመጪው ጥር የቼልሲ ቀዳሚ የዝውውር ኢላማ ነው፡፡ (ዴይሊ ሜይል)

የ 27 ዓመቱ የአርሰናል አጥቂ አሌክሲ ሳንቼዝ በክለቡ ደስተኛ እንደሆነና ስምምነቱን የማራዘሙ ጉዳይ ግን በክለቡ ፍላጎት ላይ የተወሰነ እንደሆነ “በእርግጥ ጉዳዩ በኔ ላይ የተመሰረተ አይደለም ነገር ግን ክለቡ በእኔ ላይ ባለው መተማመን የሚወሰን ነው፡፡” ሲል በሰጠው አስተያየት ገልጿል፡፡ (ስካይ ስፖርት)

ፔፔ ጋርዲዮላ(ከስር በምስሉ ላይ የሚታየው) በመጪው ጥር ምንም አይነት ተጫዋች የማያስፈርሙ ይሆናል፡፡ (ዴይሊ ሚረር)


በሌላ በኩል ሲቲዎች የተከላካይ ችግራቸው በዚህ ከቀጠለ የሳውዛምፕተኑን የመሀል ተከላካይ ቨርጂል ቫን ዲጂክን ማስፈረምን ሊያስቡ ይችላሉ፡፡ (ዴይሊ ቴሌግራፍ)

ነገር ግን ይህ ደቻዊ ተከላካይ ሲቲዎችን 50 ሚሊዮን ፓውንድ ሊያስወጣቸው ይችላል፡፡(ኢቭኒንግ ታይምስ)

ቼልሲዎች በ 60 ሚሊዮን ፓውንድ ወደ ቻይናው ስአይፒጂ ክለብ ሊያመራ የሆነውን አማካኙን ኦስካርን(ከስር ምስሉ የሚታየውን) ለመተካት በማሰብ የ 22 ዓመቱን የሞናኮ አማካኝ ቲሞው ባካያዮኮን ለማምጣት አቅደዋል፡፡(ታይምስ)

ዊስትሀሞች የ 23 ዓመቱን የቼልሲ አጥቂ ሚች ባትሱሀይን በውሰት ለመውሰድ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ (ዘ ሰን)

የሰንደርላንዱ አሠልጣኝ ዴቪድ ሞይስ የሰንደርላንድን ትክክለኛ የገንዘብ አቅም ከመጀመሪያው ቢያውቁ ኖሮ የአሰልጣኝነት ስራውን ጥያቄ ውድቅ ያደርጉ አንደነበር ተናገሩ፡፡ (ዴይሊ ሜይል)

ቶኒ ፑሊስ የ 23 አመቱ አጥቂያቸው ሰይዶ ብራሂኖ በዌስትብሮም እንዲቆይ ፈልገዋል ነገር ግን በመጪው ጥር ከባድ የዝውውር ንትርክ እንደሚያጋጥማቸው ከወዲሁ ተገንዝበዋል፡፡ (ኤክስፕረስና ስታር)

ቶትነሀም የ 23 ዓመቱ የኤቨርተን አማካኝ ላይ አይኑን ቢጥልም የኤቨርተኑ አሠልጣኝ ሮናልድ ኩመን ግን የሮስ ባርክሌይ የስምምነት ማራዘሚያ ጉዳይ የክለቡ ቀዳሚ አጀንዳ አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡ (ኢቪኒንግ ስታንዳርድ)

የማንችስተሩ የ 22 ዓመት የክንፍ ተጫዋች ሜምፈስ ዲፔይ ሌላኛውን የክለቡን አጋር ሞርጋን ሽንደርሊን አስከትሎ ኤቨርተንን ሊቀላቀል ከጫፍ ደርሷል፡፡ (ማንችስተር ኢቪኒንግ ኒውስ)

ነገር ግን እንደ ሞሪንሆ ገለፃ ከሆነ ዩናይትድ በመጪው ጥር ምንም አይነት ተጫዋች አይገዛም፡፡ (ፎር ፎር ቱ)

ሞሪንሆ(ከስር በምስሉ ላይ የሚታየው) ስዊድናዊውን የቤኔፊካ ተከላካይ ቪክቶር ሊንድሎፍን የዝውውር ተቀዳሚ ኢላማቸው ቢያደርጉም እሱን ለማስፈረም እስከ መጪው ክረምት መጠበቅ ይኖርባቸዋል፡፡ (ዴይሊ ሚረር)

የሲቲው አሠልጣኝ ጋርዲዮላ የቡድኑ በረኛው ክላውዲዮ ብራቮ ወደ ባርሲሎና ይመለሳል ተብሎ ቢወራም እሱ ግን በክለቡ እንደሚቆይ ተናግሯል፡፡ (ኢንዲፔንደንት)

ጋርዲዮላ ብራቮን በእንግሊዝ ተረጋግቶ እንዲቆይ ለመርዳትና በቅርበት ለማነጋገር አብሮት ቁርስ በልቷል፡፡ (ዴይሊ ሚረር)

የዩናይትዱ አጥቂ አንቶኒዮ ማርሻል በሞውሪንሆ ስር በተቀያሪ ወንበር ላይ መቀመጡ እንዳናደደው ተናግሯል፡፡ (ኤስኤፍአር ስፖርት ጋርዲያንን ጠቅሶ እንደፃፈው)

ለቀድሞው የአርሰናል አጥቂ ጀርቪንሆ በእያንዳንዱ ጨዋታ ላይ 83,000 ፓውንድ የሚከፍለው የቻይናው ሀብታም ክለብ ሄቢ ፎርቹን ለአለም ኮከብ ተጫዋቹ ሜሲ(ከስር በምስሉ ላይ የሚታየው) በአመት የ100 ሚሊዮን ዮሮ ወይም የ83.7 ሚሊዮን ፓውንድ አመታዊ ደሞዝ የሚያስገኝ አዲስ የዝውውር ጥያቄ ይዞ ብቅ ብሏል፡፡ (ስፖርት ስካይ ስፖርትን ጠቅሶ እንደፃፈው)

ኮሎምቢያዊው የማድሪድ አጥቂ ጀምስ ሮድሪጌዝ ብዙ ነገር ቢወራበትም በነጮቹ ቤት ደስተኛ መሆኑን ተናግሯል። (አስ)

የስቶክ ሲቲው ማርክ ሂውዝ ተጫዋቾቻቸውን በገና በአል እለት ለልምምድ እንዲገኙ ያዘዙ ሲሆን ለቡድኑ የውጪ ሀገር ተጫዋቾች ግን እረፍት መስጠታቸውን ፀጉራቸውን እያሻሹ ተናግረዋል። (ስቶክ ሴንቲኔል)

የ31 ዓመቱ የዩናይትድ አጥቂ ዋይኒ ሩኒ ባለፈው ክረምት ለናፓሊ ክለብ ለሽያጭ ቀርቦ እንደነበር አንድ ጣሊያናዊ ወኪል ተናገረ። (ራዲዮ ሲአርሲ ጎልን ጠቅሶ እንዳወራው)

ከእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን አሠልጣኝነት የተሰናበቱት ሳም አላርዳይስ(ከላይ በምስሉ ላይ የሚታዩት) በመጪው ጥር ወደ አሠልጣኝነት መመለስ ፈልገዋል። (ቢን ስፓርትስ)

በማህበራዊ ሚዲያ ትኩረት ወዳገኙ ጉዳዮች ስናልፍ …..

የሲቲው አጥቂ ሰርጂዮ አጉዌሮ በትዊተር ባስተላለፈው መልዕክት የቡድን አጋሩ ጉንዶጋን በጉልበቱ ላይ በተፈጠረ ጉዳት ቀዶ ጥገና ሊያረግ በመሆኑ የተዘማውን ሀዘኔታ ገልጿል።

አንድሬያ ፔርሎ በኢንስታግራም ገፁ ፓብሎ ከሚሰኘው ውሻው ጋር ለጠዋት እግር ጉዞ(foggy walk) ሲወጣ የሚያሳይ ምስል ለጥፏል።

በትዊተር ይፋ በተደረገ ፎቶ ደግሞ የዩናይትዶቹ ባስቲያን ሸዋንስታይገር፣ ዋይኒ ሩኒና ኢብራሂሞቪች ሲቀላለዱና ሲስቁ የሚያሳይ ፎቶ ይፋ ተደርጓል።

ከደቂቃዎች በኃላም የቡድን አጋሮቹን ፎቶ የተመለከተውና ጉዳዩ ያጓጓው ሌላኛው የዩናይትድ ተጫዋች(ከስር በምስሉ የሚታየው) ሁዋን ማታ “እንደማስበው ቀልዱ አልገባኝም(i think i didn’t get the joke)” የሚል ፅሁፍ በትዊተር ገፁ አስነብቧል።

በመጨረሻም ….

የቀድሞው የቼልሲ አጥቂ ፍሎረንት ማሉዳ በሚገኝበት ዴሊሂ ዳይናሞስ በታሪክ አስደናቂ የሆነ የፍፁም ቅጣት ምት ስህተት ሰርቷል። (ጆኤ)

Advertisements

ሚኪያስ በቀለ View All

ይህን ዘገባ ያቀረብኩላችሁ የኢትዮአዲስ ስፓርት ኤዲተርና ፀሀፊ እኔ ሚኪያስ በቀለ ነኝ።

%d bloggers like this: