Skip to content
Advertisements

ሳዲዮ ማኔ፣ የቀያዮቸን ነፍስ ዳግም የዘራው ሴኔጋላዊ ኮከብ [ልዩ ዘገባ]

  • SMS
  • W
  • ሳዲዮ ማኔ ባለፈው ክረምት ውዱ አፍሪካዊ ተጫዋች ሆኗል
  • ሊቨርፑል ከሳውዛምፕተን ለማስኮብለል 34 ሚ.ፓውንድ ወጪ አድርጎበታል
  • እድገቱ በሴኔጋል የሆነው የ24 ዓመቱ ተጫዋች በአንፊልድ ጥሩ ጊዜን እያሳለፈ ይገኛል
  • ግርማ ሞገስ ባላቸው የርገን ክሎፕ ስልጠናም ደስተኛ ነው

​ሳዲዮ ማኔ ወንበሩ ላይ ወደኋላ ተደገፈና ሳቀ። ማኔ ኮስታራ ሰው ቢሆንም አሁን ግን እንደዚያ አይደልም። ምክኒያቱም ለመሳቅ የሚያስገድደው  ነገር ገጥሞታል።

ማኔ ኃይማኖተኛ ከሆኑት ሴኔጋላዊያን ቤተሰቦች የተገኘ እንደሆነ ሲገልፅ በልጅነት ጊዜው ቤተሰቦቹ ምን ያህል ወደቤተክርስቲያን እንደሚሄዱ መጠየቁ ነበር የሳቁ ምንጭ። “ሙስሊሞች ናቸው። ብዙም ወደቤተክርስቲያን አይሄዱም።” አለና ሳቁን ቀጠለ።

ማኔ በሊቨርፑሉ የልምምድ ሜዳ ሜልዉድ ዝነኛ የሆነ ተጫዋች ነው። በብዙዎቹ ጓደኞቹ ዘንድ ትሁትና ራሱን ዝቅ ያደረገ ሰው በመሆኑም ይታወቃል። አንዳንድ የፕሪሚየር ሊግ ተጫዋቾች ራሳቸውን እንደዝነኛ ሰው ሲያስቡ ማኔ ግን ከዚያ ተቀራኒ የሆነ ባህሪ ነው ያለው።

ብዙዎች የማኔ ግዢ የየርገን ክሎፕ የሊቨርፑል አስተዳደር ልማድ አድርገው ነበር የቆጠሩት። ምክኒያቱም ክሎፕ እንደሰር አሌክስ ፈርጉሰን ሁሉ ተጫዋቾችን የሚገዙት ተጫዋቾቹ ባሏቸው ስብእናና በእግርኳስ ክህሎታቸው ጭምር ነው። ማኔ ደግሞ እንደዘያ ዓይነት ተጫዋች ነው።

የሳዲዮ ማኔ እድገት አባቱ የአንድ መስጊድ ኢማም በነበሩበት ደቡባዊ ሴኔጋል በምትገኝ ባምባሊ በተሰኘች መንደር ነው። ባለፈው ወር አንድ ጋዜጠኛ ወደዚያች መንደር አምርቶ ያችን አባቱ የሚያገለግሉባትን መስጊድን መልሶ ለመገንባት ክፍያ እንደፈፀመ ተነግሮታል። 

ጋዜጠኛው በዘገባው ጭምሮ እንዳመለከተ ከሆነም ማኔ እንደትላልቅ የአፍሪካ ዝነኛ ተጫዋቾች ሁሉ መንደሯ በምትገኝበት ክልል ላይ የአከባቢው ነዋሪ ለመርዳት ገንዘቡን ፈሰስ የማድረግ ዕቅድ አለው።

Sadio Mane sat down with Sportsmail's Oliver Holt ahead of Liverpool's clash with Everton

ሳዲዮ ማኔ ከስፖርትስሜሉ ጋዜጠኛ ኦሊቨር ሆልት ጋር ተቀምጦ ሰፊ የሆነ ጭውውት አድርጓል

The 24-year-old became the world's most expensive African footballer in the summer

የ24 ዓመቱ የፊት ተጫዋች በክረምቱ ውድ ክፍያ የተከፈለበት የምንጊዜውም አፍሪካዊ ተጫዋች ተሰኝቷል

Mane has hit the ground running at Anfield by scoring seven goals in 17 games for Liverpool

ማኔ በሊቨርፑል በ17 ጨዋታ ሰባት ግቦችን ለማስቆጠር በቶሎ ዝነኛ ሆኗል

ኃላፊነት ከማይሰማቸው ጥቂት የፕሪሚየር ሊጉ ተጫዋቾችም በእጅጉ የተቃረነ ባህሪ ያለው ተጫዋች ነው። “ፈፅሞ አልኮል በእጄ አልነካም።” ይላል ማኔ ሜልዉድ ከሚገኝ አንድ ትንሽ ቢሮ ውስጥ ቁጭ ብሎ ከዘሜል ስፖርቱ ጋዘጠኛ ጋር እየተጨዋወተ። “ለእኔ ኃይማኖት ወሳኝ ነገር ነው። የእስልምናን ህግጋቶች አከብራለሁ። ሁልጊዜም በቀን ለአምስት ጊዜያት ያህል ፀሎት አደርሳለሁ።”

“በሴኔጋል 90 በመቶው ህዝብ ሙስሊም ነው። ምናምልባትም ክርስቲያኑ 10 ፐርሰንቱ ሊሆን ይችላል። ሁሉም ህዝብ በህብረት ጎረቤት ለጎረቤት ሆኖ በወዳጅነት ይኖራል። የእኔ የቅርብ ጓደኞ የሆነው ሉኬ ክርስቲያን ነው። እኔ ወደእሱ ቤት እሄዳለሁ እሱም ከእኔ ቤት አይጠፋም።

“በኃይማኖት ግጭት አልነበረም። እኔም እግር ኳስ መጫወት እወድ ነበር። እድገቴም በትክክለኛው መስመርና መንገድ ነበር። ቤተሰቦቼም ፕሮፌሽናል እግርኳስ ተጫዋችን በመሆኔ እውነታ ላይ በጣም ኩራት ይሰማቸዋል።አሁንም ድረስ ኑሯቸው በዚያው መንደር ነው። ነገር ግን እኔ በዳካር ቤት ስላለኝ ሲያሻቸው ወደዚያ በመሄድ ይቆያሉ። ቤቴ ለእነሱ ሁሌም ክፍት ነው።

“ወጣት ከነበርኩበት ጊዜ አንስቶ በህይወቴ ላይ ግፊት ያደርስብኝ የነበርው ነገር በተለየ መልኩ ለመንደሬ በምላሹ ላበረክተው የምፈልገው ነገር መኖሩ ነው። በዚህም ላይ በሴኔጋል ከሚገኙ ወዳጆቼ ጋር እየተማከርኩ ነው። እኔ አሁን ወጣት ነኝ። ነገር ግን በቅርብ ጊዜ እንድ ነገር ይፈጠራል።” ሲል ተናግሯል።

ማኔ አሁን ያለበት ደረጃ ለመድረስ የገጠመው መንገድ  ቀላል አልነበረም። የሃገሪቷ ካርታ እንደሚያሳየው ካደገበት መንደር ባምባሊ ወደተቀረው የሴኔጋል ከተሞች ለማምራትና አትላንቲክን አንደመውጫ በር ለመጠቀም አቋራጩ መንገድ የጎረቤት ሀገሯ ጋምቢያ ነበርች። 

ማኔ በፈረንሳይ በአንድ ትልቅ ክለብ ውስጥ የመጫወት ህልም እንዳለው ለአጎቱ በነገረው ጊዜ ስቆበታል። 

“አላመምኩትም።” ይላል የማኔ አጎት ባለፈው ወር 34 ሚ.ፓውንድ በሆነ ዋጋ ለሊቨርፑል በፈረመበት ጊዜ የምንጊዜውም የአፍሪካ ውድ የዝውውር ዋጋ ስለወጣበት ተጫዋች መሰረት ስለሆነችው ባምባሊ ለመዘገብ ለሄደው ጋዜጠኛ ሲናገር። “ነገር ግን እሱ እምነት ነበረው። በሃገሪቱ የፀደይ ወቅት ውድድሮች ላይ እንኳ ይህንን ነገር ደጋግሞ ይለኝ ነበር።” ሲል ተናግሯል።

ከሃገሪቱ ዋና ዋና ተቀናቃኝ ቡድኖች ከሆኑት ቲንቲንኮንግና ማራሱም ጋር በመንደሩ ቡድን ውስጥ በኮከብ ተጫዋችነት ከመጫወቱ በፊት እንኳ ይህን ይል ነበር። ሁልጊዜም ተነሳሽ፣  እምነት የለውና ዝነኛ የመሆን ከፍተኛ ፍላጎት ነበረው።

“የሚያስደስተው ነገር እግር ኳስ ብቻ እነደሆነ ይናገር ነበር።” ሲል አንድ ጓደኛው ለሃገሪቱ ጋዜጠኛ ተናገሯል።

Mane (right) will come up against his former Southampton boss Ronald Koeman on Monday

ማኔ ሰኞ ምሽት የቀድሞን የሳውዛምፕተን አሰልጣኙን ሮናልድ ኮማንን በተቃራኒ ይግጥማል

He holds the record for scoring the fastest Premier League hat-trick - the impressive feat came against Aston Villa while he was playing for former side Southampton in May 2015 (pictured)

የፕሪሚየር ሊጉ ፈጣኑ ሃትሪክ ክብረወሰን የተመዘገበው በእሱ ነው (ሳውዛምፕተን ሳለ በአስቶንቪላ ላይ ያስቆጠራቸው) 

ማኔ ከኮማን ይልቅ  የክሎፕ አሰላለፍ ተመችቶታል

• ሊቨርፑል ከኤቨርተን ጋር ባደረጋቸው የመጨረሻዎቹ 11 የፕሪሚየር ሊጉ ደርቢ ጨዋታዎች ሽንፈት አልገጠመውም (ድል4 አቻ 7)

• በሁለቱ ክለቦች መካከል በሊግ ውድድሮች ላይ ከ1979 እስከ 1984 ድረስ በተደረጉ 11 ጨዋታዎች ላይ ባለመሸናነፍ የሊጉ ቀዳሚ ናቸው።

•  ኤቨርተን ካለፉት የመጨረሻዎቹ 19 የደረቢ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው በአንዱ ብቻ ነው።

የ24 ዓመቱ ማኔ ከባምባሊ አባሯማ ሜዳዎች እስከፕሪሚየር ሊጉ ከቲድራሎች ለመድረስ ህልሙን ለማሳካት ያደረገውን ጉዞ ቀላል እንዳልነበሩ ይናገራል።

“አሁን ጥሩ ነገር ማድረግ እፈልጋለሁ።” ይላል ማኔ። “አሁንም ድረስ መሻሻል እፈልጋለሁ። አሁንም ድረስ ህልሜ ላይ የደረስኩ አይመስለኝም። ጠንክሬ መስራትና የምፈልገው ቦታ ለመድረስ መጣር ይኖርብኛል።” 

ማኔ በሊቨርፑል የሚደንቅ ጅማሮ ማሳየት የቻለ ሲሆን ክለቡ በውድድር ዘመኑ ለዋንጫ ተፎካካሪ ለመሆን ከፊት ስፍራ አጣሚሮዎቹ ፊሊፔ ኮቲንሆና ሮቤርቶ ፈርሚኖ ጋር አስፈሪ የአጥቂ ጥምረት ፈጥሯል።

ሰኞ ምሽት ለማኔ የመጀመሪያው በሚሆነው የመርሲሳይድ ደርቢ ኤቨርተንን በጊዲሰን ፓርክ ይገጥማሉ። እናም ማኔ እዚህ ከመድረሱ በፊት አዕምሮው ለደርቢ ጨዋታ ከዚህ ቀደም ወደአሳለፈባቸው ሶስት የአውሮፓ ሃገራት ይዘውት ይነጉዳሉ። 

በሳልዝበርግ የከተማ ደርቢና በሜትዝ ያለ ትልቅ ጨዋታ እንዲሁም በሳውዛምፕተን። ነገር ግን ከሁሉ በላይ የማይዘነጋ ትውስታ ያለው በሃገሩ ሴኔጋል ዋና ከተማ ዳከር የሚደረገው ጨዋታ ነው። ይህንንም ሲያስብ በፈገታ ይሞላል።

የወጣቶች ማሰልጠኛ ገና የ16 ዓመት ወጣት ሰልጣኝ ሳለ በዴምባ ዲዮፕ ስታዲየም ትልቅ የፍፃሜ ጨዋታ ይካሄድ ነበር። ጨዋታውም በሁለቱ የዳከር ትልልቅ ክለቦች ጃራፍ እና ናያሪ ታሊ መካከል የሚደረግ ነበር። እንደዚህ ያለ መጥፎ የጦርነት ባህሪ ያለው ጨዋታ ላይ ተጫውቼ አላውቅም።” ይላል ማኔ ስለጨዋታው ኃይለኝነት ሲናገር “ነገር ግን ይህኛው በእጅጉ አስፈሪ ጨዋታ ነበር። የሁለቱም ደጋፊ ያልንበርኩ ቢሆንም አጋጣሚው ግን ትልቅ ነበር።” ብሏል።

ማኔ  ከጋዜጠኛው ጋር ባደረግው ቃለመጠይቅ  ጥሩ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ችሎታ ቢኖረውም የልቡ አልደርስ ሲለው  ግን  ፈረንሳይኛን ይቀላቀል ነበር። 

ማኔ አስከሚያስታወሠው ጊዜ ድረስ እብድ ያለ የእግርኳስ ወዳጅ ነው። የ15 ዓመት ታዲ ሲሆን ወደአንዳድን ፕሮፌሽናል ቡድኖች በማምራት ሙከራ ለማደርግ ቤተሰቦቹን ተማፅኗል።

The Senegal international has built up a fine partnership with Roberto Firmino (right)

ሴኔጋላዊው ተጫዋች ከሮቤርቶ ፈርሚኖና ፊሊፔ ኮቲንሆ ጋር ጥሩ የፊት ለፊት ጥምረት መፍጠር ችሏል

The former Manchester United target is enjoying his life under current Reds boss Jurgen Klopp

የቀድሞው የማንችስተር ዩናይትድ ዒላማ ከወቅታዊው የቀዮቹ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ጋር ያለው ህይወት ደስተኛ አድርጎታል

ማኔ በሊቨርፑል ያሳካቸው ቁጥራዊ መረጃዎች

ይደግፈው የነበረ ቡድን በመኖሪያ መንደሩ ባምባሊ አቅራቢያ የአንድ ሰዓት ከግማሽ የመኪና ጉዞ ርቀት ላይ የሚገኘው የደቡባዊ ሴኔጋል ከተማ ዚጉንኮር ክለብ የሆነው ካሳ ስፖርትስ የተሰኘው ትልቅ ክለብ ነው። 

“የእኔ መንደር ከዳካር ብዙ የራቀ ነው። እዚያ ድረስ መጥቶ ማንም ሊያየኝ እንደማይመጣ አስብ ነበር። ስለዚህ እግርኳስን እንደምወድና መሻሻል እንደምፈልግ ለወላጆቼ በመንገር  በተለያዩ ቡድኖች ውስጥ ለመሰልጠን ወደከተማ አመራን። ያን ጊዜም ነበር መመረጥ የቻልኩት።” ሲል ተናግሯል። ስለፕሮፌሽናል እግርኳስ ጅማሮው ሲናገር።

የመጀመሪያ ሙከራ ሲያደርግ በማኔ ላይ ተሳልቀውበታል። ለመጀመሪያ ጊዜ ወደሙከራ ስፍራድ ሲያመራ  የተቀደደ ጫማና ዘባተሎ መለያ በመልበስ ነበር። ነገር ግን ከዚያ በኋላ ከፈረንሳዩ ሊግ 1 ክለብ ከሆነው ሜትዝ ጋር የጠበቀ ቁርኝት ያለው ጀነሬሽን ፉት የተሰኘው ዝነኛ የእግርኳስ ማሰልጠኛ ተቋም ተመለከተውና በዚያ እንዲሰለጥን ዕድሉን ሰጡት። 

የአጎቱን ጥርጣሬ ጥሶም ወደፈረንሳዩ ሊግ ለመጫወት ወደአውሮፓ አመራ። ቀጥሎም ከሜትዝ ዳጎስ ባለ የዝውውር ክፍያ የትልልቅ ክለቦችን ቀልብ ወደገዛበት ሬድቡል ሳልዝበርግ ተዛወረ።

በወቅቱ ክሎፕ አሰልጣኝ ወደነበሩበት ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ለመዛወር ከጫፍ ደረሶ በመጨረሻዋ ሰዓት ዝውውሩ ሳይሳካ ቀርቶ ሰኞ በተቃራኒ የሚገጥማቸውን ሮንልድ ኩመን ወደሚሰለጥነው ሳውዛምፕተን አመራ። 

“በእንግሊዝ በመጀመሪያ አከባቢ የአየሩ ፀባይና ዝናቡ ትንሽ ችግር ሆኖብኝ ነበር።” ይላል ማኔ ስለእንግሊዝ ቆይታው ሲናገር “ነገር ግን የዚህን ሃገር የእግር ኳስ ባህል እወደዋለሁ። ወደሊቨርፑል ሳመራ ለተወሰኑ ጊዜያት የቆየሁት በሆቴል ነበር። አሁን ግን በከተማው ደቡባዊ ክፍል የመኖሪያ ስፍራ አግኝቻለሁ። ከጓደኞቼ ጋር በመሆንም ወደሬስቶራንቶች እሄዳለሁ። እዚህ መሆኔንም ወድጄዋለሁ።”

Mane will miss a handful of Liverpool's January fixtures due to the Africa Cup of Nations

ማኔ ሙሉ የጥር ወርን በአፍሪካ ዋንጫ ምክኒያት ከሊቨርፑል ጨዋታ ይርቃል

He insists Liverpool will cope without his services during his time away with his country

እሱ ለሃገሩ ለመጫወት ሲያመራ ሊቨርፑል ያለእሱ ጨዋታዎችን በሚገባ እንደሚወጡ ያስባል

ሳውዛምፕተን በነበረበት ወቅት ግንቦት 2015 የፕሪሚየር ሊጉን ፈጣን ሃትሪህ በመስራት ክብረወሰን ይዟል። ቀድሞ በሮቢ ፎውለር ተይዞ የነበረውን ክብረወሰንም ሳውዛምፕተን አስቶንቪላን 6ለ1 በረታበት ጨዋታ ነበር በሁለት ደቂቃዎች ከ56 ሰከንድ ጊዜ ውስጥ ሶስት ግቦችን ከመረብ ላይ በማስረፍ የተረከበው።

በዚያው ዓመት ክረምት ወደማንችስተር ዩናይትድ እንደሚዛወር ስሙ ከክለቡ ጋር ተያይዞ ነበር። ነገር ግን ክሎፕ ባለፈው ሰኔ ወር እስኪያስፈርሙት ድረስ በሴንቲ ሜሪ ሊቆይ ችሏል።

አንዳንዶች ሊቨርፑል ከመጠን በላይ ወጪ አድጎበታል ብለው ሊያስቡ ይችላሉ። ይሁን እንጂ ከፊርሚኖ እና ከኮቲንሆ ጋር አስፈሪ ጥምረት ለመፍጠር ያስቻለውን አጨዋወት የተመለከተ ግን ሃሳቡ ስህተት እንደነበር መረዳት ይችላል።

“በአስለጣኙ ትዕዛዝ ጨዋታን መተግበር የሚያስደስት ነገር ነው።” ይላል ማኔ ስለክሎፕ ሲናገር። “የእሱ ጥሩ  ነገር ተጫዋቾች አቅማቸውን አውጥተው እንዲጠቀሙበት የሚያደርገው ግፊት ነው። ሁላችንንም እንደቡድን ነው የሚያነሳሳን። እሱ ተጫዋቾቹን በሙሉ ይወዳል። ተጫዋቾችም ለእሱ አድናቆት አላቸው።

“በክሎፕ ላይ ምን የተለየ ነገር አለ? ያ ጥሩ ጥያቄ ነው።” ይላል ማኔ ስለክሎፕ ሲናገር ” ትልቁ ልዩነት ከተጫዋቾቹ ጋር ጥብቅ የሆነ ቀረቤታ ያለው መሆኑ ነው። እነሱም ከእነሱ ጋር ጥብቅ ቁርኝት እንዳላቸው  ነው የሚሰማቸው። ይህ የሰብዓዊነት ቀረቤታ ነው። ተጫዋቾች ለእሱ ይጫወታሉ። ለእሱ ሲሉም ማሸነፍ ይሻሉ። ከፊት ያለነው ተጫዋቾችም በማጥቃቱ ሚና ላይ ያለውን ፍሰት እንወደዋለን።

“ዘዴንው በጠም ወደነዋል። ክፍት የሆነ አጨዋወት መጫወት መቻላችንንም በሚገባ የምንወደው ነገር ነው። በዚህ መንገድ መስራቱንም እንወዳለን። ይህም ነው በግብ ማግባቱ ላይ የራሴን አስተዋፅኦ እንዳደርግ የረዳኝ።”

በቀጣዩ ወር በጋቦን በሚደረገው የአፍሪካ ዋንጫ ሊቨርፑል የእሱን አስተዋፅኦ እንደሚያጣው ሲጠየቅ ማኔ እራሱን በአሉታ ነቅንቆ “ያለእኔም እንደሚሆን እርግጠኛ ነኝ።” በማለት በፈገግታ ተሞልቶ። “እንዲያውም እዚህ ያሉት ልጆች ይበልጥ የተሻሉ ይሆናሉ።” ሲል ጉድለቱ ጉዳት እንደማይፈጥር በማሰብ ቀናውን ተመኝቷል።

Categories

ሊቨርፑል

Advertisements
%d bloggers like this: