Skip to content
Advertisements

የሰኞ አመሻሽ የአውሮፓ ጋዜጦች የዝውውርና ሌሎች አስደንጋጭ እንዲሁም አዝናኝ ወሬዎች

ታህሳስ 10, 2009| በ ሚኪያስ በ. ወርዶፋ

የ21 ዓመቱ የሊቨርሉ አጥቂ ኦሪጊ ኤቨርተኖች በዛሬው የደርቢ ጨዋታ “ለጦርነት” እንዲዘጋጁ ሲል አስጠንቅቋል፡፡ (ዴይሊ ቴሌግራፍ)

የቀድሞው የዩናይትድ አሠልጣኝ ሊውስ ቫንሀል የፓሪስ ሰንዥርሜን አሠልጣኝ እንዲሆኑ በክለቡ እቅድ ውስጥ ተይዘዋል፡፡ (ቲኤፍ አይ)

29 ዓመቱ የቼልሲ አማካኝ ጆን ኦቢ ሚካኤል ወደ ፈረንሳይ ሊግ 1 ክለብ ማርሴል ለመዘዋወር ከፈረንሳዩ ክለብ ጋር በድርድር ላይ ነው፡፡ (ዴይሊ ሚረር)

የ 36 ዓመቱ የቼልሲ አምበል ጆን ቴሪ የቻይና ክለብ አዲሱ የዝውውር ኢላማ ሲሆን የቻይና ሊግ ክለቦች የሆኑት ጓንዙ ኤቨርግራኔድና ሻንጋይ ሺኑዋ ተከላካዩን ለማስፈረም ፍላጎት አሳድረዋል፡፡ (ዴይሊ ኤክስፕረስ)

ቶትነሀሞች ዩናይትድና ቼልሲ ጭምር ለሚፈልጉት የአትላንታው አማካኝ ፍራንክ ኬሲ የ 19 ሚሊዮን ፓውንድ የዝውውር ሂሳብ አቀረበ፡፡ (ካልሲሜርካቶ)

ክሪስታል ፓላሶች ለ 32 ዓመቱ አማካኝ ማቲው ፍላሚኒ ወደ ማርሴል እንዲመለስ ፈቃድ ሰጥተውታል፡፡ (ዴይሊ ሚረር)

የ35 ዓመቱ የዩናይትድ አጥቂ ዛላታን(ከላይ በምስሉ ላይ የሚታየው) ኢብራሂሞቪች እስከ 50 ዓመቱ ሊጫወት እንደሚችል ተናገረ፡፡ (ዴይሊ ስታር)

ኢንተር ሚላኖች በሞውሪንሆ ስር ዘንድሮ ስምንት ጨዋታ ብቻ ማድረግ የቻለውን የዩናይትዱን የ 27 ዓመት አማካኝ ሞርጋን ሽንደርሊንን ከሚፈልጉ ክለቦች አንዱ ሆነው ብቅ አሉ፡፡ (ካልሲሜርካቶ)
የሪያል ማድሪዱ ኮሎምቢያዊ የ 25 ዓመት አጥቂ ጀምስ ሮድሪጌዝ ብዙ ጨዋታዎችን ለማድረግ ከመፈለግ ጋር በተያያዘ ክለቡን ሊለቅ እንደሚችል ተናገረ፡፡ (ስካይ ስፖርት)

ሮድሪጌዝ በቃሉ እንዳረጋገጠው ከሆነ ቼልሲዎች ወደ ቻይና ሊግ ሊያመራ በዝግጅት ላይ ያለውን ኦስካርን(ከስር በምስሉ የሚታየው) ለመተካት በማሰብ ለዝውውሩ 75 ሚሊዮን ፓውንድ አቅርበዋል፡፡ (ዘ ሰን)

ነገር ግን የነጮቹ አምበል ሰርጂዮ ራሞስ ከትናንትናው የአለም የክለቦች ዋንጫ ድል በኃላ ወዲያውኑ ሮድሪጌዝ ስለ ዝውውር ጉዳይ በማውራቱ አለመደሰቱን “ይህ ቀን የግል ጉዳይ የሚወራበት አይደለም።” ሲል በመናገር ንዴቱን ገልጿል፡፡ (አስ)

ሊቨርፑሎች ለ 19 ዓመቱ የሳንቶስ አጥቂ ቲያጎ ማያ ፍላጎት አሳድረዋል፡፡ (ኢኤስፒን)

ባርሴሎናዎች ከሊዮኔል(ከስር በምስሉ የሚታየው) ሜሲ ጋር በውል ማራዘሚያ ዙሪያ ንግግር ገና እንዳልጀመሩና የሜሲ ወኪል የሆኑት አባቱ ጆርጌ ወደ ስፔን መምጣታቸው ጥሩ ምልክት ቢሆንም ደጋፊዎች ብዙ እንዳይጠብቁ ተገልጿል፡፡ ነገር ግን የውል ማራዘሚያው ስምምነት ላይ ከተደረሰ አዲሱ ስምምነት ሜሲን የአለም ውዱ ተከፋይ ተጫዋች እንደሚያደርገው ታውቋል፡፡ (ዴይሊ ሚረር)

የመዶሻዎቹ አሠልጣኝ ስላቪያን ቢሊች ባሳለፍነው ሳምንት ከነበራቸው ሶስት ጨዋታዎች ሰባት ነጥብ ሰብስበው ስኬትን ቢያስመዘግቡም የክለቡን የገና ድግስ ሰርዘዋል፡፡ ተጫዋቾቹ በገና እለት መጠጥ እንዲጠጡ ግን ፈቃድ ሰጥተዋል፡፡ (ዴይሊ ቴሌግራፍ)

የሊቨርፑሉ አሠልጣኝ የርገን ክሎፕ ቡድናቸው እንደ አርሰናል ያለፈው ሳምንት አጋማሽ ግጥሚያ በጉዲሰን ፓርክ እንደማይዝረከረክ ተናገሩ፡፡ (ዴይሊ ሚረር)   

ኤሲ ሚላኖች ዌስትሀም አይኑን የጣለበት የ 30 ዓመቱ አጥቂያቸው ካርሎስ ባካ ለሽያጭ እንደማይቀርብ ተናግረዋል፡፡ (ኢቪኒንግ ስታንዳርድ)

የቼልሲው አማካኝ ኒማኒያ ማቲች ቡድናቸው ያለፈውን ዓመት ውድቀት አንደረሳና ይልቅ የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ስለማንሳት እያሰበ እንደሆነ ተናገረ፡፡ (ዴይሊ ሚረር)

አክሴል ዊትስል ወደ ጁቬ ለመግባት ጫፍ ላይ በመሆኑ ከቼልሲ አለቃ አንቶኒዮ የቀረበለትን የስልክ ጥሪ ውድቅ አደረገ፡፡ (ዴይሊ ሚረር ዘ ሰንን ጠቅሰ እንደፃፈው)

በማህበራዊ ሚዲያዎች ትኩረት ወዳገኙ ጉዳዮች ስናልፍ ….. 

ከትናንት የሲቲና አርሰናል የደርቢ ጨዋታ ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ሲቲዎች በጉልበት ጉዳት ምክንያት ቀዶ ጥገና በማድረጉ አመቱን ሙሉ ወደ ሜዳ የማይገባውን ጀርመናዊውን አማካኝ ኤከር ጉንዶጋንን ለማሰብ የሱ ስምና የማሊያ ቁጥር ከፊት የተፃፈበት ቲሸርት በማሊያቸው(ከስር በምስሉ ላይ እንደሚታየው) ላይ ደርበው ወደ ሜዳ መግባታቸው በማህበራዊ ሚዲያዎች ትልቅ ትኩረት ያገኘ ጉዳይ ሆኗል፡፡

ይህ እድለ ቢስ ጀርመናዊ ሀገሩ የ 2014 ዓለም ዋንጫን ስታነሳ በጉዳት ምክንያት ከስብስቡ ውጪ ሆኖ የነበረ ሲሆን ዘንድሮ በተደረገው የ 2016 የፈረንሳይ አለም ዋንጫም እንዲሁ በጉዳት በውድድሩ ላይ ሀገሩን መወከል ሳይችል ቀርቷል፡፡ 

በመጨረሻም ….              

አርሰን ቬንገር ከትናንትናው ሽንፈት በሁዋላ የፕሪምየር ሊጉ ዳኞች ያልተገባ እንክብካቤ እየተደረገላቸው እንደሚገኙና “እንደ አንበሳ” በልዩ ሁኔታ እየተጠበቁ እንደሆነ በመናገር የቃላት ጥቃት ሰንዝረውባቸዋል፡፡ ቬንገር ለቁጡ ንግግር የዳረጋቸው በትናንትናው ጨዋታ ቡድናቸው የተቆጠሩበት ሁለት ግቦች ‘ከጨዋታ ውጪ ናቸው’ የሚል ምክንያት ነው፡፡  (ዴይሊ ሚረር) 

የሆፈንየሙን መሀል ተከላካይ ኒክላስ ሱሌይን ለማስፈረም የሚደረገውን እሽቅድድም ከሊቨርፑሎች በመቀበል ሰማያዊዎቹ ቼልሲዎች እየመሩ ይገኛል፡፡ (ፉት ቦል 365)

ሴስክ ፋብሬጋዝን በ 40 ሚሊዮን ፓውንድ የዝውውር ሂሳብ ለመውሰድ የቻይናው ክለብ ጓንዙ ኤቨርግራኔድ ኢላማ ውስጥ አስገብቶታል፡፡ (ዴይሊ ሜይል)

እውነት ለመናገር በፋብሬጋዝ ዙሪያ የሚወራው ወሬ እርባና ቢስ ነው፡፡ የ 29 ዓመቱ ስፔናዊ ወደ ኮንቴ ቡድን ዳግም ተመልሷል፡፡ በቼልሲ የፕሪምየር ሊግ ጉዞ ላይም ወሳኝ አስተዋፅኦ ይኖረዋል፡፡ (ፉት ቦል 365)   

ዩናይትድ በመጪው ጥር ከቡድኑ የሚለቁትን ሽንደርሊንና ሜምፈስ ዲፔይን(ከላይ በምስሉ የሚታየው) ለመተካት 15 ሚሊዮን ፓውንድ የተገመተውን የሳውዝአምፕተን አምበል ጆሴ ፎንቴና የዎልፍስበርጉን አማካኝ ቪክቶር ሊንድሎፍን ራዳር ውስጥ አስገብቷል፡፡ (ፉት ቦል 365)  

Advertisements

ሚኪያስ በቀለ View All

ይህን ዘገባ ያቀረብኩላችሁ የኢትዮአዲስ ስፓርት ኤዲተርና ፀሀፊ እኔ ሚኪያስ በቀለ ነኝ።

%d bloggers like this: