Skip to content
Advertisements

ንጎሎ ከንቴ፦ የሁለት ክለቦች ስኬቶች ቁልፉ ተጫዋች 

 • SMS
 • WhatsApp

ወንድወሰን ጥበቡ | ታህሳስ 10፣ 2009 ዓ.ም

  የአንድ ዓመት ጊዜ በሌስተርና ቼልሲ ቤት ምንኛ የተለያየ ለውጥ መፍጠር ችሏል። ሁለቱ ክለቦች ወደአዲስ ዓመት የእረፍት ወቅት ውድድሮች ሲቃረቡ የተለዩ አቋሞችን በመያዝ ነው።

  ከ12 ወራት በፊት ወደኋላ ተጉዘን ስንመለከት ግን ሌስተር ሲቲዎች በስፖርቱ ዓለም ያልተለመደ ስኬትን ማስመዝገብ የቻሉበት፣ ቼልሲ ደግሞ በእጅጉ ስኬት ርቆት አሰልጣኙን ጆዜ ሞሪንሆን ከክለቡ ያስናበተበት ወቅት ነበር።

  ሁለቱ ክለቦች አሁን ያሉበትን ሁኔታ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ካነፃፅርነው ግን ቼልሲ በደረጃው አናት ላይ በቀዳሚነት መደላድሉን አመቻችቶ ሲገኝ፣ በአንፃሩ ቀበሮዎቹ ባለፈው ዓመት ሰማያዊዎቹ በተመሳሳዩ ጊዜ ተቀምጠውበት በነበረ የ15ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። እና ግን እነዚህን ሁለት ክለቦች የሚያቆራኛቸው አንድ ነገር አለ?

  N'Golo Kante has been a revelation for Chelsea and a key factor behind their blistering formእሱም ደቃቃ ግን ጠንካራ፣  መሮጥ የማይታክተውና ጨዋታን ለማጨናገፍ ወደኋላ የማይለው ፈረንሳዊው ተጫዋች ን’ጎሎ ካንቴ ነው።

  ቼልሲ የሌስተሩን እንቁ ባለፈው የክረምት የዝውውር ወቅት ያስፈረመው አንቶኒዮ ኮንቴ በስማያዊዎቹ አዲስ ዘመን ጅማሮ ይሆናቸው ዘንድ ቀዳሚ ዒላማቸው ካደረጉት በኋላ በ32 ሚ.ፓ ዋጋ ነበር። 

  ካንቴ፣ ከሪያድ ማህሬዝና ከጄሚ ቨርዲ ጋር ለሌስተር የእንግሊዝ ሻምፒዮንነት አብይ ምክኒያት በመሆኑ ውዳሴ የሚቸረው ተጫዋች ነው።

  ካንቴን ይጫወትበት ከነበረው የሰሜን ምዕራቡና የሊግ አንዱ ክለብ ኬን ወደእንግሊዝ የእግር ኳስ መድረክ ለማምጣት የቀበሮዎቹ  የምልመላ ቡድን እይታ አድናቆት የሚቸረው ነው።

  Kante has thrown himself into the action since his move and has looked instantly at home

  አማካኙ በዓለም የእግርኳስ መድረክ ላይ በሌስተር ጎልቶ ከመውጣቱና በዩሮ 2106ቱ የዲዲየ ደሾምፕ የመጀመሪያ የፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድን ተጫዋቾች ዝርዝር ላይ በቀዳሚነት ለመስፈር ያደረገው የሽግግር ምንጭ መነሻው የፈረንሳዩ ስድስተኛ ዲቪዚዮን ነው።

  ካንቴ ለአንቶኒዮ ኮንቴው ቼልሲ ከፈረመበት ጊዜ አንስቶ ድንቅ ብቃቱን እያሳየም ይገኛል። የእሱ በቡድኑ ውስጥ መገኘትና ቼልሲ በፕሪሚየር ሊጉ ላይ ዳግም ማንሰረራትና በአዲሱ ዓመት በደረጃው አናት ላይ መገኘት መቻል የአጋጣሚ ጉዳይ አይደለም። 

  እስካሁን ችልሲ በዚህ የውድድር ዘመን ባደረጋቸው በሁሉም 17 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ 12 የግብ እድሎችን ሲፈጥር፣ ኳስ የማቀበል ስኬቱም 89 በመቶ ነው።

  ካንቴ በሌስተር – በ2015/16 የውድድር ዘመን

  ተሰለፈ – 37

  አሸነፈ – 23

  ተሸነፈ – 3

  ግብ – 1 

  ኳስ የማጨናገፍ ስኬት – 71%

  ስኬታማ  ኳስ ቅብብል – 277

  ጥፋት – 43 

  ካንቴ በቼልሲ – በ2016/17

  ተጫወተ – 17

  አሸነፈ – 14

  ተሸነፈ – 2

  ግቦች – 1 

  ኳስ የማጨናገፍ ስኬት  – 58%

  ስኬታማ  ኳስ ቅብብል  – 94

  ጥፋት – 23 

  ፈረንሳዊ ተጫዋች የማንችስተር ዩናይትድ ተከላካዮችን በማለፍ በስታንፎርድ ብሪጅ የሞሪንሆውን ቀያይ ሰይጣኖቹን 4ለ0 መርታት የቻሉበትን አንድ ግብም ማስቆጠር ችሏል።

  ካንቴ ባለፈው የውድድር ዘመን በሌስተር ማሳደር የቻለውን ተፅእኖ በዚህ የውድድር ዘመንም የምዕረብ ለንደኑ ክለብ በፕሪሚየር ሊጉ ባስመዘገበው ተከታታይ ድል ላይ ተሳታፊ በመሆን ተመሳሳይ ተፅእኖ እያሳደረ ይገኛል። 

  Kante has carried his incredible form over to Chelsea, as reflected in his win percentage

  የካንቴን የማሸነፍ ስኬት ከተመለከትን በቼልሲ የሚደንቅ ብቃት ማሳየት ችሏል

  The midfielder allowed the likes of Jamie Vardy to flourish last season with the Foxes

  አማካኙ በሌስተር እንደጄሚ ቫርዲ ያሉ ተጫዋቾች ጎልተው እንዲወጡ ማድረግ ችሏል

  Chelsea boss Antonio Conte made Kante his priority target when taking over at the club

   የቼልሲው አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ ክለቡን ሲረከቡ ካ’ንቴ የመጀመሪያ ዒላማቸው ነበር

  በእንግሊዞቹ መሪ ክለቦች ውስጥ በነበረው ቆይተም ካንቴ ከመሰል ተጫዋቾች የላቀ ከፍ ያለ የማሸነፍ ስኬት አለው። ካደረጋቸው 54 ጨዋታዎች በ37ቱ ድል ማጣጣም ችሏል። ከእሱ የተቀራረበ የማሸነፍ ስኬት ያላቸው የአርሰናሉ ናቾ ሞንሬልና የማንችስተር ሲቲው ያያ ቱሬ ናቸው።

  በቼልሲ ቡድን ውስጥ የካንቴ መኖር የአንቶኒዮ ኮንቴው ቡድን ሚዛኑንን እንዲጠብቅና እንደኤዲን ሃዛርድና ዲያጎ ኮስታ ላሉ ተጫዋቾች ይበልጥ የማጥቃት እድል ለመፍጠር ነፃነት የሚሰጥ ሲሆን፣ ለአዲሶቹ የቼልሲ ሶስቱ ተከላካዮች ጥምረት ተጨማሪ የመከላከል አቅም ይፈጥራል። 

  ይሁን እንጂ ቼልሲ በዚህ የውድድር ዘመን ለመጀመሪያ ጊዜ በሁሉም የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ላይ መስለፍ የቻለውን ፈረንሳዊ ተጫዋች ሳይዝ ቀጣዩን የሊግ ጨዋታ ያደርጋል።

  ከንቴ ቼልሲ ከሜዳው ውጪ ክሪስታል ፓላስን በረታበት ጨዋታ በውድድር ዘመኑ አምስተኛ ቢጫ ከርድ መመልከቱን ተከትሎ ሰማያዊዎቹ በቦክሲንግ ደይ ጨዋታ በሜዳው ቦርንማውዝን የሚገጥሙበት ጨዋታ ላይ መሰለፍ አይችልም።

  The defensive midfielder earned the acclaim of his peers last season, winning Player's Player of the Season with Leicester

  አማካኝ ተከላካዩ ባለፈው የውድድር ዘመን ባሳየው ድንቅ ብቃት በተጫዋቾች የተመረጠ ምርጥ ተጫዋችነትን ክብር ተቀዳጅቷል

  የኮንቴ ቡድን ይህን ጨዋታ የሚያሸንፍ ከሆነም አዲሱን የ2017 ዓመት በመሪነት ተቀብሎ ስድስተኛውን የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ለማንሳት የተሻለ ዕድል ያለው መሆኑንም ያስመሰክርበታል።

  ሌስተሮች በበኩላቸው የውድድር ዘመኑን ደካማዎቹን ከዋክብቶቻቸውን በመቀየርና አምና ድንቅ የነበረውን ተንሳፋፊ መርከባቸውን ማደስ ግድ ይላቸዋል።

  እስከዚየው ግን ን’ጎሎ ካንቴ በክለቡ ላይ የፈጠረው ሰፊ ክፍተት በግልፅ ታይቷል። ይህን ክፍተት ለመድፈንም ቀላል የማይባል ጊዜ መውሰዱ እሙን ነው።

  Advertisements
  %d bloggers like this: