Skip to content
Advertisements

የማክሰኞ አመሻሽ የአውሮፓ ጋዜጦች የዝውውርና ሌሎች አስደንጋጭ እንዲሁም አዝናኝ ወሬዎች

ታህሳስ 11, 2009|በሚኪያስ በ. ወርዶፋ

አርሰናሎች ሚሶት ኦዚልን ወይም አሌክሲስ ሳንቼዝን በክለቡ ማቆየት ካልቻሉ በምትኩ የጀርመኑን የ 27 ዓመት የፌት መስመር ተሰላፊ ማርኮ ሩስን ለማምጣት አስበዋል፡፡ (ቴሌግራፍ)

ቼልሲዎች ለአጥቂው ዲያጎ ኮስታ የሁለት አመት አዲስ የውል ማራዘሚያ ስምምነት ሊያቀርቡ ሲሆን በአዲሱ ስምምነት መሰረትም የዲያጎ ኮስታ ሳምንታዊ ደሞዝ በ 50,000 ፓውንድ ጭማሪ አሳይቶ 200,000 ፓውንድ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ (ሚረር)

ማንችስተርና ቼልሲ የሮማውን የ 23 ዓመት ጀርመናዊ ለማስፈረም እየተፎካካሩ ናቸው፡፡ (ዘ ሰን)

ሰማያዊዎቹ ቼልሲዎች የፈነርባቼውን የ 27 ዓመት ጀርመናዊ የመሀል ተከላካይ ሲሞን ኪጃርን ለማስፈረም ፍላጎት አሳድረዋል፡፡ (ኢኤስፒኤን)

የ 32 ዓመቱ አርጀንቲናዊ አጥቂ ካርሎስ ቴቬዝ ሪከርድ በሆነ ሳምንታዊ 615 ሺህ ፓውንድ ክፍያ ክለቡን ቦካ ጁንየርስን ለቆ ወደ ቻይናው ሊግ ክለብ ሻንጋይ ሺንዋ ሊያመራ ነው፡፡ (ዴይሊ ሜይል) 

የቤኔፊካው ፕሬዝዳንት 38 ሚሊዮን በተገመተው ስዊድናዊው ተከላካያቸው ቪክቶር ሎንድሎፍ ዝውውር ዙሪያ ከዩናይትድ ባለስልጣናት ጋር ለመነጋገር ወደ እንግሊዝ በረዋል፡፡ (ኦጆጆ – ፓርቹጋል)

የማንችስተሩ ቤልጄማዊ አማካኝ ማርዋን ፌላኒ(ከላይ በምስሉ የሚታየው) ወደ ጣሊያን ለማማምራት አስቧል፡፡ (ዴይሊ ሜይል)

አርሰናሎች ለጀርመናዊው የዎልፍስበርግ የ 23 ዓመት አማካኝ ጁሊያን ድራክስለር 30 ሚሊዮን ፓውንድ ለመክፈል አስበዋል፡፡ (ዴይሊ ኤክስፕረስ)

የዌስትሀሙ የ 29 ዓመት አማካኝ ዲሜትሪ ፓዬት ወደ ፈረንሳይ ሊግ 1 ክለብ ወደ ሆነው ማርሴይ ለመመለስ ራሱን ክፍት ሊያደርግ እንደሚችል ተናገረ፡፡ (ኤስኤፍ አር ስፖርት – ፈረንሳይ)

የስዋንሲ ክለብ ተጫዋቾች ዘንድሮ የገና በዓል ድግስ እንደማይኖራቸው በስምምነት ወስነዋል፡፡ እንደ ምክንያት ያቀረቡትም ክለቡ በፕሪምየር ሊጉ 19ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ ወራጅ ቀጠና ውስጥ በሚገኝበት በዚህ ሰዓት ድግስ ማዘጋጀቱ ተገቢ አይደለም ብለው በማሰባቸው ነው፡፡ (ዌልስ ኦንላየን)

ጉንጋምፕ የተሰኘው የፈረንሳ ክለብ ብቸኛው አሠልጣኙ ከተጫዋቾቹ የበለጠ ደሞዝ የሚያገኙበት ክለብ ነው፡፡ (ሌኪፕ – ፈረንሳይ)

ዩናይትድ በ 42 ሚሊዮን ፓውንድ የቤንፊካውን ተከላካይ ቪክቶር ሊንድሎፍ ለማስፈረም ከጫፍ ላይ ነው፡፡ ሊንድሎፍ የ 22 ዓመት ባለ ብሩህ ራእይ ተከላካይ ሲሆን የዩናይትዱ ኢብራሂሞቪችም ለክለብ ጉዋደኞቹ ተጫዋቹ ወደ ትልቅ ክለብ ለመዘዋወር እንደተዘጋጀ ነግሯቸዋል፡፡ 

ስዊድናዊው ኢንተርናሽናል 11 ጨዋታዎችን ለሀገሩ ማድረግ የቻለና በቤኔፊካ ባለው አስደማሚ ብቃቱ የተለያዩ የአውሮፓ ክለቦች አይናቸውን የጣሉበት ታዳጊ ነው፡፡ ለዝውውሩም ቤኔፊካ 42 ሚሊዮን ፓውንድ የጠየቀ ሲሆን ዩናይትድ ግን 37 ሚሊዮን በቂ ነው እያለ ነው፡፡ 

ባለፉት ሳምንታት ፊል ጆንስና ማርኮስ ሮሆ በዩናይትድ ቤት አስደናቂ የሆነ ጥሩ የመከላከል ቅንጅት ቢፈጥሩም ፖርቹጋላዊው አሠልጣኝ ጆሴ ሞውሪንሆ ኤሪክ ቤሊ በመጪው ጥር ወደ አፍሪካ ዋንጫ እንደሚያመራ በመገመት ይህንን ስዊድናዊ ለማማጣት ፈልገዋል፡፡ (ሜትሮ)

ቼልሲዎች በመጪው ጥር የ 21 ዓመቱን አጥቂ ባትሱሀዪ በውሰት ለማንም ክለብ እንደማይሰጡ ታወቀ፡፡ ይህንን ታዳጊ አጥቂ ለመውሰድ ከኤሲሚላን ውጪ የእንግሊዙ ክለብ ዌስትሀም ፈልጎ የነበረ ቢሆንም አንቶኒዮ ኮንቴ ወደ የትኛውም ክለብ መሄድ እንደሌለበት ውሳኔ አሳልፈዋል፡፡ (ዘ ጋርዲያን)

በመጨረሻም …

የዌስትሀሙ አማካኝ ተጫዋች ዲሜትሪ ፓዬት የጥር ወር የዝውውር መስኮት ሊከፈት ቀናት በቀሩበት በዚህ ሰዓት በፈረንሳይ ባደረገው አንድ ቃለ መጠይቅ ላይ የአርሰናል ክለብ አድናቂ መሆኑን በመናገር ለመድፈኞቹ “ኑና ውሰዱኝ” የሚል መልዕክት አስተላልፏል፡፡

የመድፈኞቹ አቃ አርሰን ቬንገር ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የፓዬት አድናቂ መሆናቸውና ሊያስፈርሙት እንደሚፈልጉ እየተዘገበ ሲሆን ተጫዋቹም የዝውውር ጭምጭምታውን እንደሰማና እንደሚያውቅ አምኗል፡፡ 

ለመዶሻዎቹ ዌስትሀሞች 55 ጨዋታዎችን ማድረግ የቻለው ይህ የአጥቂ አማካኝ ስለጉዳዩ ሲጠየቅም “አርሰን ቬንገር በአርሰናል ቤት የጎደለውን ቦታ እንድሞላ እኔን ማሰባቸውን አንብቤያለሁ:: ነገር ግን ስለኔ ምንም አልተናገሩም::” በማለት መልሱን በሳቅ አጅቦ ሰጥቷል፡፡ (ሜትሮ)            

በሌላ በኩል የቼልሲው አለቃ አንቶኒዮ ኮንቴ የስብስባቸውን ጥልቀት ይበልጥ ለማሳደግ በማሰብ የጄኖዋውን የክንፍ ተጫዋች ዲዬጎ ላክሳልት በመጪው የጥር የዝውውር መስኮት ለማስፈረም እቅድ ይዘዋል፡፡ (ዴይሊ ሚረር) 

የአትሌቲኮው ማድሪዱ የፊት መስመር ተጫዋች አንቶኒዮ ግሪዝማን የአርሰናሉ ሎውረንት ኮሽሊኒ ወደ ኢምሬትስ እንዲመጣና ለአርሰናል እንዲፈርም በተደጋጋሚ እንደሚጎተጉተው ዛሬ ይፋ አድርጓል፡፡

ፈረንሳዊው አጥቂ ለስፔኑ ክለብ 126 ጨታዎችን አድርጎ 66 ጎሎችን በማስቆጠር በክለቡ ስኬታማ ጊዜን ማሳለፍ የቻለ ተጫዋች ሲሆን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን ለበርካታ ጊዜ ስሙ ከእንግሊዝ ፕሪምር ሊግ ክለቦች ጋር እየተያያዘ ይገኛል፡፡

የተለያዩ ሪፖርቶች እንደሚጠቁሙትም ተጫዋቹን በጥብቅ የሚገልጉት ዩናይትዶች ሲሆኑ ተጫዋቹም ወደ ቀያዮቹ ሴይጣኖች ማምራት እንደሚፈልግ በተደጋጋሚ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ እንደውም አንዳንድ የዜና ምንጮች ዝውውሩ ውስጥ ለውስጥ መጠናቀቁን እየተናገሩ ይገኛሉ፡፡ 

ስለጉዳዩ የተጠየቀው ግሬዝማን ግን አሁን በስፔን ባለው ህይወቱ ደስተኛ እንደሆነ ገልፆ ነገር ግን የብሄራዊ ቡድን አጋሩ ሎውረንት ኮሽሊኒ ከመጋረጃ በስተጀርባ ወደ ሰሜን ለንደን እንዲመጣ የሚሳድርበትን ተፅእኖ ይፋ አድርጓል፡፡ (ሜትሮ)

Advertisements

ሚኪያስ በቀለ View All

ይህን ዘገባ ያቀረብኩላችሁ የኢትዮአዲስ ስፓርት ኤዲተርና ፀሀፊ እኔ ሚኪያስ በቀለ ነኝ።

%d bloggers like this: