Skip to content
Advertisements

አዲስ አበባ ከተማ ከ ደደቢት የጨዋታ ዳሰሳ

አስራት ሀይሌን በዋና አሰልጣኝነት ከሾመ በዋላ በውጤታማ ጉዞ ላይ የሚገኘው ደደቢት ከአዲስ አበባ ከነማ ጋር ይገናኛል

image

በፈይሰል ኃይሌ
የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ዋና አሰልጣኝ  አስራት ሀይሌን አሰልጣኙ አድርጎ ከሾመ በዋላ መልካም በሚባል መሻሻል እያሳየ የሚገኘው ደደቢት የፊታችን እሁድ  በአዲስ አበባ ስቴዲየም አዲስ አበበ ከነማን ያስተናግዳል፡፡ ከመሪው ቅዱስ ጊዮርጊስ በግብ ክፍያ ተበልጦ በሊጉ 2ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው ደደቢት ልክ እንደ ፈረሰኞቹ ሁሉ ተከለካካይ ክፍሉ ጠንካራ ነው እስካሁን በሊጉ ባደረጋቸው 6 ጨዋታዎች 2 ግቦች ብቻ ያስተናገደው ደደቢት ከወዲሁ ለሊጉ አሸናፊነት ትንቅንቁን ጀምሯል፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ኢትዮአሌክትሪክን በጎዶሎ ተጫዋች መርታታቸውን ተከትሎ በርከት  ያሉ ውደሳዎችን ያገኙት ሰማያዊዎቹ  የፊታችን እሁድ ጠንካራውን የመሀል ተከላካያቸውን አይናለም ሀይሉን በቅጣት ምክንያት ማሰለፈ አይችሉም፡፡ ክለቡ  ካስቆጠራቸው 7 ግቦች 6ቱን በማስቆጠር የሊጉን ኮከብ ግብ አግቢነት እየመራ የሚገኘው አጥቂው ጌታነህ ከበደ ሰበሮም  በሊጉ በአንድ አመት ውስጥ የምንጊዜውም  ከፍተኛ ግብ አግቢ ለመሆን እየታተረ ይገኛል፡፡

የደደቢት ተጋጣሚ የሆኑት አዲስ አበባ ከነማዎች ጅማሬያቸውን አዋሳ ከነማን በመርታት ቢያሳምሩም እያደር ግን  እየጣሏቸው በሚገኙ ወርቃማ ነጥቦች ምክንያት ወራጅ ቀጠናው ላይ ተቀምጠዋል፡፡ 1 ጨዋታ ብቻ አሸንፈው በ3ቱ ሽንፈት አስተናግደው በ2ቱ አቻ የተለያዩት የዋናው ከተማው ተወካዮቹ በዚህ ብቃታቸው ከቀጠሉ በቀጣይ አመት ወደ ከፍተኛው ሊግ እንዳይወርዱ ተሰግቷል፡፡ የተከላካይ ክፍላቸውም በሊጉ ካሉ ክለቦች መሀል በርከት ያሉ ግቦችን ያስተናገደ ሲሆን  እስካሁን ድረስ 7 ግቦችን ተቆጥረውበታል፡፡ ማስቆጠር የቻለው ደግሞ 5 ግቦችን ሲሆን በ2 የግብ እዳዎችም 14ኛ ደረጃን በሊጉ ይዝዋል፡፡
ሁለቱ ክለቦች ባለፉት 4 የሊጉ ጨዋታዎች ውጤታቸው
W – WIN (አሸነፈ)
D-  DRAW (አቻ)
L – LOSE (ተሸነፈ)
አዲስ አበባ ከነማ   D L L L
ደደቢት            D W D W

Advertisements

ፈይሰል ኃይሌ View All

የኢትዮአዲስ ስፖርት ስራ አስኪያጅ እና የስፖርት ዜናዎች ፀሀፊ

%d bloggers like this: