Skip to content
Advertisements

የሀሙስ አመሻሽ የአውሮፓ ጋዜጦች የዝውውርና ሌሎች አስደንጋጭ እንዲሁም አዝናኝ ወሬዎች

በሚኪያስ በ. ወርዶፋ| ታህሳስ 13, 2009

ሊቨርፑል በጣሊየኑ ቶሪኖ በውሰት የሚገኘውን የ 29 ዓመቱን የሲቲ ግብ ጠባቂ ጆይ ኸርትን ለማስፈረም ፈልጓል፡፡ (ሚረር)

ዌስትሀሞች የአጥቂ መስመር ችግራቸውን ለመፍታት የቴሌግራፉ ማት ሎው “ህልመኛ” ሲል የገለፀውን አንቶኒ ማርሻልን ወይም ማርከስ ረሽፎርድን ወደ ክለባቸው የማምጣት ህልም እንዳላቸው ታውቋል፡፡ ከዚህ ቀደም ኢብራሂሞቪችን ለማስፈረም ፈልገው ሲሞን ዛዛን አስፈርመው ያረፉት መዶሻዎቹ አሁን ደሞ ከዩናይትድ ሁለት ተስፈኛ ወጣቶች አንዱን ወደ ክለባቸው ማምጣት ፈልገዋል፡፡ ከሁለቱ ታዳጊዎች በተጨማሪም የቼልሲውን አጥቂ ሚቺ ባትሱሀይ እና የሊቨርፑሉን ዳንኤል ስቱሪጅን በዝውውር እቅዳቸው አካተዋል፡፡ (ፉትቦል 365)

የሲቲው አሠልጣኝ ፔፔ ጋርዲዮላ ለክንፍ ተጫዋቹ ራሂም ስተርሊንግ “ቀጥተኛና ተግባር ተኮር” እንዲሆን የሰጠው ምክር አሁን ውጤት እያመጣ እንደሆነ ተናገረ፡፡ (ዘ ጋርዲያን) 

የዩናይትዱ አለቃ ጆሴ ሞውሪንሆ በቀጣዩ የጥርና የክረምት የዝውውር መስኮት 180 ሚሊዮን ፓውንድ በመመደብ የአትሌቲኮውን አንቶን ግሬዝማን፣ የቤኔፊካዎቹን ቪክቶር ሊንድሎፍንና ኔልሰን ሴሜዶ  እና የሞናኮውን አማካኝ ቲሞ ባካዮኮን ለማስፈረም አስበዋል፡፡ (ቴሌግራፍ)

ሌሎች ሪፓርቶች እንደሚጠቁሙት ሊንድሎፍ የማንችስተር ብቸኛው የጥር ወር የዝውውር ኢላማ ነው፡፡ (ሚረር)

የሲቲው ያያ ቱሬ ክለቡን ማንችስተር ሲቲን ከጉረቤቱ ዩናይትድ ክለብ በላይ ማስቀመጥ ፍላጎቱ መሆኑንና ህልም ቢሆንም ጠንክረው ከሰሩ እንደሚሳካ ተናገሯል፡፡ (ዘ ጋርዲያን)

የእንግሊዙ ስቶክ ሲቲ ሊንድሎፍን በ 17 ዓመቱ ለሙከራ ወደ ክለቡ ጠርቶት የነበረ ቢሆንም በወቅቱም 260,000 በሆነ አነስተኛ ክፍያ ተጫዋቹን የማስፈረምን እድል “ብቁ አይደለም” በሚል ምክንያት ዝውውሩን ውድቅ አድርጎታል፡፡ (ዴይሊ ሜይል)

ቼልሲ 60 ሚሊዮን ፓውንድ የተለጠፈበትን ጀምስ ሮድሪጌዝን “ዋጋው ውድ ነው” በሚል ምክንያት የማስፈረም እቅዱን ሊሰርዝ ነው፡፡ (ዘ ሰን)

ሳውዝአምፕተኖች  45 ሚሊዮን ፓውንድ የሚገመት የዝውውር ሂሳብ በመጠየቅ ቨርጂል ቫንዲጂክን በክለባቸው ለማቆየት አስበዋል፡፡ (ስኳዋክ)

ነገር ግን ማንችስተር ሲቲዎች የጥር የዝውውር መስኮት ሲከፈት ለቫንዲጂክ 50 ሚሊዮን ፓውንድ በመመደብ ተጫወቹን ወደ ኢትሀድ ለማዘዋወር አስበዋል፡፡ (ዴይሊ ሜይል)

የዩናይትዱ የቀኝ ተከላካይ አንቷን ቫሌንሽያ የሁለት ዓመት ኮንትራት በመፈረም በማንችስተር ቤት ቆይታውን እስከ 2018 ድረስ አራዝሟል፡፡ (ዘ ሰን)

ፒኤስጂ ከዚህ ቀደም ሁለት ጊዜ ሞክሮ ያልተሳካለትን አርሰን ቬንገርን የማዘዋወር ተልዕኮ ድጋሚ ለመጀመር ተዘጋጅቷል፡፡ (ዘ ሰን)

ዌስትሀም በመጪው ጥር የዝውውር መስኮት የስብስቡን ጥልቀት ለማሳደግ ለፕሪምየር ሊጉ ክለቦች “ተጫዋቾቻችሁን በዝውውር መልክ እንድወስድ ፍቀዱልኝ” የሚል የልመና መልክ ያዘለ ደብዳቤ ከመላክ የማይተናነስ የዝውውር ስራ እየሰራ ይገኛል፡፡ (ቴሌግራፍ)   

የቀድሞው የሊቨርፑልና የሲቲ አወዛጋቢ አጥቂ ማሪዮ ባላቶሊ በመጪው ጥር ወደ እንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ለመመለስ በንግግር ላይ መሆኑን ወኪሉ ሚኖ ራዮላ ተናግሯል፡፡ (ቶክ ስፖርት)

በሌላ በኩል ራዮላ ጨምሮ እንደተናገረው ከሆነ ሌላኛው ደንበኛው ሮሚዮ ሉካኩ በኤቨርተን ኮንትራቱን ለማራዘም 99.9 ፐርሰንት ከስምምነት ላይ መድረሱን ተናግሯል፡፡ (ቶክ ስፖርት)

የአትሌቲኮው ዲያጎ ሲሞኔ ኮንትራቱ በቅርቡ ወደ ሁለት ዓመት ቢያጥርም ይህ ስምምነት ካበቃ በኃላም በአትሌቲኮ ማድሪድ አሠልጣኝነት ሊቀጥል እንደሚችል ተናግሯል፡፡ (ቢን ስፖርት)

ብራዚላዊው የቼልሲ ክንፍ ተጫዋች ዊሊያን ለመጀመሪያ ጊዜ በጥቅምት ወር ስለሞቱት እናቱ ተናግሯል፡፡ (ለንደን ኢቪኒንግ ስታንዳርድ)

በመጨረሻም …

የብራዚሉ ቻፖኮንሴ ከዘግናኙ አደጋ በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሶስት ተጫዋቾች አስፈርሟል፡፡ (ሚረር)

ጆሴ ሞውሪንሆ ከቻይና ክለቦች በከፍተኛ ገንዘብ የአሰልጥንልን ጥያቄ ቢቀርብላቸውም ወደ ቻይና ሄዶ ለማሰልጠን እድሜያቸው ገና መሆኑንና የቻይና ክለቦችን ለመረከብ “በጣም ወጣት” መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ እንደ 53 ዓመቱ ፖርቹጋላዊ ከሆነ ከዚህ በኃላ በአውሮፓ ክለቦች ለመቆየት የሚያስችላቸው ብዙ አመታት ወደፊት እንዳሉዋቸው ተናግረዋል፡፡ 


“ከቻይና ክለቦች እየቀረበ ያለው ገንዘብ ማንንም የሚያጓጓ ነው፡፡ ነገር ግን እኔ የምፈልገው እግር ኳስን በከፍተኛ ደረጃ ማሰልጠን ነው::” ሲሉ ሞውሪንሆ ለስካይ ስፖርት ተናግረዋል፡፡ በሌላ በኩልም በቡድናቸው የመሰለፍ እድል እየሰጧቸው ላልሆኑ ተጫዋቾች ያላቸውን ሀዘኔታ ሞውሪንሆ ጨምረው ገልፀዋል፡፡ (ዘ ጋርዲያን)

             

Advertisements

ሚኪያስ በቀለ View All

ይህን ዘገባ ያቀረብኩላችሁ የኢትዮአዲስ ስፓርት ኤዲተርና ፀሀፊ እኔ ሚኪያስ በቀለ ነኝ።

%d bloggers like this: