Skip to content
Advertisements

የአርሰናል የ22 ዓመታት ክብረወሰን በሰንደርላንድ ይሰበር ይሆን? [ልዩ ዘገባ]

​በወንድወሰን ጥበቡ | ታህሳስ 13፣ 2009 ዓ.ም

ሰንደርላንድ ይህን የውድድር ዘመን በሙሉ ያሳለፈው በእጅጉ ተቸግሮ ነው። የጥቋቁር ድመቶቹ አብይ ችግር ደግሞ የቱ ጋር እንደሆነ ግልፅ ነው፤ ግቦችን የማስቆጠር።

ሰንደርላንድ በዚህ የውድድር ዘመን ዝቅተኛ ግብ ያስቆጠረ ክለብ ነው። ዋጋ ቢስ የሆኑት እነዚህ ጠቅላላ ግቦቹም በደረጃ ሰንጠረዡ ላይ የተቀመጡት ኸል ሲቲዎች 14 ብቻ ባያስቆጥሩ ኖሮ ዝቅተኛው ይሆን ነበር። 

ከዚህም በላይ ይህን ይበልጥ መጥፎ የሚያደርግበት ደግሞ አነዚህን ግቦችን እንማን እንዳስቆጠሩ ከተመለከትን ነው። በዚህ የውድድር ዘመን እስካሁን ሶስቱ የሰንደርላንድ ተጫዋቾች፣ ጀርሜድ ዴፎ፣ ቪክቶር አኒቼቤ እና ፓትሪክ ቫን አንሆልት ብቻ እነዚህን ጥቂት ግቦች በሙሉ ማስቆጠር ችለዋል።

Sunderland have scored 15 times in the Premier League - Jermain Defoe has eight of them

ሰንደርላንዶች በፕሪሚየር ሊጉ ያስቆጠሩት ግብ 15 ብቻ ነው – ከዚህም ስምንቱን ያስቆጠረው ጀርሜን ዴፎ ነው

እናም ብዙም በማያስደንቅ ሁኔታ በዚህ የውድድር ዘመን ከሁሉም ክለቦች ይህን ያህል ጥቂት ተጫዋቾች ግብ ያስቆጠሩበት ክለብ ሰንደርላንድ ነው።

ከ15ቱ ግቦችም አጥቂው አኒቼቤና የግራ ክንፍ ተከላካዩ ቫንሆልት ለየብቻ ሶስት ሶስት ግቦችን ሲያስቆጥሩ የዴፎ የግብ አስተዋፅኦ ከግማሽ በላይ ነው፤ ስምንት። አንዷ ቀሪ ግብ ደግሞ የተቆጠረችው የተቃራኒ ቡድን ተጫዋች በስህተት በራሱ መረብ ላይ ያሳረፋት ናት።

የዴቪድ ሞይሱ ቡድን በዋንጫ ጨዋታዎች ላይ ያስቆጠረውን ግቦች መቁጠር ከቻልን ደግሞ ተጨማሪ ግቦች ያስቆጠረው አምስት ብቻ ናቸው። ከእነዚህም ሶስቱ በሊግ ካፕ ጨዋታ ላይ በፓዲ ማክሌር የተቆጠሩ ሁለት ግቦችና በአድናን ያኑዛይ የተቆጠረ አንድ ግብ ናቸው። በዚያ ላይ በስታዲየም ኦፍ ላይት ላይ የግብ ማስቆጠር ከፍተኛ የግብ ድርቅ አለባቸው።

እስከሁን ባለው የ2016-17 የውድድር ዘመን የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች ምን ያህል ተጫዋቾቻቸው ግብ አስቆጥረዋቸዋል?

ቡድን የተለያዩ ግብ አስቆጣሪዎች ግብ አስቆጣሪ ተጫዋቾች
ማንችስተር ሲቲ 12 አጉዌሮ፣ ስተርሊንግ፣ ኖሊቶ፣ ጉንዶጋን፣ ኢሄናቾ፣ ደ ብሩይኔ፣ ቱሬ፣ ፈርናንዲንሆ፣ ሳኔ፣ ዛባሌታ፣ ኮላሮቭ፣ ሲልቫ
ቦርንማውዝ 11 ዊልሰን፣ አኬ፣ ስታኒስላስ፣ ጎስሊንግ፣ ኪንግ፣ ኩክ፣ ዳኒልስ፣ ስሚዝ፣ ፍሬዘር፣ አፎቤ፣ ፑፍ
በርንሌይ 11 ቮክስ፣ ሄንድሪክ፣ ባርነስ፣ ኬን፣ ቦይድ፣ ኤርፊልድ፣ ዋርድ፣  በርግ፣ ማርኔ፣ ደፎር
ሌስተር ሲቲ 11 ቫርዲ፣ ስሊማኒ፣ ማህሬዝ፣ ኦካዛኪ፣ ሙሳ፣ ፉክስ፣ ሞርጋን፣ ኪንግ፣ ኡሉዋ፣ ግሬይ፣ አማርተይ
ሊቨርፑል 11 ማኔ፣ ላላና፣ ኮቲንሆ፣ ፊርሚኖ፣ ሚልነር፣ ኦሪጊ፣ ቻን፣ ሎቭረን፣ ማቲፕ፣ ዊናልደም፣ ሄንደርሰ
ዋትፎርድ 11 ካፑ፣ ዲኒይ፣ ፔርይራ፣ ሆሌባስ፣ ኦካካ፣ ካባሰሊ፣ ኢግሃሎ፣ ያንማት፣ ፕሮድል፣ ሰክሰስ፣ ዙኒጋ
አርሰናል 10 ሳንቼዝ፣ ዋልኮት፣ ኦዚል፣ ዥሩ፣ ኮሸልኒ፣ ኦክስሌድ-ቻምበርሌን፣ ካዛሮላ፣ ዣካ፣ ኢዎቢ፣ ቻምበርስ
ቼልሲ 10 ኮስታ፣ ሃዛርድ፣ ፔድሮ፣ ሞሰስ፣ ዊሊያን፣ ባትሹኣዪ፣ አሎንሶ፣ ፋብሬጋስ፣ ካሂል፣ ካንቴ
ክሪስታል ፓላስ 10 ቤንቴኬ፣ ማክአርተር፣ ዛሃ፣ ቶምኪንስ፣ ዳን፣ ዊክሃም፣ ሌድሊ፣ ታውንሴንድ፣ ካባይ፣ ከምፕቤል
ቶተንሃም ሆትስፐርስ 9 ኬን፣ ሶን፣ ኤሪክሰን፣ ዴል፣ ሮዝ፣ ዋንያማ፣ ያንሰን፣ ላሜላ፣ ዊንክስ
ዌስት ብሮምዊች አልቢዮን 9 ሮንዶን፣ ቻድሊ፣ ፊሊፕስ፣ ማክአውሊ፣ ሞሪሰን፣ ብረንት፣ ፍሌቸር፣ ማክክሊን፣ ኤቫንስ
ኤቨርተን 8 ሉካኩ፣ ኮልማን፣ ባርክሌይ፣ ባሪ፣ ቦላሲ፣ ሚራለስ፣ ቤንስ፣ ዊሊያምስ
ኸል ሲቲ 8 ስኖድግራስ፣ ዲዮማንዴ፣ ዳውሰን፣ ሜይለር፣ ሊቨርሞር፣ ኸርናንዴዝ፣ ማሰን፣ ማሎኒ
ማንችስተር ዩናይትድ 8 ኢብራሂሞቪች፣ ራሽፎርድ፣ ፖግባ፣ ማታ፣ ማታ፣ ሩኒ፣ ሚክሂታሪያን፣ ስሞሊንግ፣ ማርሻል
ስቶክ ሲቲ 8 አለን፣ ቦያን፣ ሻኪሪ፣ ቦኔ፣ ዋልተርስ፣ አርናቶቪች፣ ሙኒሳ፣ አዳም
ዌስት ሃም ዩናይትድ 8 አንቶኒዮ፣ ላንዚኒ፣ ፓየ፣ ኖብል፣ ሳኮ፣ ኮሊንስ፣ ካሮል፣ ሪድ
ሚድልስብሮ 7 ኔግሬዶ፣ ስቱዋኒ፣ ራሚረዝ፣ ደ ሩን፣ ዳውኒንግ፣ ጊብሰን፣ አያላ
ሳውዛምፕተን 7 ኦስቲን፣ ሮድሪጌዝ፣ ሬድሞንድ፣ ታዲች፣ ቡፋል፣ በርትራንድ፣ ዋርድ-ፕሮውስ
ስዋንሲ ሲቲ 6 ፈር፣ ሎረንቴ፣ ሲጉርድሰን፣ ሮትሎጅ፣ ቫር ደር ሁርን፣ ባስቶን
ሰንደርላንድ 3 ዴፎ፣ ቫን አንሆልት፣ አኒቼቤ

የዴቪድ ሞየሱ ቡድን ከ1993-94 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዘመን አንስቶ እስካሁን የቆየና በእጅጉ እንዲሆን የማይሹትን የሊግ ክብረወሰን የመስበር አደጋ ውስጥ ይገኛል።

በዚያ የውድድር ዘመን ይህን ስድስት ተጫዋቾች ብቻ ግብ በማስቆጠር ክብረወሰን ይዞ ያጠናቀቀው አርሰናል ነበር። ይሁን እንጂ የዚያን ወቅቱ የጆርጅ ግራህም ቡድን ይህ ዝቅተኛ ክብረወሰን በውድድር ዘመኑ በአራተኝነት ከመጨረስና በአውሮፓ ውድድር ላይ ከመሳተፍ አላገደውም።

በውድድር ዘመኑ አርሰናል ካስቆጠራቸው 39 ግቦች 23ቱን አጥቂው ኢያን ራይት በማስቆጠሩ ምክኒያት ሌሎች ግቦችን ለሌሎች ተጫዋቾች ለማከፋፈል አላስፈለገውም።

Thanks to Ian Wright (left), Arsenal finished fourth in 1993/94 with only six goalscorers

ምስጋና ለኢያን ራይት (በግራ በኩል የሚታየው) ይሁንና አርሰናል 1993-94 የውድድር ዘመን የጠናቀቀው በስድስት ግብ አስቆጣሪዎዥ ብቻ ነበር

በወቅቱ ፓል ማርሰን፣ አለን ስሚዝ፣ ሬይ ፓርለር እና ስቲቭ ቦልድ ብቻ ነበሩ ተጨማሪዎቹ ግብ አስቆጣሪ ዝርዝር ውስጥ መካተት የቻሉት ተጫዋቾች።

ከዚያ በኋላ ይህን የፕሪሚየር ሊግ ዝቅተኛ ግብ አስቆጣሪ ተጫዋቾች ቁጥር  ክብረውሰን ለመስበር ተቃርበው የነበሩት ፉልሃም (በ2001-02) እና በርንሌይ (በ2014-15) ናቸው። ሁለቱም ክለቦች ግብ ያስቆጠሩላቸው ሰባት ሰባት ተጫዋቾች ብቻ ነበሩ። 

2014-15 የውድድር ዘመን በርንሌይ ወደታችኛው ዲቪዚዮን ወርዷል። እናም የ34 ዓመቱ ዴፎ ከአሁኑ አንስቶ እስከውድድር ዘመኑ መጨረሻ ድረስ ባለው ጊዜ ተጨማሪ 20 ግቦችን ማስቆጠር እስካልቻለ ድረስ ሰንደርላንድ የሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎን ከማግኘት ይልቅ የበርንሌይ ዓይነት ተመሳሳይ ዕጣ ፈንታ ሊገጥመው ይችላል።

Danny Ings' 11 goals for Burnley in 2014-15 were not adequately backed up by his team mates

በ2014-15 የውድድር ዘመን ዳኒ ኢንግስ ያስቆጠራቸው 11 ግቦች በርንሌይን ከመውረድ አልታደገውም

የትኛው የፕሪሚየር ሊግ ክለብ ዝቅተኛ የግብ አስቆጣሪ ተጫዋች ቁጥር አለው?

6 – አርሰናል፣ 1993-1994

7 – ፉልሃም፣ 2001-02፤ በርንሌይ 2014-15 

8 – ተንሃም ሆትስፐርስ፣ 1994-95 እና 1995-96፣ ኮንቨንትሪ ሲቲ፣ 1996-97፤ ዊምብልደን፣ 1998-99፤ ዌስት ሃም ዩናይትድ 2002-03፤ ዋትፎርድ፣ 2015-16 

በዚህ የውድድር ዘመን ከሰንደርላንድ ሶስት ዝቅተኛ ግብ አስቆጣሪዎች ቀጥሎ ሌላው በወራጅ ቀጠና ላይ የሚገኘው ስዋንሲ ሲቲ በስድስት ተጫዋቾቹ ይከተላል።

ይሁን እንጂ አዲሱ አዳጊ የፕሪሚየር ሊግ ክለብ ከሆነው ሚድልስቦሮ ጋር ሳውዛምፕተን በውድድር ዘመኑ 17 ግቦችን ብቻ ቢያስቆጥሩም ሰባት ሰባት የተለያዩ ግብ አስቆጣሪ ተጫዋቾች አሏቸው። ሆኖም ስድስት ግቦችን ያስቆጠረው የሳውዛምፕተኑ አጥቂ ቻርሊ ኦስቲን የረጅም ጊዜ ጉዳት ገጥሞታል።

Only seven players have scored for Southampton this season, including Charlie Austin (left)

በዚህ የውድድር ዘመን ለሳውዛምፕተን ግብ ያቆጠሩት ቻርሊ ኦስቲንን ጨምሮ ሰባት ተጫዋቾች ብቻ ናቸው

ሙሉ በሙሉ በ34 ዓመቱ ዴፎ ሃሳቡን የጣለው የዴቪድ ሞየሱ ቡድን በፕሪሚየር ሊጉ ለመዝለቅ በአንድ ተጫዋች ላይ ብቻ መደገፍ አይችልም።

ዴቪድ ሞየስ በጥር ወር ምንም የዝውውር ወጪ የማያደርግ ከሆነ ግብ የማስቆጠር ጫናውን የሚጋራ ተጫዋች ለማግኘት ሲል  ፊቱን አኒቼቤን ወዳገኘበት የነፃ ዝውውር ገበያው ሊያዞርም ይችላል። 

Every Sunderland goalscorer in the Premier League this season is in this one photograph 

የዚህ የውድድር ዘመን ሶስቱ የሰንደርላንድ ግብ አስቆጣሪ ተጫዋቾች
Advertisements
%d bloggers like this: