Skip to content
Advertisements

የባርሴሎና የ2017-18 የውድድር ዘመን መለያ ይፋ ባልሆነ መንገድ አፈትልኮ ወጣ

​በወንድወሰን ጥበቡ | ማክሰኞ ታህሳስ 18፣ 2009


የባርሴሎና እግር ኳስ ቡድን ተጫዋቾች በ2017-18  የውድድር ዘመን ለብሰው የሚጫወቱበት መለያ ምስል ይፋዊ ባልሆነ መንገድ አፈትልኮ ወጥቷል። 
ከታች ያለው የአዲሱ መለያ ምስል እንደሚያመለክተው በፊት ለፊት በኩል ቀድሞ የመለያው ስፖንሰር የነበረው የኳታር አየር መንገድ በአዲሱ መለያ ከክለቡ ጋር የአለማችንን ትልቁን የስፖንሰርሺፕ ስምምነት የፈፀመውና ከሚቀጥለው የውድድር ዘመን አንስቶ እስከ 2021-22 ድረስ ስምምነቱ የሚዘልቀው የጃፓኑ የኤሌክትሮኒክስ ግብይትና የኢንተርኔት ኩባንያ የሆነው ራኩተን ተተክቷል። 

የመጀመሪያው መለያ ተለምዷዊውን የባርሴሎና ቀይና ሰማያዊ ቀለምን የያዘ ሲሆን፣ የቀለማቱ ቋሚ መስመር ግን በፊት ለፊት በኩል ያልተለመደ አሰፋፈር አለው።

ሁለተኛው መለያ ሙሉ ለሙሉ ውሃ ሰማያዊ ቀለም ያለው ሲሆን ሶስተኛው መለያ ግን ሙሉ ቀይቡኒ ሆኖ በአንገትጌው፣ በእጅጌውና በቁምጣው ግራና ቀኝ ቁልቁል በመስመር የሚቀርድ ቀይ ቀለማት የሰፈሩበት የጣሊያኑን ሮማ መለያ የሚመሳሰልና ለካታሎኑ ክለብ ጨርሶ አዲስ የሆነ ቀለም ነው።

የባርሴሎናን ሶስተኛ መለያ ከጣሊያኑ ክለብ ሮማ ተመሳሳይ ነው
ይፋዊ ባልሆነ መንገድ የወጡት የባርሴሎና አዲሶቹ የ2017-18 የውድድር ዘመን መለያዎች

Categories

ባርሴሎና

Advertisements
%d bloggers like this: