የተረጋገጠ: – ስዋንሲ ቦብ ብራድሌን አባረረ

By Eyob Dadi ታህሳስ 18 ቀን 2009 ዓም


ስዋንሲ ከቡድኑ አሰልጣኝ አሜሪካዊው ቦብ ብራድሌ ጋር የነበረውን ኮንትራት ከሁለት ወራት በኋላ ቀደደ።

ብራድሌ ባለፈው ጥቅምት ወር ላይ የቡድኑ አሰልጣኝ ሆነው ቢሾሙም የቡድኑን አቋም ለማሻሻል ከብዷቸዋል።

11 ጨዋታ ተጫውተው 7 ጊዜ በመሸነፋቸው ቡድኑ በቀጣዩ አመት በሊጉ ላይ መቆየቱ አጠራጣሪ ሆኗል።

የዌልሱ ተወካይ በዌስትሀም 4 – 1 ከተሸነፈ በኋላም በ 3 ተከታታይ ጨዋታዎች ላይ በመሸነፍ አስከፊ ጉዞውን ቀጥሎበታል።

የቡድኑ ሊቀመንበር በመግለጫቸው ሲናገሩ

“ከአጭር ጊዜ በኋላ ቦብ ብራድሌን ማጣታችን አዝነናል፣ያለመታደል ሆኖ ነገሮች በታቀደላቸው መንገድ አልተጓዙም

“ስለዚህ ግማሽ ጨዋታ በቀረው የፕሪምየርሊግ ጨዋታ ላይ አሰልጣኝ ለመቀየር ወስነናል

“በዚህ በአስቸጋሪ ወቅት ከችግር የሚያወጣንን መፍትሄ መፈለግ እና መሞከር ይኖርብናል

“በግሌ አሰልጣኙን አደንቀዋለው፣ለቡድኑ ብዙ ነገር የሰጠ ጥሩ ሰው ነው፣ወደፊትም መልካም እንዲገጥመው እንመኛለን።” ሲሉ ተናግረዋል።

ቦብ ብራድሌ ወደ ስዋንሲ ከማምራታቸው በፊት በፈረንሳይ ሁለተኛ ዲቪዝየን የሚገኘው ሊ ሀቭሬ ሲያሰለጥኑ ቆይተዋል።

Advertisements