Skip to content
Advertisements

“ሁላችንም ተስፋ ቆርጠናል” – አርሰን ቬንገር

በሚኪያስ በ. ወርዶፋ| ሀሙስ ታህሳስ 27, 2009

በማክሰኞው ምሽት ጨዋታ መድፈኞቹ በበርንማውዝ ከ 3-0 መመራት ተነስተው ጨዋታውን 3-3 በሆነ አቻ ውጤት ቢጨርሱም ቺሊያዊው የቡድኑ አጥቂ ከፍተኛ ንዴትና ተስፋ መቁረጥ ውስጥ ገብቶ ታይቷል። 

አሌክሲስ ቡድኑ በጨዋታው ላይ ነጥብ በመጣሉ ንዴት ውስጥ እንደገባና ከጨዋታው በኃላም በመልበሻ ቤት ውስጥ የቡድን አጋሮቹን በጠንካራ የትችት ቃላት እየተናገረ ሲበሳጭ መታየቱን የእንግሊዝ ሚዲያዎች እየተቀባበሉ እያወሩት ይገኛል።

በተጫዋቹ ሰሞነኛ ባህሪ ዙሪያ ከጋዜጠኞች ጥያቄ የቀረበላቸው አርሰን ቬንገርም “ምንድነው የሚያስደንቀው ነገር? ጨዋታዎችን ማሸነፍ እንፈልጋለን። ካላሸነፍክ ደስተኛ አትሆንም። ይህ የተለመደ ነገር ነው። 

እስከ 70 ኛው ደቂቃ 3-0 እየተመራህ ስሜት   ከሌለህና በስሜት ካልተጫወትክ ማገገም አትችልም። አሌክሲስ ብቻ ሳይሆን ሁላችንም በወቅቱ ተስፋ ቆርጠናል። ግን ሁሉም ነገር ጥሩ ሁኔታ ላይ ነው።” ሲሉ መልስ ሰጥተዋል።

የቀድሞው የባርሴሎና ተጫዋች ሳንቼዝ በአሁኑ ወቅት ከክለቡ ጋር በኮንትራት ማራዘም ዙሪያ ውዝግብ ላይ ይገኛል። በክለቡ 180,000 ፓውንድ ሳምንታዊ ደሞዝ የሚያስገኝ አዲስ ስምምነት ቢቀርብለትም ቺሊያዊው አጥቂ ግን 250,000 ፓውንድ እንዲቀርብለትና አርሰናል ከትልልቅ ክለቦች ጋር መወዳደር የሚችል መሆኑን ማረጋገጥ ፈልጓል።

እየወጡ እንዳሉ ሪፓርቶች ከሆነም የፈረንሳዩ ታላቅ ክለብ ፒኤስጂ፣ የጣሊያኑ ኢንተርና የቻይና ሱፐር ሊግ ክለቦች ለተጫዋቹ ከፍተኛ ደሞዝ አቅርበውለታል። የስፔን የዜና ወኪል የሆነው ዶንባሎን እንዳለውም ከሁሉም ፈላጊ ክለቦቹ ጋር ግንኙነት እንዳረገና የመድፈኞቹ ቤት ቆይታው በአየር ላይ እንዳለ አውርቷል።

በሌላ በኩል የእንግሊዙ ዘ ሰን እንዳወራው ከሆነ መድፈኞቹ በዘንድሮው የውድድር ዘመን እናሳካዋለን ብለው የሚያስቡት የኤፍኤካፕ ዋንጫ ብቻ መሆኑን ገልፆ ቅዳሜ ለሶስተኛው ዙር የኤፍኤካፕ ጨዋታ ወደ ፕሪስተን የሚያመሩትም ካለፋት ሶስት አመታት ሁለቱን የውድድሩ አሸናፊ መሆናቸውን እያሰቡ ለሶስተኛ ጊዜ ድል ለማድረግ እያሰቡ መሆኑን ፅፏል። 
ቬንገርም “ለእኛ ዋንጫው ተቀዳሚ ኢላማችን ነው። በታሪክ ውስጥም ትኩረት እንሰጠው እንደነበር ይፃፍልናል። ውድድሩ ለሁሉም ቡድን ከባድ ፉክክር ያለበት ነው።” ሲሉ ነግረውኛል ብሎ ጋዜጣው ጨምሮ ፅፏል።

Advertisements

ሚኪያስ በቀለ View All

ይህን ዘገባ ያቀረብኩላችሁ የኢትዮአዲስ ስፓርት ኤዲተርና ፀሀፊ እኔ ሚኪያስ በቀለ ነኝ።

%d bloggers like this: