Skip to content
Advertisements

 ያፕ ስታም የሬዲንግ አሰልጣኝ ሆኖ የቀድሙ ክለቡን ለመግጠም ቅዳሜ ኦልድ ትራፎርድ ይመለሳል

ዘውዱ በሬሳ | ታህሳስ 27, 2009


የሶስትዮሽ የዋንጫ ድልን ያሳካው የ 1999ኙ የአለክስ ፈርጉሰን ስብስብ አባል የነበረውና ከዚያም ወደጣልያን በማምራት ለላዚዮና ኤሲ ሚላን መጫወት የቻለው የጠንካራው ሆላንዳዊ ተከላካይ በኤፍ ኤ ዋንጫ ቀያይ ሰይጣኖቹን ለመግጠም ወደኦልድ ትራፎርድ ይመለሳል፡፡ 

ሬዴንግን ማሰልጠን ከጀመረ አንስቶ ቡድኑን በመልካም ጎዳና ላይ እየመራው የሚገኘው ስታም ለዩናይትድ እጅግ ከፍተኛ ክብር እንዳለው ቢናገርም ብዙ ግምት ላልተሰጣቸው ሬዲንጎች ማንነታቸውን ማሳየት የሚችሉበት አሪፍ አጋጣሚ የሚሆንላቸው ጨዋታ እንደሚሆን ሀሳቡን ሰጥቷል፡፡

ለጆዜ ሞሪንሆ አድናቆት እንዳለው የተናገረው ስታም “ጆዜ ከታላላቆቹ የአለማችን አሰልጣኞች አንዱ ነው፡፡ በዩናይትድ ቤት የመጀመሪያ ጊዜያት ቢቸገርም በሂደት የለመደውን አሸናፊ ቡድን መገንባት ችሏል ፤ ከዛ በላይ ደግሞ ዝላታን ኢብራሂሞቪችን ጨምሮ እጅግ በላቀ ክህሎት የተሞላ ስብስብ አለው” ሲል የቀድሞ ክለቡንና ጆዜን አሞካሽቷል፡፡

ስታም በ1999 የሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ

ማንችስተር ዩናይትድና ሬዴንግ የሚያደርጉት የኤፍ ኤ ዋንጫ ጨዋታ የፊታችን ቅዳሜ እንደሚደረግ ይታወቃል፡፡

Advertisements
%d bloggers like this: