Skip to content
Advertisements

አጫጭር ወሬዎች: የቅዳሜ አመሻሽ የአውሮፓ ጋዜጦች የዝውውርና ሌሎች አዝናኝና አጓጊ ወሬዎች

በሚኪያስ በ. ወርዶፋ| ቅዳሜ ታህሳስ 29, 2009

ቶትነሀም በዊልፍሬድ ዘሀ ዙሪያ ያለውን ፍላጎት ያቋረጠ ሲሆን በመጪው ክረምት ግን መልሶ ተጫዋቹን ለማስፈረም ዳግም እንደሚንቀሳቀስ ታወቀ። (ዘ ሰን)

ሲቲና ሊቨርፑል በጥብቅ የሚፈልጉት የሳውዝአምፕተኑ ተከላካይ ቨርጂል ቫንዲጂክ እንደማይሸጥ በክለቡ ተነግሯቸዋል። (ዴይሊ ስታር)

አርሰን ቬንገር በያዝነው የጥር የዝውውር መስኮት ምንም አይነት ዝውውር እንደማያካሂዱና ይልቅ የአሌክሲስ ሳንቼዝ፣ ሜሶት ኦዚል፣ ኦሊቨር ዥሩና ፍራንሲስ ኮክለንን የኮንትራት ማራዘም ለማጠናቀቅ እንደሚሰሩ ታወቀ። (ዘ ሰን)
ነገር ግን አሌክሲስ ሳንቼዝን በመጪው ክረምት 60 ሚሊዮን ፓውንድ በማቅረብ ለማስፈረም ፒኤስጂዎች የተጫዋቹና የአርሰናል የኮንትራት ማራዘም ውዝግብ በቶሎ እንዳይፈታና እንዲቀጥል እየሰሩ ይገኛል። (ዴይሊ ሚረር)

የሲቲው አለቃ ፔፔ ጋርዲዮላ የ 27 አመቱን ተከላካይ ባድስቱበርን በስድስት ወራት የውሰት ውል ወደ ኢትሀድ ለማምጣት እንደሚጥር ታውቋል።(ዘ ሰን)

የቶትነሀሞቹን ዴል አሊና ሀሪ ኬንን፣ የኤቨርተኑን ሮዝ ባርክሌይን እና የሊቨርፑሉን ዳንኤል ስቱሪጅ ለመውሰድ ተቀዳሚ ምርጫ ውስጥ ያስገባው የቻይናው ሱፐር ሊግ ከፍተኛ የሆነ ሳምንታዊ 800,000 ፓውንድ ደሞዝ ለእነዚህ ኮከቦች ለማቅረብ ተዘጋጅቷል። (ዴይሊ ሜይል)

ኤቨርተን የተሻሻለ አዲስ የ 22 ሚሊዮን ፓውንድ ጥያቄ ለዩናይትዱ የ 27 አመት አማካኝ ሞርጋን ሽንደርሊን ለማቅረብ አስቧል። (ስኳውክ)

ሳውዝአምፕተኖች ተከላካያቸው ጆሴ ፎንቴ የቀረበለትን የዝውውር ጥያቄ በመቀበሉ የሊቨርፑሉን የ 26 አመት ተከላካይ ለማስፈረም እንደሚጥሩ ታወቀ። (ሌኪፕ ዴይሊ ስታርን ጠቅሶ እንደፃፈው)  

ሙሳ ዴምቤሌ ለዝውውሩ ከዌስትሀም 20 ሚሊዮን ፓውንድ ቢቀርብለትም ሴልቲክን መልቀቅ አልፈለገም። (ዴይሊ ሜይል)

የጁቬንቱስ ግራ ተከላካይ ፓትሪስ ኤቭራ የቀድሞ ክለቡን ዳግም ሊቀላቀል የሚችል ሲሆን ነገር ግን ዩናይትድን የሚቀላቀለው በተጫዋችነት ሳይሆን በአሰልጣኝነት ብቻ ነው። (ጋዜጣ ዴሎስፓርት)

ቼልሲና ሲቲ የቀድሞውን የስቶክ አማካኝ ስቴቨን ንዞንዚን ማስፈረም ፈልገዋል። ለስፔኑ ሲቪላ እየተጫወተ የሚገኘው የ 28 አመቱ አማካኝ የ 25 ሚሊዮን ፓውንድ ውል ማፍረሻ ሂሳብ ሲኖረው ጁቬንቱስም ከፈላጊ ክለቦቹ አንዱ ነው። (ሌኪፕ ዴይሊ ስታርን ጠቅሶ እንደፃፈው) 

በመጪው ክረምት የአርሰናል ቤት የኮንትራት ጊዜያቸው የሚጠናቀቀው መድፈኞቹ ፔር ሜርትሳከርና ሳንቲ ካዞርላ የ 12 ወራት አዲስ የኮንትራት ማራዘሚያ ስምምነት ቀርቦላቸዋል። (ታይምስ)

ሆላንዳዊው የቀያየቹ ሴይጣኖች ተከላካይ ሜንሳ በያዝነው የጥር የዝውውር መስኮት በውሰት ክለቡን መልቀቅ እንደማይችል ተነግሮታል። (ማንችስተር ኢቭኒንግ ኒውስ)

ቼልሲ የ 31 አመቱን የስዋንሲ አጥቂ ፈርናንዶ ሎረንቴን በዚህ በጥር የዝውውር መስኮት ለማስፈረም እራሱን እያዘጋጀ ነው። (ስካይ ስፓርትን ጠቅሶ ቶክ ስፓርት እንደፃፈው) 

ነገር ግን ቼልሲዎች ገና በስፔናዊው አጥቂ ዝውውር ዙሪያ ከስዋንሲ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት አላደረጉም። (ሳውዝ ዌልስ ኢቭኒንግ ኒውስ)

የ23 አመቱ የጁቬንቱስና አርጀንቲና አጥቂ ፓውሎ ዳይባላ ከባርሴሎና ይልቅ ወደ ማድሪድ መዘዋወርን መርጧል። (ማርካ)

የማንችስተርና ኤሲሚላን የዝውውር ኢላማ የሆነው የ 21 አመቱ ሴኔጋላዊ አጥቂ ኬይታ ባልዴ ዲዮ በያዝነው ጥር ላዚዮን አይለቅም። (ካልቺዮ መርካቶ)

በመጨረሻም …

የዌስትሀሙ ምክትል ፕሬዝዳንት ኬረን ብራዲ የክለባቸውን ውስጣዊ ጉዳይ የሚያወራው የክለቡ ድህረገፅ የጭምጭምታ አምድ እንዲወገድ መልዕክት አስተላልፈዋል። የመዶሻዎቹ ሀላፊ ይህን የተናገሩት ክለባቸው ለሴልቲኩ ሙሳ ዴምቤሌ ያቀረበው የ 20 ሚሊዮን ፓውንድ የዝውውር ጥያቄ ውድቅ ስለመደረጉ ፍንጭ ከሰጠ በኃላ መሆኑ ታውቋል።  (ስኳውክ)

ጆሴ ሞውሪንሆ ለ 14 ተከታታይ ጨዋታ (የዛሬውን የሬዲንግ ድል ጨምሮ) ቡድናቸው በድል ቢጓዝም ገና የሚፈለገው ደረጃ ላይ እንዳልተደረስ ተናገሩ። (ጋርዲያን)

Advertisements

ሚኪያስ በቀለ View All

ይህን ዘገባ ያቀረብኩላችሁ የኢትዮአዲስ ስፓርት ኤዲተርና ፀሀፊ እኔ ሚኪያስ በቀለ ነኝ።

%d bloggers like this: