Skip to content
Advertisements

ቡርኪናፋሶ – የስብስቡ አባላት፣ የውድድሩ ተሳትፎ ታሪክ፣ በውድድሩ የሚጠበቅባት ስኬት እና ሌሎች መረጃዎች

በሚኪያስ በ. ወርዶፋ | ማክሰኞ ጥር 2፣ 2009 ዓ.ም

ቡርኪናፋሶ በእግር ኳስ ታሪኳ ላትታወቅ ትችል ይሆናል፡፡ ነገር ግን ወደብ አልባዋ ሀገር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወደ እግር ኳሱ መድረክ ብቅ ማለት ጀምራለች፡፡ በጣም ትልቅና ያማረ ስኬትንም አሳይታናለች፡፡ በዚህ ውድድር ላይ ምንም እንኳን ለቡርኪናፋሶዎች ዋንጫ ማግኘት (ያለፈው ውድድር የፍፃሜ ተፋላሚ ነበሩ) እንደ ሰማይ ሩቅ ቢሆንም በውድድሩ መሳተፍ እራሱ ትልቅ ደስታቸው ነው፡፡ እግር ኳስ በቡርኪናፋሶ ተወዳጅ ስፖርት ነው፡፡ በፕሮፌሽናልም ሆነ በተለምዶ በመላ አገሪቱ እግር ኳስ ከዳር እስከ ዳር የተንሰራፋ የስፖርት አይነት ነው፡፡ 
 

የቡርኪናፋሶ ወሳኝ ተጫዋቾች እነማን ናቸው?

1. ቻርለስ ካቦሬ፣ የተከላካይ አማካኝ፣ ኤፍሲ ክራስኖዳር (ሩሲያ)

በአሁኑ ሰአት የመሸጫ ዋጋው 6 ሚሊዮን ፓውንድ የደረሰው ኮባሬ እስካሁን 70 ኢንተርናሽናል ጨዋታዎችን ማድረግ ችሏል፡፡ 

2. ፕሪጁስ ኒጉሁዊቤ ናኩልማ፣ የክንፍ ተጫዋች፣ ካይዘርስፖር (ቱርክ)
ናኩልማ ትልቅና በኃይል የተሞላ በክንፍም ሆነ በአጥቂ ቦታ ላይ መሰለፍ የሚችል ተጫዋች ነው፡፡ ለሀገሩም በ32 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ 6 ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል፡፡ 

3. ቤርትራንድ ትራኦሬ፣ አጥቂ፣ አያክስ (ከቼልሲ በውሰት)

ትራኦሬ ከ 15 አመቱ ጀምሮ አለም አቀፍ ተጫዋች መሆን የቻለና ሀገሩን ባለፉት ሁለት የአፍሪካ ዋንጫዎች ለመወከል የበቃ ነው፡፡ ባሳለፍነው አመትም በክለቡ ቼልሲ በአምስት ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ አራት ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል፡፡ ነገር ግን እነዚህ ጎሎች በስታምፎርድ ብሪጅ ለመቆየት ዋስትና ሊሆኑት ሳይችሉ ቀርተው በውሰት በሆላንዱ አያክስ ይገኛል፡፡ 

የቡርኪናፋሶ አፍሪካ ዋንጫ ተጫዋቾች ስብስብ

በረኞች፡ ጀርሜን ሳኑ (ቢሆቪያስ/ፈረንሳይ)፣ ሀርቬ ኮፊ (ኤስኢሲ አቢጃን/ኮትዲቩዋር)፣ አቡበከር ሳዋዶጎ (አርሲ ካዲዮጎ)

ተከላካዮች፡ ባካሪ ኮኔ (ማላጋ/ስፔን)፣ እርነስት ኮንጎ (አይዜድኬ ኬምሴት/ሞሮኮ)፣ ኢሱፍ ፓሮ (ሳንቶስ/ደቡብ አፍሪካ)፣ ፓትሪክ ማሎ (ስሞሀ/ግብፅ)፣ ኢሱፍ ዳዮ (ሬሲንግ ክለብ በርካኔ/ሞሮኮ)፣ ያኮብ ኩሊባሊ (አርሲቢ/ቡርኪናፋሶ) እና ስቴቭ ያጎ (ቱሉዝ/ፈረንሳይ)

አማካኞች፡ ባካሪ ሳሬ ዲት ቦባ (ሞሪነርዜ/ፓርቹጋል)፣ አብዱ ራዛቅ ትራኦሬ (ካራቡዝፑር/ቱርክ)፣ ብላቲ ቱሬ (ኦሞኒያ ኒኮሲያ/ ቆፕሮስ)፣ አዳማ ጉዬራ (አርሲ ሌንስ/ፈረንሳይ)፣ ቻርለስ ካቦሬ (ክራስኖዳር/ሩሲያ)፣ አሌይን ትራኦሬ (ካይሰርስፑር/ቱርክ) እና ሳይሪሌ ባያላ (ሼሪፍ ትራስፖል/ሞልዶቪያ)

አጥቂዎች፡ ጆናታን ፒትሮፒያ (አልናስር/ሳውዲ አረቢያ)፣ ፕሪጁስ ናኩልማ (ካይዘርስፖር/ቱርክ)፣ አርስቲዴ ባንሴ (ኤኤስኢሲ/ኮትዲቩዋር)፣ ጆናታን ዞንጎ (አልሜሪያ/ፈረንሳይ)፣ ቤርትራንድ ትራኦሬ (አያክስ/ሆላንድ)፣ ባኑ ዲያዋራ (ስሙሀ ክለብ/ግብፅ) እና ኢሱማሊ ሊንጋኒ (ሀፖል አሽሎን/እስራኤል)

ቡርኪናፋሶ እንዴት ለውድድሩ ለማለፍ በቃች?

ቡርኪናፋሶ በማጣሪያው ከስድስት ጨዋታዎች አራቱን በማሸነፍ ከኡጋንዳ ጋር አንገት ለአንገት ተናንቃ በአንደኝነት ለጋቦኑ ውድድር መብቃት ችላለች፡፡ ምስጋና ለጆናታን ፒትሮፒያ ግብ ይግባና በሜዳቸው ኡጋንዳን 1-0 መርታት ችለዋል፡፡ ከሜዳቸው ውጪ በነበረው ግጥሚያ ደግሞ 0-0 በሆነ የአቻ ውጤት ጨዋታውን ጨርሰዋል።

የቡርኪናፋሶ አሰልጣኝ ማን ናቸው?

ፓውሎ ጆርጌ ሬቤሎ ዱራቴ የቀድሞ የፖርቹጋል የመሀል ተከላካይ ሲሆኑ በ 18 አመት የተጫዋችነት ዘመናቸው በዩኒያኦዲ ሊይሪያ ክለብ ለ12 አመታት የቆዩ ሲሆን በ238 ጨዋታዎችም ላይ መሰለፍ ችለዋል፡፡ ቡርኪናፋሶን ለማሰልጠን በ 2014 ወደ ብሄራዊ ቡድኑ ከመምጣታቸው በፊትም ክለቡን ማሰልጠን ችለዋል፡፡ 

የቡርኪናፋሶ የአፍሪካ ዋንጫ ታሪክ ምን ይመስላል?

ቡርኪናፋሶዎች በ1998 ባዘጋጁት የአፍሪካ ዋንጫ በአራተኛነት ማጠናቀቅ ችለው ነበር፡፡ የአፍሪካ ዋንጫ ትልቁ ውጤታቸውም በ2013 የፍፃሜ ግጥሚያ በናይጄሪያ የተረቱበት ነው፡፡  

በውድድሩ ላይ ከቡርኪናፋሶ ምን ይጠበቃል? 

ቤርትራንድ ትራኦሬ ባሳለፍነው የውድድር ዘመን በቼልሲ ቤት ዲያጎ ኮስታን በልጦ መሰለፍ የቻለ ነበር፡፡ በዚህ ውድድር ላይም የቡርኪናፋሶ እድል ተደርጎ ተወስዷል፡፡ በእውነትም ቡርኪናፋሶዎች ከምድቡ ለማለፍ ከተቀናቃኞቻቸው የተሻለ ውጤት እንደሚያስመዘግቡም ይጠበቃል፡፡
 

Advertisements
%d bloggers like this: