Skip to content
Advertisements

አነጋጋሪ ውሳኔ: በአለም ዋንጫ 48 ቡድኖችን የማሳተፍ እቅድ እንዴት ሊተገበር ይችላል? 

በሚኪያስ በ. ወርዶፋ | ማክሰኞ ጥር 2፣ 2009


አለም ዋንጫን ምን ገጠመው?

አዎ ቀጣዮቹ ሁለት የአለም ዋንጫዎች በተጠበቀው መልኩ ከዚህ ቀደም እንደነበረው 32 ቡድኖችን ይዘው የሚካሄዱ ይሆናል። ከዛ በኃላ ግን በተሳታፈዎች ቁጥር እድገት አለም ዋንጫው በጨዋታ ብዛት ታምቆ የሚቀጥል ይሆናል።  

የተሳታፊዎች ቁጥር እደገቱምን ያህል ትልቅ ነው?

50 በመቶ። በ2026 አለም ዋንጫ 48 ቡድኖች የሚሳተፉ ሲሆን 64 የነበረው የጨዋታ ብዛትም ወደ 80 የሚያድግ ይሆናል።  

ይህ ግን ትልቅ ቁጥር ነውን? 

አዎ በእርግጠኝነት ትልቅ ነው። የመጀመሪያው አለም ዋንጫ 13 ቡድኖችን ብቻ ነበር ያሳተፈው። ነገር እግር ኳስ ከዛ በኋላ ትልቅ እድገት አስመዝግቧል። በአሁኑ ወቅት ያሉት የፊፋ አባል ሀገራት ቁጥርም 211 ደርሷል። ፊፋ ይህንን አዲሱን የተሳታፊ ሀገሮች ቁጥር እድገት ውሳኔ ያመጣውም የእግር ኳስ ደረጃቸው አነስተኛ የሆኑትን እንደ ቻይናና ህንድ ያሉትን ሀገሮች ተሳትፎ በማረጋገጥ አለም ዋንጫውን ለማድመቅ መሆኑን ገልጿል።  

ግን ጥሩ አካሄድ ነው?
አይደለም እንዴ ?

ስለዚህ ውሳኔው ከገንዘብ ጋር የተገናኘ ነገር የለውም?

በእርግጥ ፊፋ ውድድሩን በማስፋት 1 ቢሊዮን ዶላር (823 ሚሊዮን ፓውንድ) ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት አቅዷል። ነገር ግን የተቋሙን ትክክለኛ ያልሆነ የገንዘብ ዝውውር አካሄድ ለተገነዘበ ሰው ከውድድሩ ተሳታፊ ሀገሮች ቁጥር መጨመር ጀርባ ስላለው ምክንያት ማወቁ አስፈላጊ ነገር አይደለም።  

እቅዱ እንዴት ሊተገበር ይችላል? 

አዲሱ የፊፋ ውሳኔ የምድብ ድልድሉን በፊት ከነበረው በመቀየር ሶስት ቡድኖችን በያዙ 16 ምድቦች ይተካዋል። ከዛም እርስ በርስ በሚያደርጉት ግጥሚያ ከእያንዳንዱ ምድብ አንደኛና ሁለተኛ ሆነው የሚጨርሱት ቡድኖች 32 ቡድኖችን ወደሚያፋልመው የጥሎ ማለፍ ጨዋታ የሚቀላቀሉ ይሆናል። ከጥሎ ማለፉ በኋላ የእግር ኳስ አፍቃሪ ከልጅነት ጀምሮ በሚያውቀውና በለመደው መንገድ የአለም ዋንጫ ጨዋታዎች ቅርፅ ውድድሩ እስከ ፍፃሜው ይጓዛል። 

ትንሽ ያስደነግጥ ይሆን?

በእርግጥ ከዚህ ቀደም ከነበረው የምድብ ጨዋታ በአንድ ብቻ ነው የሚያንሰው። ነገር ግን በመጨረሻ ጨዋታዎች ላይ የነበሩትን በጎል ልዩነትና በመሳሰሉት አነስተኛ ልዩነቶች ቡድኖች የሚበላለጡበትን የፉክክር መንፈስ ትንሽ ሊያደበዝዘው ይችላል። 

ፊፋ እንደሚያምነውም እዲሱ የምድብ ጨዋታ ቅርፅ ይህንን የተለመደ ፉክክር ይቀንሰዋል። የሶስት ቡድኖች ምድብ የሚያስደስታቸው ሞውሪንሆም ለአዲሱ እቅድ “እኔ ሶስት ቡድኖች የሚሳተፉበትን ምድብ ነው የምወደው። ሁለት ጨዋታ ታደርጋለህ ወይ ወደ ጥሎ ማለፍ ትገባለህ ወይ ወደ ሀገርህ። በዚህ መንገድ ሁለቱ ጨዋታዎች ወሳኝ ይሆናሉ።” ሲሉ ድጋፋቸውን ገልፀዋል። 

ግን ይሄ ነገር እንደ 2016 የአውሮፓ ዋንጫ ጎል በመከላከል ላይ የተመሰረተ አጨዋወትና ያለጎል የሚጠናቀቁ ጨዋታዎችን ያሳየን ይሆን? 

አዎ። እንደዚህ አይነት ነገር ሊያጋጥመን ይችላል። ከዚህ በተጨማሪም በመጨረሻው የምድብ ግጥሚያ የሚገናኙ ሁለት ቡድኖች በየትኛው ውጤት ቢለያዩ ተያይዘው ወደ ቀጣዩ ዙር እንደሚያልፋ ቀድመው አውቀው ሊጫወቱ የሚችሉበት አጋጣሚ ሊፈጠር ይችላል።  

ነገር ግን እስካሁን ባይፀድቅም እንደዚህ አይነቱን ችግር ለመቅረፍና የምድብ ጨዋታዎች ውጤት በአወንታዊ መልኩ እንዲጠናቀቅ አንድ መላ በእቅድ ደረጃ ተይዟል። በሌላ ቋንቋ በአቻ ውጤት የሚጠናቀቁ የምድብ ጨዋታዎች ከዚህ ቀደም ከነበረው በተለየ ወደ ፍፁም ቅጣት ምት እንዲያመሩና ውጤታቸው በፍፁም ቅጣት ምት እንዲታወቅ ይደረጋል። 

በአህጉር ደረጃ ጭማሪው ምን ይመስላል?

በአዲሱ ውሳኔ መሰረት አውሮፓ 16 (እስካሁን 13 ነበር)፣ አፍሪካ 9 (5)፣ እስያ (8.5) (4.5)፣ ደቡብ አሜሪካ 6 (4.5)፣ ኮንካፋ 6.5 (3.5)፣ ኦሽኒያ 1 (0.5)፣ አዘጋጅ አገር 1 (1) የአለም ዋንጫ ውክልና ይኖራቸዋል። 

* በክፍልፋይ ነጥብ የተገለፁ ቁጥሮች ያላቸው  አህጉሮች ከሌላ አህጉር ከሚገኝ ሌላ ሀገር ጋር በእርስ በርስ ጥሎ ማለፍ (playoff) ጨዋታ ወደ አለም ዋንጫው ሊገባ የሚችል ቡድን ያላቸው በመሆኑ ነው። 

Advertisements

ሚኪያስ በቀለ View All

ይህን ዘገባ ያቀረብኩላችሁ የኢትዮአዲስ ስፓርት ኤዲተርና ፀሀፊ እኔ ሚኪያስ በቀለ ነኝ።

%d bloggers like this: