Skip to content
Advertisements

አጫጭር ወሬዎች: የማክሰኞ አመሻሽ የአውሮፓ ጋዜጦች የዝውውርና ሌሎች አዝናኝና አጓጊ ወሬዎች

በሚኪያስ በ. ወርዶፋ| ማክሰኞ ጥር 2, 2009

የሲቲ የዝውውር ኢላማ የሆነው የባርሴሎናው አማካኝ ራክቲች በስፔኑ ክለብ ያለውን ቆይታ ለማራዘም የውል ማራዘሚያ ድርድር እያደረገ ነው፡፡ (ዴይሊ ሜይል)

ዩናይትድና ሲቲ የቶትነሀም ተከላካይ የሆኑትን ካይሊ ዎከርና ዳኒ ሮዝን ለማስፈረም ትንቅንቅ ሊጀምሩ ነው፡፡ (ዘ ሰን)

ሲቲዎች 18 ወር የኮንትራት ጊዜ የሚቀረውንና በቦርንማውዝ በውሰት የሚገኘውን የአርሰናሉን አማካኝ ጃክ ዊልሻየርን ማስፈረም ፈልገዋል፡፡ (ዴይሊ ስታር) 

ሲቲዎች ሊስፈርሙት የሚፈልጉት የባርሴሎናው አማካኝ ኢቫን ራክቲች ወኪሎች ተጫዋቹ በኒውካምፕ ደስተኛ መሆኑን ገለፁ፡፡ (ዴይሊ ሜይል)

የሊቨርፑሉ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ በ 60 ሚሊዮን ፓውንድ አማካኛቸውን ለመውሰድ ያሰበውን የስፔኑን ባርሴሎና አስጠነቀቁ፡፡ (ዴይሊ ሚረር)

ስዋንሲ የቼልሲውን አጥቂ ሚቹ ባትሱሀይ ወንድም የሆነውን አሮን ሌያ ኢሳቅን ከአንደርሌክት ካስፈረመ በሁዋላ ሰማያዊዎቹ የስዋንሲውን አጥቂ ፈርናንዶ ሎረንቴን እስከ አመቱ መጨረሻ በውሰት መውሰዳቸው እርግጥ ይመስላል፡፡ (ዴይሊ ስታር)

ዌስትሀሞች ለኤፍኤካፕ እንደሚለብሱት ያስተዋወቁትና ከሲቲ ጋር በነበራቸው ጨዋታ ለደጋፊዎች እስከ 55 ዶላር ድረስ የሸጡት ማሊያ ከእንግሊዝ እግር ኳስ ማህበር (FA) ደንቦች ጋር የሚጣረስ መሆኑንና መልበስ እንዳልነበረባቸው ተገለጸ፡፡ (ዴይሊ ሜይል)

ኢንተር ሚላኖች የሮማውን የ 25 አመት ተከላካይ ኮስተስ ማኖላስ ለማስፈረም ከዩናይትድ ጋር ፉክክር ለመጀመር ተዘጋጅተዋል፡፡ (ካልቺዮ መርካቶ ዴይሊ ኤክስፕረስን ጠቅሶ እንደፃፈው) 

በሌላ በኩል ዩናይትድ በአማካኙ ሞርጋን ሽንደርሊን ዝውውር ዙሪያ ከኤቨርተን ጋር በድርድር ላይ ነው፡፡ የኦልትራፎርዱ ክለብ አማካኙን ከሳውዝአምፕተን ሲያመጣ የከፈለውን 24 ሚሊዮን ፓውንድ የተጠጋ ገንዘብ ከኤቨርተን እንደሚቀርብለት ተስፋ አድርጓል፡፡ (ስካይ ስፖርት ዴይሊ ኤክስፕረስን ጠቅሶ እንደፃፈው)

ሲቲ የበርንስሌዩን የ 19 አመት የመሀል ተከላካይ ለማስፈረም የቅድሚያ ግምት አግኝቷል፡፡ (ዴይሊ ሚረር)

ጆሴ ሞውሪንሆ አሁንም የፈርጉሰን የዩናይትድ ቤት ራዕይ እንዲቀጥልና የቀድሞው አለቃ ጫና በክለቡ ላይ እንዲኖር እየሰሩ መሆኑን ተናግረው ፈርጉሰን በፈለጉት ሰአትም እየመጡ ልምምዶቻቸውን እንደሚከታተሉና እሳቸው በሚቀመጡበት የአሰልጣኞች ማረፊያ ላይ እንደሚቀመጡ ገለፁ፡፡ (ዴይሊ ቴሌግራፍ)

በአርሰናል እንደሚፈለግ የተወራለት የቶሪኖው አጥቂ አንድሬ ቤሎቲ ከአርሰናል የሚቀርብለትን የዝውውር ጥያቄዎች ማሰብ እንደማይፈልግ ተናገረ፡፡ (ቱቶ ስፖርት) 

በመጨረሻም …

የዩናይትዱ የክንፍ ተጫዋች አሽሊ ያንግ የቡድን አጋሩ ማርኮስ ሮሆ በስህተት የወሰደ በማስመሰል የኤፍኤ ዋንጫ ሜዳሊያውን ደብቆበት በመፈለግ እንዳሰቃየውና ከደቂቃዎች በሁዋላ ግን እንደመለሰለት ተናገረ፡፡ (ዘ ሰን)

የሼፍልድ ዌንስዴዩ ተጫዋች ጆሴ ሴሜዶ የቡድን አጋሮቹ የክርስቲያኖ ሮናልዶ ጓደኛ እንደሆነ ሲነግራቸው ስላላመኑት የ 31 አመቱን አጥቂ ፌስታይም (facetime) በተሰኘውና ፊት ለፊት እየተያዩ መደዋወል በሚያስችለው የመልዕክት መለዋወጫ አፕሊኬሽን እንዲያዋራው በማድረግ ጉዋደኛው እንዳልሆነና እንደዋሻቸው በመናገር ላበሸቁት የቡድን አጋሮቹ እውነቱን መሆኑን አረጋግጦላቸዋል፡፡ (90 ሚኒትስ ዴይሊ ሜይልን ጠቅሶ እንደፃፈው)

ትውልደ ኢትዮጲያዊው የአርሰናል አጥቂ ጌዲዮን ዘላለም የጀርመኑን ክለብ ቦርሲያ ዶርትሙንድን ሊቀላቀል ከጫፍ ደርሷል፡፡ (ዴይሊ ስታር) 

የአለም እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ፊፋ ዛሬ ባደረገው የምክር ቤት ስብሰባ ከ 2026 አለም ዋንጫ ጀምሮ የተሳታፊ ቁጥሮችን ወደ 48 የሚያሳድገውን ረቂቅ ደንብ አፀደቀ።

በዚህ በአዲሱ አሰራር መሰረትም ሶስት ቡድኖችን የሚይዙ 16 ምድቦች ሲኖሩ ምድቡን በአንደኛና ሁለተኛነት የሚጨርሱ ወደ ቀጣዩ ዙር የሚያልፉ ይሆናል። 

ይህ ዛሬ ከሰአት በፊፋ ምክር ቤት አባላት የፀደቀውን ሀሳብ ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና፣ ካርሎስ ፑዮልና ጆሴ ሞውሪንሆ የመሳሰሉ የእግር ኳስ ቤተሰቦች ድጋፍ ሰጥተውታል። (ጎል)

Advertisements

ሚኪያስ በቀለ View All

ይህን ዘገባ ያቀረብኩላችሁ የኢትዮአዲስ ስፓርት ኤዲተርና ፀሀፊ እኔ ሚኪያስ በቀለ ነኝ።

%d bloggers like this: