Skip to content
Advertisements

የአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ትንተና -ካሜሮን

በሚኪያስ በ. ወርዶፋ | ማክሰኞ ጥር 2፣ 2009 ዓ.ም

ካሜሮን ራሱን ከቡድኑ ስብስብ ውጪ ያደረገውን የሊቨርፑሉን መሀል ተከላካይ ዮል ማቲፕን ሳትይዝ ወደ ጋቦን የምታመራ ይሆናል፡፡ ‘አይበገሬዎቹ አምበሶች’ ከዚህ ቀደም ለአራት ጊዜያት የአፍሪካን ዋንጫ ማንሳት የቻሉ ሲሆን ዘንድሮም የቀድሞውን ያህል አስፈሪ ባይሆንም ለጥሩ ውጤት ከሚጠበቁት ቡድኖች አንዱ ናቸው፡፡

የካሜሮን ደጋፊዎች ስሜታዊ የሆነ የድጋፍ ታሪክ አላቸው

የካሜሮን ወሳኝ ተጫዋቾች እነማን ናቸው?

ኒኮላስ ኒኮሉ፣ አማካኝ፣ ሊዮን ኒኮሉ የቀድሞውን የካሜሮንና ባርሴሎና ዝነኛ ተጫዋች ሳሙኤል ኢቶን ለአለም ያበረከተው የካዲጂ ስፖርት አካዳሚ ፍሬ ነው፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ ዋንጫ የተሳተፈው በ 2010 ሲሆን በተመሳሳይ አመት ለተደረገው የደቡብ አፍሪካ የአለም ዋንጫም ሀገሩን መወከል ችሎ ነበር፡፡ የቀድሞው የሞናኮ መሀል ተከላካይ ማርሴይን ወክሎ በቻምፒዮንስ ሊግ ላይም መጫወት ችሏል፡ ክሊንተን ኒጄ፣ ክንፍ ተጫዋች፣ ማርሴይ (ከቶትነሀም በውሰት)

ኒኮላስ ን’ኮሉ ከማርሴ ወደዋና ተቀናቃኙ ሊዮን በሰኔ ወር ተዛውሯል

የቶትነሀሙ ኒጄ በውሰት በፈረንሳይ ሊግ 1 የሚገኝ ሲሆን የእግር ኳስ ህይወቱን የጀመረው ከዩናይትዱ አጥቂ ማርሻል ጋር በመሆን በፈረንሳዩ ሌላኛ ክለብ ሊዮን ነው፡፡ ከኮንጎ ጋር በነበረው የ 2014 ጨዋታም ለሀገሩ ግብ ማስቆጠር ችሏል፡፡ ቤንጃሚን ሙካንድጆ፣ አጥቂ፣ ሎርዬንት ሙካንድጆ ሌላኛው የካዲጂ ስፖርት አካዳሚ ፍሬ ሲሆን አሁን በፈረንሳዩ ክለብ በአጥቂነት ሚና እየተጫወተ ይገኛል፡፡ የ 28 አመቱ አጥቂ ለመጀመሪያ ጊዜ በ 2011 ለብሄራዊ ቡድን ጨዋታ ጥሪ የቀረበለት ሲሆን የ 2014 አለም ዋንጫ ተሳታፊም ነበር፡፡

የሎሪየንቱ ቤንጃሚን ሞካንጂ በ2014 የዓለም ዋንጫ ላይ ተሰልፏል

የካሜሮን የአፍሪካ ዋንጫ የተጫዋቾች ስብስብ

በረኞች፡ ፋብሪክ ኦንዶአ (ሲቪላ፣ ስፔን)፣ ጁሌስ ጎዳ (አጃሲዮ፣ ፈረንሳይ)፣ ጆርጀስ ቦክዌ (ኮተን ስፖርት)

ተከላካዮች፡ ኒኮላስ ኒኩሉ (ሊዮን፣ ፈረንሳይ)፣ አምብሮይሲ ኦዮንጎ (ሞንትሪያል ኢምፓክት፣ ካናዳ)፣ ሞሀመድ ዲጄቲ (ጅምናስቲክ ዲ ቶራኖ፣ ስፔን)፣ ጆናታን ንግዌም (ፕሮግሬሶ)፣ ሚካኤል ንጋዱ ንጋድጁ (ስላቪያ ፕራግ፣ ቼክ ሪፐብሊክ)፣ አዶልፌ ትዬኩ (ሶሽዋ፣ ፈረንሳይ)፣ ኮሊንስ ፋይ (ስታንዳርድ ሊዤ፣ቤልጄም)፣ እርነስት ማቡካ (ኤምስኬ ዚሊያን፣ ስሎቫኪያ)

አማካኞች፡ ኤድጋር ሳሊ (ኤፍሲ ኑረምበርግ፣ ጀርመን)፣ ጆርጀስ ማንዲጂክ (ሜትዝ፣ ፈረንሳይ)፣ ሰባስቲያን ሲያኒ (ኦስቴንዴ፣ ቤልጄም)፣ ፍራንክ ቦያ (ኤፒኢጄኢኤስ አካዳሚ)፣ አርናሁድ ጆሁም (ሀርትስ፣ ስኮትላንድ) 

አጥቂዎች፡ ቪንሰንት አቡበከር (ቤሽኪሽታሽ፣ ቱርክ)፣ ቤንጃሚን ሙካንድጆ (ሎርዬንት፣ ፈረንሳይ)፣ ክሊንተን ኒጄ (ማርሴይ፣ ፈረንሳይ)፣ ጃኪዌስ ዙሀ (ኤፍሲ ካይዘርሉተን፣ ጀርመን)፣ ካርል ቶኮ ኢካምቢ (አንገርስ፣ ፈረንሳይ)፣ ሮበርት ንዲፒ ታምቤ (ስፓርታክ ትሮኖቫ፣ ስሎቫኪያ)፣ ክርስቲያን ባሶጎግ (ኤኤቢ፣ ዴንማርክ)

ካሜሮን እንዴት ለውድድሩ ለማለፍ በቃች?

ካሜሮን ለጋቦኑ የአፍሪካ ዋንጫ ስታልፍ ምድቧን ከሞሪሽየስ፣ ደቡብ አፍሪካና ጋምቢያ በልጣ በአንደኛነት በማጠናቀቅ ነው፡፡ በማጣሪያውም የማይበገሩት አምበሶች ሁሉንም ጨዋታ ሳይሸነፉ ሰባት ጎሎችን ማስቆጠር ችለዋል፡፡ በአፍሪካ ዋንጫውም በምድብ ሀ ከአዘጋጇ ጋቦን፣ ቡርኪናፋሶና ጊኒቢሳው ጋር በአንድ ምድብ ተደልድለዋል፡፡

የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ማን ናቸው? 

ሁጎ ብሩስ ለአምስት አመታት በክለብ ብሩዥ የተጫወቱ ሲሆን በአሰልጣኝነትም የቤልጄሙን ክለብ ለሁለት የቤልጄም ሊግ አሸናፊነት አብቅተውታል፡፡ የካሜሮንን ብሄራዊ ቡድን ለማሰልጠን ጥያቄ ያቀረቡት ቡድኑን የማሰልጠን የስራ ማስታወቂያ በኢንተርኔት ላይ ከተመለከቱ በኋላ ነው፡፡

የካሜሮን የአፍሪካ ዋንጫ ታሪክ ምን ይመስላል?

ሮጀር ሚላ በማዕዘን መምቻው ላይ ያሳየው የደስታ መግለጫ ዳንስ ግብ ካገቡ በኋላ የሚደረግ የደስታ መግለጫ እንቅስቃሴን ለዘልዓለም ቀይሮታል

ካሜሮን የ 1984፣ 1988፣ 2000 እና የ 2002 የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ በመሆን የውድድሩ ስኬታማ ሀገር ናት፡፡ የቀድሞው የቡድኑ አጥቂ ሳሙኤል ኢቶም በ 18 ጎሎች የአፍሪካ ዋንጫ ኮከብ ጎል አስቆጣሪ ነው፡፡ ባሳለፍነው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ግን በሁሉም የምድብ ጨዋታዎች ተረተው በጊዜ መሸኘታቸው ይታወሳል፡፡ ካሜሮኖች በ 2019 የሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ አዘጋጅ እንደመሆናቸው ይሄን ውድድር አሸንፈው ያሳለፍነው የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ ተብለው በሀገራቸው የሚካሄደውን ውድድር ለመጀመር በማሰብ ወደ ጋቦን ያመራሉ፡፡ ከዚህ ሌላ ከየትኛውም የአፍሪካ ቡድን በበለጠ ሁኔታ ለሰባት ጊዜያት ለአለም ዋንጫም ማለፍ የቻሉ ናቸው፡፡

የካሜሮኑ ታሪካዊ ተጫዋች ሳሙኤል ኤቶ በ18 ግቦች የአፍሪካ ዋንጫ የምንግዜውም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ነው

ካሜሮን ከጋቦኑ ውድድር ምን ይጠበቅባታል? 

ካሜሮኖች ከቡርኪናፋሶ በመቀጠል ከምድቡ ለማለፍ ትልቅ ግምት አግኝተዋል፡፡ ነገር ግን ጋቦን በሜዳዋ እንደመጫወቷና ጊኒቢሳውም በአለም የአገሮች የእግር ኳስ ደረጃ ከማይበገሩት አምበሶች በሶስት ብቻ ማነሷ ካሜሮን ትልቅ ፈተና እንደሚጠብቃት ይነግረናል፡፡ ከምድቡ በሁለተኛነት የምታልፍ ከሆነም የሰይዱ ማኔ ሀገር ከሆነችውና ብዙ ተስፈኛ ኮከቦችን ከያዘችው ተጠባቂዋ ሴኔጋል በጥሎ ማለፍ የመገናኘት እድሏ ሰፋ ያለ ይመስላል፡፡ ይህም ፈተናዋን ይበልጥ እንዳይጨምረው ተሰግቷል፡፡

Advertisements
%d bloggers like this: