Skip to content
Advertisements

የ2026 ዓለም ዋንጫን አሜሪካ ከካናዳና ሜክሲኮ ጋር በጥምረት ልታዘጋጅ ትችላለች

በወንድወሰን ጥበቡ | ረቡዕ ጥር 3፣ 2009 ዓ.ም

በ2026 የዓለም ዋንጫ ተሳታፊ ሃገራት ወደ48 ሲያድጉ በዓለም ዋንጫው ታሪክ ለመጀምሪያ ጊዜ ውድድሩ በሶስት ሃገራት ማለትም በአሜሪካ፣ በካናዳና በሜክሲኮ አስተናጋጅነት የሚዘጋጅበት ዕድል ይኖራል።

የፊፋ ምክር ቤት ማክሰኞ ዕለት የውድድሩ ተሳታፊ ሃገራትን ቁጥርን በ16 ከፍ ለማድረግ በሙሉ ድምፅ ውሳኔ ላይ መድረሱን ተከትሎ የሶስት አዘጋጅ ሃገሮች ሊኖሩ እንደሚችሉም ውሳኔውን አሳልፏል።

እንዲሁም ለመጨረሻዎቹ የምድብ ጨዋታዎች ምድብ ማጣሪያ አላፊዎችን ለመለየት በምድብ ጨዋታዎች ላይ የመለያ ምት ተግባራዊ ሊደረግም እንደሚችልም ተገልፅዋል። 

በአዲሱ የውድድር መዋቅር ሶስት ሶስት ቡድኖች ያሉበት 16 ምድብ ይኖርና ከየምድቡ ሁለቱ ቡድኖች ወደ32ቱ የጥሎማለፍ ዙር እንዲያልፉ ይደረጋል። አጠቃላይ ውድድሩም በ32 ቀናት የሚጠናቀቅ ይሆናል። በምድብ ማጣሪያ ላይም በቀን አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ። ለፍፃሜ የሚደርሱ ብሄራዊ ቡድኖችም በውድድሩ በአጠቃላይ እንደቀድሞው ሰባት ጨዋታዎችን ያደርጋሉ። 

አሜሪካ የ2026ቱን የዓለም ዋንጫ የማዘጋጀት የተሻለ ዕድል ያላት ቢሆንም፣ ውድድሩን የምታዘጋጀው ግን ከካናዳና ሜክሲኮ ጋር በመጣመር ነው። ሆኖም 80 ጨዋታዎችን የማስተናገድ የአንበሳውን ድርሻ የምትወስድም ትሆናለች።

የኮንካፋ ፕሬዘደንት የሆኑት ካናዳዊው ቪክቶር ሞንታጋሊያኒ ይህን አስመልክተው “እግርኳስ ከቃላት ጨዋታ ወጥቶ “የትረምፕ ፖለቲካ ይሆናል።” ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ገልፀው። አዲስ የሚሾሙት የአሜሪካን ፕሬዘዳንት በሃገራት ድንበር ላይ ግዙፍ ግንብ መገንባታቸውን ትተው ይህን ውድድር ከሜክሲኮ ጋር በጥምረት ማስተናገዳቸው አሜሪካንን ያስደስታታል ብለው እንደሚያስቡም ገልፀዋል።

ሞንቶጋሊያኒ አክለውም “የአሜሪካ-ካናዳ- ሜክሲኮ የ2026 ዓለም ዋንጫ የመሆን ዕድሉ እጅግ ሰፊ ነው። ምክኒያቱም ህጉ አሁን ይህን ይፈቅዳል። ይህ ደግሞ ለኮንካፋ መልካም ዕድል ነው።” ብለዋል።

የዓለም ዋንጫ አስተናጋጆች

1930 ኡራጓይ

1934 ጣሊያን

1938 ፈረንሳይ

1942 አልተካሄደም

1946 አልተካሄደም

1950 ብራዚል

1954 ስዊዘርላንድ

1958 ስዊድን

1962 ቺሊ

1966 እንግሊዝ

1970 ሜክሲኮ

1974 ጀርመን

1978 አርጄንቲና

1982 ስፔን 

1986 ሜክሲኮ

1990 ጣሊያን 

1994 አሜሪካ 

1998 ፈረንሳይ

2002 ጃፓን እና ደቡብ ኮሪያ

2006 ጀርመን

2010 ደቡብ አፍሪካ

2014 ብራዚል 

2018 ሩሲያ 

2022 ኳታር 

“ብዙ ሃገራት በጣም ደስተኞች ይሆናሉ። በ21ኛው ክፍለዘመን የዓለም ዋንጫን ቅርፅ ማስያዝ ይኖርብናል። አሁን ከአውሮፓና ደቡብ አሜሪካም በተጨማሪ እግርኳስ ጨዋታ ይኖራል።” ሲሉ የፊዋው ፕሬዝዳንት ኢንፋንቲኖ አዲሱን ህግ አስመልክተው ተናግረዋል። 

በዓለም ዋንጫው ላይ 48 ሃገራታ ተሳሳታፊ እንደሚሆኑ ውሳኔ ላይ ቢደረስም ሁሉም ኮንፌዴሬሽኖች በጭማሪው ላይ ፈቃደኝነታቸውን እስኪገልፁ ድረስ የተሳታፊ ሃገራትን ስብጥር በተመለከተ ምንም አይነት የተገባ ቃል ግን የለም።

የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር ውሳኔውን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ “የዓለም ዋንጫን ተሣታፊዎች ቁጥር ከፍ በመደረጉ ላይ ሌሎች ኮንፌዴሬሽኖች በህብረት እንደሚስማሙ ግልፅ ነው። በዚህ መሰረትም የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር አዲሱን መዋቅር ለመደገፍ እንደሚቀላቀል ውሳኔ ላይ ደርሷል።” 

አዲሱ የውድድር መዋቅር በ2026 የዓለም ዋንጫ ላይ እንዴት ተግባራዊ ይሆናል

ጥያቄ፡ የምድብ ድልድሉ ምን ይመስላል?

እያንዳንዱ ብሄራዊ ቡድን በሶስት ቡድኖች በተዋቀርው ምድቡ ውስጥ ሁለት ጊዜ ይጫወታል። የበላይ ሆነው የሚጨርሱ ሁለት ቡድኖች ወደ32 የመጨረሻ ዙር ያልፉና በዚህ ዙር የጥሎ ማለፍ ውድድሩ የሚጀመር ይሆናል። በምድብ ማጣሪያ ጨዋታ ላይ በአቻ የሚጠናቀቁ ጨዋታዎች የመጨረሻ የጨዋታ ውሳኔ ለመስጠት ሲባል በመለያ ምት እንዲለለያዩ ይደረጋል።

ጥያቄ፡ 48 ቡድኖች መሆናቸው ሌላ የሚፈጥረውን ነገር ምንድ ነው?

ብዙ ቡድኖች አሉ ማለት ብዙ ጨዋታዎች ይኖራሉ ምለት ነው። በዚህም አሁን ባለው የውድድር መዋቅር ይደረጉ የነበሩ 64 ጨዋታዎች ወደ80 ያድጋሉ። ይሁን እንጂ አንድ ቡድን እስከፍፃሜው ቢዘልቅ በውድድሩ ላይ በአጠቃላይ የሚያደርጋቸው ጨዋታዎች አሁን ተግባራዊ ከሚደረገው ጋር በተመሳሳዩ ሰባት ጨዋታዎችን የሚያደርግ ይሆናል።

ጥያቄ፡ የ2026 ዓለም ዋንጫ የት ይካሄዳል?

እስካሁን አልታወቀም። ነገር ግን አሜሪካ የማዘጋጀት ጥያቄውን ታቀርባለች ተብሎ ይጠበቃል። አሜሪካ ብቸኛ አዘጋጅ አሊያም ከሜክሲኮና ከካናዳ ጋር በጥምረት ልታዘጋጅ ትችላለች።

ጥያቄ፡ ፊፋ የዓለም ዋንጫ ተሳታፊዎችን ቁጥር ማሳደግ ለምን አስፈለገው?

ኢንፋንቲኖ የሴፕ ብላተርን የፊፋ ፕሬዝዳንታዊ ዙፋን ለመረከብ በሚያደርጉት የምርጫ ቅስቀሳ ቀጥሩን ከፍ እንደሚያደረጉ ቃል ገብተው ነበር። ይህ የትግበራ ዕቅዱም ምንም እንኳ አብዛኞቹ ድምፃች እንዲሁ ማለፍ ባይችሉም 211 የሆነውን የፊፋ አባላት አብላጫ ድምፅ ግን አስገኝቶላቸዋል። ከአውሮፓ ውጪ የሆኑ ኮንፌዴሬሽኖችም አሁን ባለው የውድድር መዋቅር ለበርካታ አመታት ተጣቃሚ እንዳልሆኑም ይሰማቸው ነበር፡፡

ጥያቄ፡ የዓለም ዋንጫ ለመጨረሻ ጊዜ የመዋቅር ለውጥ የተደረገበት መቼ ነበር?

በ1930 የመጀመሪያው ውድድር 13 ተሳታፊ ሃገራት ነበሩት። ከዚያ በኋላ ግን በ1982 የስፔኑ የዓለም ዋንጫ ውድድር ተሳታፊዎቹ 24 እስኪደርሱ ድረስ ለፍፃሜው ውድድር የሚያልፉት 16 ተሳታፊ ሃገራት ነበሩ። አሁን ተግባራዊ እየሆነ የሚገኘው የ32 ሃገራት ተሳትፎ ደግሞ የተጀመረው በ1998ቱ የፈረንሳዩ የዓለም ዋንጫ ላይ ነበር። 

ጥያቄ፡ ተጨማሪውን 16 የዓለም ዋንጫ ተሳትፎውን ማን ያገኛል?

እስከሁን አልተገለፀም።

ከቀረቡት የትግበራ ዕቅዶች አንዱ እንደሚያመለክተው ከሆነ ግን የአውሮፓ ተሳታፊ ሃገሮች ቁጥር ከ13 ወደ16 ከፍ ይላል። አብዛኛው የተሳትፎ ተጠቃሚ የሚሆነው አህጉር ግን ከአምስት ወደዘጠኝ የሚያድገው የአፍሪካ ሃጋራት የተሰትፎ ዕድል ነው። እሲያ 8.5 ቦታ ሲያገኝ፣ ሰሜን አሜሪካ ደቡብ አሜሪካ እያንዳንዳቸው 6.5 ቦታ እንዲሁም ኦሺኒያ 1.5 ቦታ ይኖራቸዋል። ግማሹ ቦታ ዝቅተኛ ኃላፊ ሃገራት የሚኖራቸው የእሲያ፣ የሰሜን አሜሪካ፣ የደቡብ አሜሪካና የኦሺኒያ ሃገራት በደርሶ መልስ ጨዋታ የሚያገኙት ይሆናል።

Categories

ፊፋ

Advertisements
%d bloggers like this: