Skip to content
Advertisements

​ጊኒ-ቢሳው – የስብስቡ አባላት፣ የውድድሩ ተሳትፎ ታሪክ፣ በውድድሩ የሚጠበቅባት ስኬት እና ሌሎች መረጃዎች [የአፍሪካ ዋንጫ]


በሚኪያስ በ. ወርዶፋ | ረቡዕ ጥር 3፣ 2009 ዓ.ም

ለመጀመሪያ ጊዜ ለአፍሪካ ዋንጫው ማለፍ የቻለችው ጊኒ-ቢሳው አስደናቂ የማጣሪያ ገድሎችን ፈፅማ የጋቦኑን ውድድር መጀመር እየተጠባበቀች ትገኛለች፡፡ ከስድስቱ የማጣሪያ ጨዋታዎች (በአስደናቂ ሁኔታ በ97ኛ ደቂቃ ጎል ዛምቢያን የረታችበትን ጨምሮ) ሶስቱን በማሸነፍ የምድቡ አንደኛ በመሆን ማለፍ ችላለች፡፡ 
 የጊኒ-ቢሳው ወሳኝ ተጫዋቾች እነማን ናቸው?
ባኩንድጂ ሳአ፣ አማካኝ፣ ፓሪስ ኤፍሲ (ፈረንሳይ)

የእግር ኳስ ህይወቱን በፈረንሳይ ያሳለፈው የ 29 አመቱ ሳአ የጊኒ-ቢሳው አምበልና ተጠባቂ ተጫዋች ነው፡፡ ለብሄራዊ ቡድኑ 11 ጨዋታዎችን ማድረግ የቻለ ሲሆን ሀገሩ ጥሩ እንቅስቃሴ ለማድረግ ከቻለች ነጥረው ሊወጡ ይችላሉ ተብለው ከሚጠበቁ የቡድኑ ተጫዋቾች አንዱና ዋነኛው ነው፡፡

የጊኒ-ቢሳው አፍሪካ ዋንጫ ተጫዋቾች ስብስብ

በረኞች፡ ሩይ ዳቦ (ኮቫ ዳፒይዳዴ/ፖርቹጋል)፣ ፓፓ ማሴ ምባዬ ፎል (ሲዲ ኦሬላና ኮስታ ዱልስ/ስፔን)፣ ጆናስ ሜንዴዝ (ሳልጉይሮስ/ፖርቹጋል)

ተከላካዮች፡ ማማዱ ካንዴ (ቶንዴላ/ፖርቹጋል)፣ ኢማኑኤል ሜንዲ (አልታወቀም)፣ ሩዲኒልሰን ሲልቫ (አልታወቀም)፣ አጎስቲንሆ ሶሬስ (ስፖርቲንግ ኮቪልሀ/ፖርቹጋል)፣ ጁሀሪ ሶሬስ (ማፍራ/ፖርቹጋል)፣ ሁምፔካ (ፍሬሙንዴ/ፖርቹጋል) 

አማካኞች፡ ቡኩንዲጂ ካ (አልታወቀም)፣ ኢድሪሳ ካማራ (አቬሊኖ/ጣሊያን)፣ ፍራንሲስኮ ጁኒየር (ስተሮምስጉደስት/ ኖርዌይ)፣ ጂን ፖል ሜንዲ (ዩኤስ ኩቭሊን/ፈረንሳይ)፣ ናኒ (ፌልጉዬራስ/ፖርቹጋል)፣ ሳና (አካዳሚካ ቪሱ/ፖርቹጋል)፣ ቶኒ ሲልቫ (ላቫዲያኮስ/ግሪክ)፣ ቶኒ ሲልቫ ብሪቶ (ብራጋ/ፖርቹጋል)፣ ፒኩዌቲ (ብራግ/ፖርቹጋል)፣ ዚዚንሆ (ሌቫዲያኮስ/ግሪክ)

አጥቂዎች፡ አቤል ካማራ (ቤሌንሰስ/ፖርቹጋል)፣  ጃኦ ማሪዮ (ቼቨስ/ፖርቹጋል)፣ ፍሬድሪክ ሜንዲ (ሁልሳን ሀዩንዳይ/ደቡብ ኮሪያ)፣ አሚዶ ባልዴ (ኦልሀኔንስ/ፖርቹጋል)

ጊኒ-ቢሳው እንዴት ለውድድሩ ለማለፍ በቃች?

በአራት ቀናት ውስጥ ከኬኒያ ጋር ሁለት የደርሶ መልስ ጨዋታዎችን ያደረገችው ጊኒ-ቢሳው 1-0 ያሸነፈችበት ጨዋታ ወደ አፍሪካ ዋንጫው ለማለፍ በጣም ጠቅሟታል፡፡ ነገር ግን ዛምቢያን በአስደናቂ ሁኔታ እስክትረታ ድረስ ማለፏ እርግጠኛ አልነበረም፡፡ የቶኒ ሲልቫ የ97ኛ ደቂቃ ግብ 3-2 እንድታሸንፍና ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ ዋንጫ መድረክ እንድትቀርብ አስቻሏታል፡፡ 

የጊኒ-ቢሰው አሰልጣኝ ማን ናቸው?

በ2016 ከስድስት አመታት ቆይታ በሁዋላ ዳግም ወደ ቡድኑ የተመለሱት የ68 አመቱ ባሲሮ ካንዴ የቡድኑ አሰልጣኝ ናቸው፡፡ ለጊኒ-ቢሳው በተከላካይነት መጫወት የቻሉት ካንዴ ከ2003-2010 ድረስ የቡርኪናፋሶ አሰልጣኝ ሆነው ሰርተዋል፡፡

የጊኒ-ቢሳው የአፍሪካ ዋንጫ ታሪክ ምን ይመስላል?

የ 2017 የጋቦኑ የአፍሪካ ዋንጫ ለጊኒቢሳው የመጀመሪያው በመሆኑ ለሀገሪቱ የተሰጠው ግምት በጣም አነስተኛ ነው፡፡ በውድድሩ የደረሳቸው ምድብም በጣም ጠንካራና አዘጋጇን ጋቦንን ጨምሮ ካሜሮንና ቡርኪናፋሶን የመሰሉ ፈታኝ ቡድኖችን ያካተተ ነው፡፡

በውድድሩ ላይ ከጊኒ-ቢሳው ምን ይጠበቃል? 

ጊኒ-ቢሳዎች ከ16ቱ ተሳታፊ ሀገሮች አነስተኛ ግምት የተሰጣቸውና ለዋንጫም እነሱን ብሎ አንድ ዶላር ላስያዘ ድንገት ዋንጫ ከበሉ 150 ዶላር (ካስያዘው ገንዘብ 150 እጥፍ) የሚያስገኙ ግምት የራቃቸው የመጀመሪያው ቡድን ናቸው፡፡ ብዙዎችም ከመጀመሪያው ምድብ አያልፉም የሚል እምነት ካሳደሩባቸው ቡድኖች አንዱና ዋነኞቹ ናቸው፡፡

Advertisements
%d bloggers like this: