Skip to content
Advertisements

መርሲሳይድ ወይስ ማንችስተር? ታላቁ የትኛው ነው?

በ ወንድወሰን ጥበቡ | አርብ ጥር 5፣ 2009 ዓ.ም


ኤቨርተን በዚህ ሳምንት መጨረሻ በጉዲሰን ፓርክ ማንችስተር ሲቲን ሲገጥም፣ በዚያው ቀን ይህን ጨዋታ ተከትሎ ደግማ  በኦልትራፎርድ የማንችስተር ዩናይትድና የሊቨርፑል ጨዋታ ይደረጋል። ነገር ግን ከመርሲሳይዶቹ ክለቦችና ከማንችስተሮቹ ክለቦች ትልቁ የትኛው ነው?

የአውሮፓው ግዙፍ ሚዲያ ስካይ ስፖርትስ ያለፉትን 50 ዓመታት የሊግ ደረጃዎቻቸውን። የተቀዳጇቸውን ድምር ክብሮችና በአሁኑ ወቅት ያላቸውን ዓለምአቀፋዊ ድጋፍ መሰረት አድርጎ የትኞቹ ጥንዶች የተሻለ ኃያል እንደሆኑ ማስረጃዎችን አስደግፎ ሰፋ አድርጎ አቅርቧል። ኢትዮአዲስ ስፖርትም እንዲህ ለእናንተ እንዲስማማ አድርጋ በሚከተለው መልኩ አቅርባልዎታለች።

የሊግ ደረጃ

ማንችስተር ዩናይትድና ሊቨርፑል እንደቅደም ተከተላቸው 20 እና 18 የሊግ ክብሮችን በመቀዳጀት በእንግሊዝ ከፍተኛ ስኬት ያላቸው ክለቦች ናቸው። ነገር ግን ሊቨርፑልም ሆነ እስከ1986/86 ድረስ ዘጠኝ የሊግ ዋንጫዎችን ካነሱ ወዲህ ፈፅሞ ዋንጫውን አንስተው የማያውቁት የመርሲሳይዱ ጎረቤቱ ኤቨርተኖዥ የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ በጭራሽ አንስተው አያውቁም። 

በአንፃሩ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ባሉት ጊዜያት ባለፉት አምስት ዓመታት ማንሳት ከቻሉት አራት ዋንጫ ሁለቱን ያነሱት ሲቲዎች ዩናይትዶች በማንችስተር ከተማ ይዘውት የቆዩትን የበላይነት እየተገዳደሩ ይገኛሉ። ይሁን እንጂ ሲቲዎች በ1964/65 እና በ1992/93 ባሉት ጊዜያቶች ውስጥ ስድስት የውውድር ዘመኖችን በእንግሊዝ ዝቅተኛው ሊግ ውስጥ ዝቅ ባለ ደረጃ አሳልፈዋል።

በተጨማሪም ሰማያዊዎቹ (ሲቲዎች) በ1995/96 ከፕሪሚየር ሊጉ ወርደው በ1998/99 በሊግ ዋን ላይ አዲስ ህይወት ጀምረዋል። ማን ሲቲዎች በ2000/01 መልሰው ወደታችኛው ሊግ ከመውረዳቸው በፊት በተከታታይ ለሁለት ጊዜያት በዝቅተኛው ሊግ ቆይተዋል። ወደእንግሊዝ ከፍተኛው ሊግ የተመለሱትም በ2002/03 ነበር።

ክለቦች በሊጉ የ50 ዓመታት ጊዜ የነበራቸውን አማካኝ ደረጃ መሰረት አድርጎ ደረጃ የሚሰጠው የስካይ ስፖርትስ “ፍፁማዊ ሊግ” ምንም እንኳ ከ1992/93 ወዲህ 13 የፕሪሚየር ሊግ ክብሮችን ቢቀዳጅም አማካኝ ደረጃው 5ኛ ከሆነው ማንችስተር ዩናይትድ አስቀድሞ ሊቨርፑልን 3.46 በሆነ አማካኝ ደረጃ የእንግሊዝ ስኬታማው ክለብ አድርጎ በቀዳሚነት ያስቀምጠዋል። 

በመሆኑም የሊግ ደረጃው  መሰረት በማድረግ የመርሳይዱ ክለብ አሁንም በድጋሚ ቀዳሚነቱን ይወስዳል። ኤቨርተናና ማንችስተር ሲቲ በዚህ የስካይ ስፖርት ፍፁማዊ ደረጃ እንደቅደም ተከተላቸው 8.98 እና 13.62 ደረጀዎችን ይዘው ተቀምጠዋል።

በጥምርም የመርሲሳይዱ ቡድን አማካኝ የሊግ ደረጃው 6.22 ሲሆን የማንችስተሩ ጥምር ቡድን ደግሞ በ9.31 ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
የመርሲሳይዱ ቡድን 1-0 የማንችስተሩ ቡድን 

የዋንጫ ክብሮች

የዋንጫ ክብሮችን ከግምት ውስጥ ካስገባን ማንችስተር ዩናይትድና እና ሊቨርፑል እንደቅድም ተከተላቸው ባነሷቸው 64 እና 60 ዋንጫዎች ቀዳሚዎቹ ክለቦች ናቸው። ምንም እንኳ ዩናይትድ የዋንጫዎች ብልጫ ቢኖረውም ሊቨርፑል ተቀናቃኙ ካነሳቸው ሶስት የአውሮፓውያኑ ዋንጫ (አሁን ሻምፒዮንስ ሊግ የሚባለው) የበለጡ አምስት የአውሮፓውያኑን ዋንጫ ማንሳት ችሏል።

መገኘት በቻለ ድምር የዋንጫ ክብር ኤቨርተን ዘጠኝ የእንግሊዝ የሊግ ዋንጫዎችንና አምስት የኤፍኤ ዋንጫዎችን ጨምሮ በድምሩ ባገኛቸው 24 ዋንጫዎች አራት የእንግሊዝ ሊግ፣ አምስት የኤፍኤ ዋንጫዎችንና እና አራት የሊግ ዋንጫዎችን በድምሩ 18 ዋንጫዎችን ማንሳት ከቻለው ማንችስተር ሲቲ ይበልጣል።  አሁንም የመርሲሳይዶቹ ክለቦች በጋራ ባገኟቸው 84 የዋንጫ ክብሮች 82 የዋንጫ ክብሮች ካሏቸው የማንችስተሮቹ ክለቦች ይልቃሉ።

የመርሲሳይዱ ቡድን 2-0 የማንችስተሩ ቡድን

የተመልካች ቁጥር

አሁንም ያለፉት 50 ዓመታት በስታዲየም ገብተው በጨዋታዎች ላይ መታደም የቻሉትን የተመልካቾች ቁጥር መሰረት እናደርጋለን። በዚህ ግን እንደ ዎርልድፉትቦል ድረገፅ (www.worldfootball.net) ቁጥራዊ መረጃ ከሆነ ብልጫውን የሚወስዱት የማንችስተሮቹ ክለቦች ናቸው። 

ዩናይትድ ከ1967/68 አንስቶ በአማካኝ 55,350 ተመልካቾችን ወደስታዲየሙ መሳብ ሲችል ጎረቤቱ ሲቲ ደግሞ 36,127 ተመልካቾች ወደስታዲየሙ መጥተው እንዲመለከቱ ማድረግ ችሏል። በመርሲሳይድ ደግሞ የሊቨርፑል የተመልካች ቁጥር በአማካኝ 41,403 ሲሆን፣ ኤቨርተን በጉዲሰን ፓርክ የተገኙለት የተመልካቾች አማካኝ ቁጥር 33,011 ነው።

በጥምር ከ1967/68 አንስቶ ስታዲየም የገቡ ተመልካቾች አማካኝ ቁጥር

ጥምር ቡድን አማካኝ 
ተመልካች
የማንችስተር ቡድን  45,738
የመርሲሳይድ ቡድን  37,207

ከ1967/68 አንስቶ በአማካኝ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተመልካች በስታዲየም የታደመባቸው ክለቦች

ክለብ አማካኝ 
ተመልካች
ማን ዩናይትድ 55,350
ሊቨርፑል 41,403
አርሰናል 39,445
ኒውካሰል 39,146
ማን ሲቲ 36,127
ሰንደርላንድ 33,718
ኤቨርተን 33,012
ሊድስ ዩናይትድ 32,886
ቼልሲ 32,483

ይህ ማለት የማንችስተሩ ቡድን በተመልካቹ ፉክክር ረገድ አሸናፊ በመሆን ቅድሚያ የተወሰደበትን የሁለት ለዜሮ ልዩነት በአንድ ዝቅ ማድረግ ይችላል።.

የመርሲሳይዱ ቡድን 2-1 የማንችስተሩ ቡድን

ዓለማቀፋዊ ድጋፍ

በፌስቡክ፣ በኢንስታግራምና በትዊተር በድምሩ 128.1 ሚሊዮን የማህበራዊ ሚዲያው ተከታታዮች ያሉት የማንችስተሩ ጥምር ቡድን ብልጫ በመውሰድ ፉክክሩ አቻ ያደርዋል። 

ስፓርታዊ የቁጥር መረጃዎችን በሚያጠናቅረው ኩባንያ ብራንድቲክስ መረጃ ከሆነ የዩናይትድ ይፋዊ ማህበራዊ ሚዲያ 97.4 ሚሊዮን ተከታዮች ሲኖሩት፣ ሲቲ ደግሞ 30.7 ሚሊዮን ተከታዮች አሉት።

የመርሲሳይዶቹ ጎረቤታሞች ደግሞ በዚሁ ኩባንያ መረጃ ሊቨርፑል 39.9 ሚሊዮን ታከታዮች ጠንካራ በሆነ ሁኔታ ቢከተልም፣ 4.2 ሚሊዮን ተከታዮች ባሉት ኤቨርተን ግን የሁለቱ ድምር የተከታዮች ቁጥርን 44.1 ሚሊዮን ላይ ብቻ እንዲገታ ያደርገዋል።

ከአራቱም ክለቦች ተጫዋቾች ዝላታን ኢብራሂሞቪች በ52.5 የተመዘገቡ ተከታዮቹ ቀዳሚ ሲሆን የክለብ አጋሩ ዋይኒ ሩኒ (48.7ሚሊዮን) እና የሲቲው ሰርጂዮ አግዌሮ (28.2 ሚሊዮን) ይከተላሉ።

በመርሲሳይድ የሊቨርፑሉ ዳንኤል ስተሪጅ 8 ሚሊዮን ተከታዮች ከሁለቱም ክለቦች ተጫዋቾች በቀዳሚነት ሲቀመጥ የክለብ ጓደኞቹ ፊሊፔ ኮቲንሆ (5.1 ሚሊዮን) እና ማማዱ ሳኮ (4.5 ሚሊዮን) የማህበራዊ ሚዲያው ተከታዮች ቀጣዮቹን ደረጃዎች ይይዛሉ።

የመጨረሻ ውጤት

የመርሲሳይዱ ቡድን 2-2 የማንችስተሩ ቡድን

እናም በሁለቱ የመርሲሳይድ እና ማንችስተር ጥምር ቡድኖች መከከል የሊግ ደረጀውን፣ የዋንጫ ክብርን፣ የማህበራዊ ሚዲያው ተከታዮች ቁጥርና የተመልካች ቁጥርን መሰረት በማድረግ ያደረግነው ፉክክር በአቻ ውጤት ተደምድሟል። ነገር ግን በእሁድ ዕለቱ ጨዋታስ የትኛው ጥምር ክለብ አሸናፊ ይሆን?

እርስዎስ ብልጫ አለው ብለው የሚያስቡት የትኛውን ነው? የመርሲሳይዱ ወይስ የማንችስተሩ ጥምር ቡድን? ሃሳቦን በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን በፌስቡክ ( http://www.facebook.com/ethioaddissport ) ወይም በትዊተር ( http://www.twitter.com/ethioaddissport ) ላይ ያጋሩን።

Advertisements
%d bloggers like this: