ጋቦን 2017: -የዲሞክራቲክ ኮንጎ ተጨዋቾች ልምምድ ላለመስራት አድማ መተዋል

By Eyob Dadi|ጥር 6 ቀን 2009 ዓም


በአፍሪካ ዋንጫ ላይ ለመሳተፍ ወደ ጋቦን ያቀኑት የዲሞክራቲክ ኮንጎ ተጨዋቾች ልምምድ ላለመስራት አድማ መተዋል።

ከሞሮኮ ጋር የመጀመሪያውን ጨዋታ የምታደርገው ኮንጎ በጥቅማጥቅም ክፍያ ምክንያት ልምምድ መስራት እንዳቆሙ ታውቋል።

የቡድኑ አምበል የኖርዊች ሲቲው ዮሱፍ ሙሉምቡ በጉዳዩ ላይ ሲናገር

“ከአመት አመት ተመሳሳይ ነገር ነው ያለው።ለጨዋታ  ጥሩ አድርገን ተዘጋጅተናል ነገርግን በመጨረሻ ላይ በቦነስ ላይ ሁልጊዜ ችግር አለ። ሲል ተናግሯል።

ችግሩንም ለመፍታት የአገሪቷ የስፓርት ሚኒስቴር ወደ ጋቦን ሌሎች ሀላፊዎችን እንደላኩ ተሰምቷል።

በክፍያ እና በጥቅማጥሞች ዙሪያ አድማ መምታት በአፍሪካ የተለመደ ነገር ሆኖ ቀጥሏል።

በዚሁ ሳምንት እንኳን የዙምባቡዌ ብሄራዊ ቡድን በቦነስ ክፍያ ምክንያት ወደ ጋቦን አንሄድም በማለት አድማ መተው እንደነበር ይታወሳል።

Advertisements