Skip to content
Advertisements

“ሊቨርፑል ወደ ሜዳ የገባው ለመከላከል ነበር ።” – ጆሴ ሞውሪንሆ


  በሚኪያስ በ. ወርዶፋ | እሁድ ጥር 7, 2009

የማንችስተር ዩናይትዱ አወዛጋቢ አሰልጣኝ ጆሴ ሞውሪንሆ ከዛሬው ምሽት የ 1-1  ውጤት በኃላ በሰጡት መግለጫ ሊቨርፑል ወደ ኦልትራፎርዱ ጨዋታ የመጣው ጥብቅ መከላከልን ለመተግበር እንደሆነ ተናግረዋል። 

ዩናይትድ በሜዳው ላይ ባደረገው ጨዋታ ለ 10ኛ ተከታታይ ጊዜ የሊግ ጨዋታ ድልን ቢያልምም የጄምስ ሚልነር የመጀመሪያ አጋማሽ የፍፁም ቅጣት ምት ጎል ስኬቱን አደናቅፋበታለች። ቡድኑን ከመሸነፍ ያዳነችውን ኳስም ስዊድናዊው የቡድኑ አጥቂው ኢብራሂሞቪች በ 84 ኛው ደቂቃ አስቆጥሮ የላንክሻየሩ ክለብ በአቻ ውጤት ጨዋታውን እንዲጨርስ አድርጓል። 

ከጨዋታው በኃላም በውጤቱ የተከፋት ጆሴ ሞውሪንሆ በፕሪምየር ሊጉ ላይ 49 ጎሎችን በማስቆጠር ዘንድሮ የሊጉን ብዙ ጎል የማግባት ደረጃ የተቆናጠውን የየርገን ክሎፕ ስብስብ ከዚህ ቀደም ጨዋታዎች በተለየ መልኩ ለመከላከል የመጣ መሆኑን በመግለፅ ወርፈውታል። 

ሞውሪንሆም “በጨዋታው ላይ አጥቅተን የተጫወትነው እኛ የነበርን ሲሆን ሊቨርፑል ግን ሲከላከል ነበር። የሚሰነዘሩብን ትችቶች ትክክል መሆናቸውን እንመልከት እስቲ። የነበረው ሁኔታው አዝናንቶኛል ነገር ግን በጨዋታው ላይ ሶስት ነጥብ ባለማግኘታችን በጣም ከፍቶኛል።” ሲሉ ለቢቢሲ ስፓርት ተናግረዋል።

ፓርቹጋላዊው በመቀጠልም “ሊቨርፑሎች ጎበዞች ነበሩ። ጊዜያቸውን በደንብ መጠቀም እና የጨዋታውን ግለት እንዴት መቆጣጠር እንደሚቻል አውቀዋል። በጨዋታው የመጨረሻዎቹ ደቂቃዎችም ላይም ሊረበሹ እንደሚችሉ ገብቷቸዋል።” ሲሉ ስለ ጨዋታም የተሰማቸውን ስሜት ገልፀዋል።  

በጨዋታው ላይ ሊቨርፑሎች ከፈጠሩት አነስተኛ የመልሶ ማጥቃት ሙከራ ውጪ ዩናይትድ በጨዋታው የበላይነት ላይ የአንበሳውን ድርሻ ወስዶ ታይቷል። በጨዋታው መጠናቀቂያ ላይም ኢብራሂሞቪች ከቫሌንሲያ ያገኛትን ኳስ ተጠቅሞ ቡድኑን አቻ ማድረግ ችሏል። 

ሞውሪንሆም “አንገቴን አሞኛል። ምክንያቱም ሙሉ ጊዜዬን ወደ ግራ ስመለከት ነበር።” ሲሉ በሁለተኛው አጋማሽ መጨረሻ አካባቢ ቡድናቸው የነበረውን አጥቆ የመጫወት ዝንባሌ ገልፀዋል። 

ውጤቱም ዩናይትድ ከምርጥ አራቱ በአራት ነጥብ ርቆ በነበረበት ስድስተኛነት እንዲቀጥል ሲያደርገው ከመሪው ቼልሲ የነበረው ልዩነትም ወደ 12 ሰፍቷል። ሊቨርፑል በበኩሉ በጨዋታው ላይ ባገኘው አንድ ነጥብ ታግዞ ደረጃውን በአንድ በማሻሻል ሶስተኛ በመሆን ከቼልሲ በሰባት ነጥቦች ርቆ ሳምንቱን ለመጨረስ ተገዷል።  

በሌላ በኩል ስለ ጨዋታው የተጠየቁት ጀርመናዊው የሊቨርፑሉ አለቃ ክሎፕ በጨዋታው ላይ ለዩናይትድ የአቻነት ጎል መመዝገብ የጭንቅላት ኳስ እገዛ ያደረገው ማርዋን ፌላኒ ከገባ በኃላ የቡድናቸው ተጫዋቾች ከተቀናቃኞቻቸው የሚመጡትን ረጅም ኳሶችን ለመቆጣጠር ተቸግረው እንደነበር ገልፀዋል።  

ከዚህ በተጨማሪም ተቀይሮ የገባው ዋይኒ ሩኒ በሚልነር ላይ በሰራው ከባድ ጥፋት ካርድ ባለመመልከቱ እድለኛ እንደነበረ ለሚወራው ሀሜትም በንዴት መልስ ሰጥተዋል።

ክሎፕም “ስለ ሁኔታው (ሩኒ ካርድ ባለማግኘቱ) እንዴት ልደነቅ እችላለሁ። በስታዲየሙ ጨዋታውን ለማየት በማይመች ቦታ ላይ ነበርኩ። ስለ ሁኔታው እናንተ ተደንቃችሁ ከነበረ ግን አንድ ውለታ ስሩልኝ። ያያችሁትን ነገር ፃፋት። ለምሳሌ አስቀያሚ ጥፋት ከነበረ ፃፋት። እኔ ስለ ጉዳዩ ስናገር ጠብቃችሁ ብቻ አትፃፋ።” ሲሉ ምሬታቸውን ገልፀዋል። 
 

Advertisements

ሚኪያስ በቀለ View All

ይህን ዘገባ ያቀረብኩላችሁ የኢትዮአዲስ ስፓርት ኤዲተርና ፀሀፊ እኔ ሚኪያስ በቀለ ነኝ።

%d bloggers like this: