Skip to content
Advertisements

የፕሪሚየር ሊጉ ስድስት የበላይ ክለቦች ባደረጓቸው የእርስርስ ግንኙነቶችን የበላይ የሆነው የትኛው ነው?

በ ወንድወሰን ጥበቡ | ማክሰኞ ጥር 8፣ 2009 ዓ.ም


ሊቨርፑል እሁድ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ባደረገው ጨዋታ ከኦልትራፎርድ ነጥብ ይዞ መመለሱ ምንም የሚደንቅ ነገር የለውም። ለምን ቢባል የየርገን ክሎፑ ቡድን ዋንጫውን ለማንሳት ከሚፎካከሩት ክለቦች ጋር ባደረጋቸው ጨዋታዎች የሰበሰባቸው ነጥቦች ከሊጉ ከፍተኛ ደረጃ ያላቸው ስድስት ክለቦች ሁሉ ከፍ ያለ ነው።

ሊቨርፑል በዚህ የውድድር ዘመን በፕሪሚየር ሊጉ አርሰናል፣ ቼልሲና ማንችስተር ሲቲን በማሸነፍ እና ከዩናይትድ ጋር ያደረጋቸውን ሁለት ጨዋታዎች እንዲሁም ከቶተንሃም ጋር ያደረገውን ጨዋታ ዳግሞ አቻ በመለያየት በሊጉ ከአንድ እስከ ስድስት ባለው ደረጃ ውስጥ ከሚገኙ ቡድኖች ጋር ባደረጋቸው ስድስት ጨዋታዎች 12 ነጥቦችን ማግኘት ችሏል። 

በእርግጥም ክሎፕ ከሊቨርፑል የቅርብ ተቀናቃኞች ጋር በሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ላይ ሁልጊዜም የበላይነትን እንደሚወስዱ እነዚህ ውጤቶች ማሳያ ናቸው። ከነዚህ ተቀናቃኞቻቸው ጋር ከሜዳቸው ውጪ ያደረጓቸውን ሰባት ጨዋታዎችም አልተሸነፉም።

ክሎፕ በትልልቅ ጨዋታዎች ላይ ተጫዋቾቹን እንዴት ማነሳሳት እንዳለበት የሚያውቅ መሆኑና የተመዘገቡ ውጤቶች ሊቨርፑል ስለምን በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ በሶተኛ ደረጃ ላይ እንደተቀመጠ የሚያሳዩ ማስረጃዎች ናቸው። ይህ መሆኑ ደግሞ የርገን ክሎፕ በሜዳቸው  ከቼልሲ፣ ቶተንሃምና አርሰናል ጋር የሚያደርጓቸውን ጨዋታዎች ጨምሮ  በቀጣዮቹ ስድስት ሳምንታት የሚያደርጓቸው የጨዋታ መርሃ ግብሮች መልካም ይሆኑላቸዋል። የዋንጫው ጫፍ ላይ የሚደርሱበርንም መንገድ የሚጠቁማቸው ሊሆን ይችላል።

ቼልሲ የፕሪሚየር ሊጉን ጎዳና በመሪነት እየተጓዘ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን የአንቶኒዮ ኮንቴው ቡድን በዚህ የውድድር ዘመን ከበላይ ስድስት ክለቦች ጋር ባደረጋቸው ጨዋታዎችና ሊያገኛቸው ይገቡ ከነበሩ 18 ነጥቦች ማግኘት የቻሉት ዘጠኙን ብቻ ነው።

አንቶኒዮ ኮንቴ ከእነዚህ ጨዋታዎቻቸው መካከልም አንዱ የሆነውና በመስከረም ወር በአርሰናል 3ለ0 በሆነ ውጤት የተሸነፉበት ጨዋታ አጨዋወታቸውን ወደ3-4-3 የታክቲክ ለውጥ በማድረግ በተከታታይ 13 ጨዋታዎችን ድል በማድረግ ራሳቸውን በደረጃ ሰንጠረዡ ጋር እንዲቀመጡ አድርጓቸዋል።

ሰማያዊዎቹ በታህሳስ ወር ማንችስተር ሲቲን 3ለ1 ሲረቱ በጥሩ አቋማቸው ላይ ይገኙ የነበረ ቢሆንም ምርጥ ጉዟቸው ግን በቶተንሃም የ2ለ0 ሽንፈት ሊገታ ችሏል።

ስፐርሶች በዚህ የውድድር ዘመን በሊጉ አናት ላይ ከተቀመጡ ስድስት ክለቦች ጋር ባደረጓቸው ስድስት ጨዋታዎች መሰብሰብ የቻሉት ስድስት ነጥብ ነው። ነገር ግን  ከእንግሊዝ የበላይ ክለቦች መካከል አንዱ የሆነውን ሲቲን በጥቅምት ወር 2ለ0 በመርታት የፔፔ ጋርዲዮላን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ የውድድር ዘመን የድል ጉዞ መግታት ችለዋል። 

በሌላ በኩል የማንችስተሮቹ ሁለት ክለቦች አብዛኛውን የውድድር ዘመን በትልልቅ ውድድሮች ላይ ተቸግረው አስሳልፈዋል። የጋርዲዮላው ሲቲ የውድድር ዘመኑ ጅማሮው ድንቅ ድል ባተቀዳጀበት ጨዋታ በኦልትራፎርድ 2ለ1 ዩናይትድን እንዲሁም በሜዳው አርሰናልን 2ለ1 ከራታበት ጨዋታ ውጪ ከበላይ ስድስት ክለቦች ጋር ያደረጋቸው ቀሪው ጨዋታዎች ከባድ ነበሩ። 

የሆዜ ሞሪንሆው ማንችስተር ዩናይትድም ከአብይ ተቀናቃኞቹ ጋር ያደረጋቸው ጨዋታዎች አስቸጋሪ ነበሩ። ምንም እንኳ ወቅታዊ ተከታታይ ድሎችን እያስመዘገበ ቢገኝም ምናልባትም በሰንጠረዡ ላይ በስድስተኛ ደረጃ ላይ ለመቀመጡ ምክኒያት ከትልልቆቹ ቡድኖች ጋር ያደረጋቸውን ጨዋታዎች አለማሸነፉ ሊሆን ይችላል።

ሊቨርፑል ከ ከበላይ ስድስት ክለቦች ጋር ያደረጋቸው

ነሃሴ 14 ከ አርሰናል (ከሜዳው ውጪ) – ድል 4-3

ነሃሴ 27  ከ ቶተንሃም (ከሜዳው ውጪ) – አቻ 1-1

መስከረም 16 ከ ቼልሲ (ከሜዳው ውጪ) – ድል 2-1

ጥቅምት 17 ከ ማን ዩናይትድ (በሜዳው) – አቻ 0-0

ጥቅምት 31 ከ ማን ሲቲ (በሜዳው) – ድል 1-0

ጥር 15 vs ማን ዩናይትድ (ከሜድው ውጪ) – አቻ 1-1

ከስድስት ጨዋታ 12 ነጥቦች

ቼልሲ ከ ከበላይ ስድስት ክለቦች ጋር ያደረጋቸው

መስከረም 16 ከ ሊቨርፑል (በሜዳው) – ተሸነፈ 1-2

መስከረም 24 ከ አርሰናል (ከሜዳው ውጪ) – ተሸነፈ 0-3

ጥቅምት 23 ከ ማን ዩናይትድ (በሜዳው) – ድል 4-0

ህዳር 26 ከ ቶተንሃም (በሜዳው) – ድል 2-1

ታህሳስ ከ ማን ሲቲ (ከሜዳው ውጪ) – ድል 3-1

ጥር 4 ከ ቶተንሃም  (ከሜዳው ውጪ) – ተሸነፈ 0-2

ከስድስት ጨዋታ 9 ነጥብ

ቶተንሃም ከ ከበላይ ስድስት ክለቦች ጋር ያደረጋቸው

ነሃሴ 27 ከ ሊቨርፑል (በሜዳው) – አቻ 1-1

ጥቅምት 2 ከ ማን ሲቲ (በሜዳው) – ድል 2-0

ህዳር 6 ከ አርሰናል (ከሜዳ ውጪ) – አቻ 1-1

ህዳር 26 ከ ቼልሲ (ከሜዳው ውጪ) – ተሸነፈ 1-2

ታህሳስ 11 ከ ማን ዩናይትድ (ከሜዳው ውጪ) – ተሸነፈ 0-1

ጥር 4 ቼልሲ (በሜዳው) – ድል 2-0

በስድስት ጨዋታ 8 ነጥብ

ማን ዩናይትድ ከ ከበላይ ስድስት ክለቦች ጋር ያደረጋቸው

መስከረም 10 ከ ማንሲቲ (በሜዳው) – ተሸነፈ 1-2

ጥቅምት 17 ከ ሊቨርፑል (ከሜዳቅ ውጪ) – አቻ 0-0

ጥቅምት 23 ከ ከቼልሲ (ከሜዳው ውጪ) – ተሸነፈ 0-4

ህዳር 19 ከ አርሰናል (በሜዳው) – አቻ 1-1

ታህሳስ 11 ከ ቶተንሃም (በሜዳው) – አሸነፈ 1-0

ጥር 15 vs ከሊቨርፑል (በሜዳው) – አቻ 1-1

ከስድስት ጨዋታ 6 ነጥብ

ማን ሲቲ ከ ከበላይ ስድስት ክለቦች ጋር ያደረጋቸው

መስከረም 10 ማን ዩናይትድ (ከሜዳ ውጪ) – ድል 2-1

ጥቅምት 2 ከ ቶተንሃም (ከሜዳው ውጪ) – ተሸነፈ 0-2

ጥቅምት 3 ከ ቼልሲ (በሜዳው) – ተሸነፈ 1-3

ታህሳስ 18 ከ አርሰናል  (በሜዳው) – ድል 2-1

ታህሳስ 31 ከ ሊቨርፑል (በሜዳው) – ተሸነፈ 0-1

ከአምስት ጨዋታ ስድስት ነጥብ

አርሰናል ከ ከበላይ ስድስት ክለቦች ጋር ያደረጋቸው

ነሃሴ 14 ከ ሊቨርፑል (በሜዳው) – ተሸነፈ 3-4

መስከረም 24 ከ ቼልሲ (በሜዳው) – አሸነፈ 3-0

ህዳር 6 vs ከቶተንሃም (በሜዳው) – አቻ 1-1

ህዳር 19 vs ማን ዩናይትድ (ከሜድው ውጪ) – አቻ 1-1

ጥቅምት 18 ከ ማን ሲቲ (ከሜዳው ውጪ) – ተሸነፈ 1-2

ከአምስት ጨዋታ 5 ነጥብ


 

የዋንጫውን አሸናፊ እና ከ1-4 ያለውን ደረጃ የሚወስኑ ጨዋታዎች

ጥር 21፡ ማን ሲቲ ከ ቶተምሃም

ጥር 31: ሊቨርፑል ከ ቼልሲ

የካቲት 4: ቼልሲ ከ አርሰናል

የካቲት 11: ሊቨርፑል ከ ቶተንሃም

የካቲት 26: ማን ሲቲ ከ ማን ዩናይትድ 

መጋቢት 4: ሊቨርፑል ከ አርሰናል

መጋቢት 18: ማን ሲቲ ከ ሊቨርፑል

ሚያዝያ 1: አርሰናል ከ ማን ሲቲ

ሚያዝያ 5: ቼልሲ ከ ማን ሲቲ 

ሚያዝያ 15: ማን ዩናይትድ ከ ቼልሲ

ሚያዝያ 29: ቶተንሃም ከ አርሰናል

ግንቦት 6: አርሰናል ከ ማን ዩናይትድ

ግንቦት 13: ቶተንሃም ከ ማን ዩናይትድ 

* የተጠቀሱት ቀኖች በአውሮፓውያኑ የቀን ቀመር መሰረት ነው።

ዩናይትድ በሲቲና በቼልሲ ከመሸመነፉም ባሻገር ከሊቨርፑል ጋር ያደረገውን የእሁድ ዕለቱን ውጤት ጨምሮ ሶስት ጨዋታዎችን በአቻ ውጤት ጨርሷል። ብቸኛ ድሉም በታህሳስ ወር ቶተንሃምን 1ለ0 የረታበት ነው።

አርሰናል ከመሪዎቹ ክለቦች ጋር ያደረጋቸው ጨዋታዎች አምስት ብቻ ናቸው። ነገር ግን ከእነዚህ ጨዋታዎች ሊያገኝ ይችልባቸው ከነበሩ 15 ነጥቦች በሊቨርፑልና በሲቲ በመሸነፍ ማግኘት የቻለው 5 ነጥቦችን ብቻ ነው።

እነዚህ የበላይ ስድስት ክለቦች መካከል ያለው ልዩነት መልሶ እንዲጠብ አሊያም ይበልጥ እንዲሰፋ ቼልሲ ሊቨርፑልና አርሰናልን እንዲሁም ሊያሸንፋቸው ይችልባቸዋል የተባሉ ከኸል ሲቲ፣ በርንሌይና ስዋንሲ ጋር የሚያደርጋቸው ጨዋታዎች ከፊቱ ይጠብቁታል።

ከለንደኑ ተቀናቃኛቸው በሰባት ነጥቦች ርቀት ላይ ተከትለው የሚገኙት ስፐርሶች በመጪው ቅዳሜ ከሲቲ ጋር የሚያደርጉትን ጨዋታ ተከትሎ ከሰንደርላንድና ሚድልስብሮ ጋር ከተጫወቱ በኋላ ወሳኝ የሆነውን ጨዋታቸውን ለማድረግ ወደሊቨርፑል ይጓዛሉ።

አርሰናል በበኩሉ  ወደስታንፎርድ ብሪጅ የሚያመራበትን (እ.ኤ.አ)የካቲት 4 ቀንን በከላንደሩ ላይ በቀይ ከቦ ይገኛል። ነገር ግን ሁለቱም ክለቦች ከበርንሌይ፣ ዋትፎርድ፣ ኸል ሲቲና ሳውዛምፕተን ጋር ከሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ብዙ ነጥቦችን መሰብሰብ ይጠበቅባቸዋል።

ጋርዲዮላ የሲቲ የዋንጫ ፉክክር እንዳበቃለት ቢናገርም ነገር ግን ከፊቱ የሚጠብቀውንና ከቶተንሃም፣ ከስዋንሲ፣ ቦርንማውዝ ከዚያም ከዩናይትድ ጋር የሚያደርጋቸውን ጨዋታዎችን ማሸነፍ የሚችል ከሆነ አሁን ያለው ሃሳብ ተቀይሮ ጉዳዩ ሌላ ሊሆን ይችላል።

ማንችስተር ዩናይትድ ደግሞ ያለመሸነፍ ጉዞውን ከፊቱ የሚጠብቁትንና ከስቶክ፣ ኸል፣ ሌስተርና ዋትፎርድ ጋር የሚያደርጋቸውን ጨዋታዎች የግድ በማሸነፍ ማስቀጠል ይጠበቅበታል።

Advertisements
%d bloggers like this: