Skip to content
Advertisements

አፍሪካ:-የሰንዳውንሱ ኪጋን ዶሊ ወደ ፈረንሳይ ሊያቀና ነው፣ጓደኞቹን ተሰናብቷል።

By Eyob Dadi|ጥር 11,2009 ዓም


ደቡብ አፍሪካ ካፈራቻቸው የግራ እግር ተጨዋቾች ውስጥ ምርጥ እንደሆነ እየተነገረለት ያለው ኪጋን ዶሊ ወደ ፈረንሳይ ሊያቀና ነው።

<!–more–>

ወጣቱን አስደናቂ የማሜሎዲ ሰንዳውንስ የመስመር ተጨዋች ዶሊን ለማዘዋወር የፈረንሳዩ ሞንፔሌ ጣጣውን እንደጨረሰ ነው የተሰማው።

ተጨዋቹም ዛሬ በፕሪቶሪያ ተገኝቶ ጓደኞቹን መሰናበቱ ታውቋል።

የፈረንሳዩ ሞንፔሌ የተጨዋቹን የውል ማፍረሻ ሟሟላት በመቻሉ ቀሪዎቹ የግል ጥቅማጥቅሞች በተጨዋቹ እጅ ላይ ወድቀዋል።

ቢሊያት እና ዶሊ

ከፈረንሳይ በወጣው መረጃም ሞንፔሌ በግል ጥቅማጥቅም ዙሪያም ከተጨዋቹ ጋር በመስማማቱ ነገ ህክምና እንዲያደርግ ቀጠሮ ተይዞለታል።

ይህን ተጨዋች በ2016 የካፍ ቻምፕየንስ ሊጉ ላይ የነበረው ብቃት አስደናቂ የነበረ ሲሆን ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ዋንጫ እንዲያነሳ ቁልፍ ሚና ነበረው።

 

Advertisements
%d bloggers like this: