Skip to content
Advertisements

ምልከታ: በዚህ ሳምንት በሚደረጉ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ላይ ትኩረት ሊሰጥባቸው የሚገቡ አምስት ነገሮች 

በሚኪያስ በ. ወርዶፋ | ቅዳሜ ጥር 13, 2009

​1.ስቶክ ሊተ ማመንበት የማይገባው ዩናይትድ በበኩሉ ርህራሄ አልባ እንዲሆን የሚጠበቅበት ጨዋታ

ዩናይትድ ብሪታኒያ ስታዲየምን ለመጎብኘት በተዘጋጀበት በዚህ ሰአት ስቶክ ዘንድሮ ከትልልቆቹ የሊጉ ክለቦች ጋር ያለውን ሪከርድ ለተመለከተ ሰው ማርክ ሂውዝም ሆነ ሞውሪንሆ ትኩረት ሊያደርጉበት የሚገባ ጨዋታ መሆኑን ይገነዘባል።

ስቶክ ከሊጉ አምስት ታላላቅ ክለቦች ጋር ያለው የእርስ በርስ ውጤት በጣም አስቀያሚ ሲሆን ከስድስት ጨዋታዎችም አምስት ያህሉን በከፍተኛ የጎል ልዩነት ተረቷል። ስቶኮች በአርሰናል 3-1፣ በቼልሲ 4-2 እና በሊቨርፑል 4-1 ሲረቱ በሲቲና ቶትነሀም በተመሳሳይ መልኩ 4-0 ተሸንፈዋል።

ከአርሰናልና ሊቨርፑል ጋር ጨዋታውን እየመሩ ከቼልሲ ጋር ደግሞ ሁለት ጊዜ አቻ መሆን ቢችሉም ስቶኮች በደካማው የተከላካይ ክፍላቸው ምክንያት በጨዋታዎቹ ላይ ብዙ ጎል ተቆጥሮባቸው ትልቅ ዋጋ ከፍለዋል።ከእነዚህ የስቶክ የሽንፈት መንስኤ ታላላቅ ክለብ ዝርዝሮች ውስጥ የሌለው ዩናይትድ ብቻ ነው። ስቶክ በጥቅምቱ የኦልትራፎርድ ግጥሚያ በአስደናቂ አጨራረስ ከላንክሻየሩ ክለብ ጋር 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ጨዋታውን መፈፀም ችሏል።

ከነገው ጨዋታ በፊትም ስቶኮች ከትልልቆቹ ጋር ያላቸውን ተከታታይ ሽንፈት ላይ ትኩረት መስጠት ሲገባቸው ቀያዮቹ ሴይጣኖች በበኩላቸው በቀጣዩ አመት ወደ ቻምፒዮንስ ሊግ መመለስ ከፈለጉ ርህራሄ አለብ መሆን እንዳለባቸው ሊያስቡበት ይገባል።2.ጂሰስ የሲቲን የፕሪምየር ሊግ ጉዞ ማዳን ይችል ይሆን ?

ከኤቨርተኑ አሳፋሪ ሽንፈት በኃላ ጋርዲዮላ በቡድኑ ውስጥ አዲስ ጣልቃገብ ተጫዋች ካስፈለገው እድለኛ ሊሆን ይችላል። ምክንያቱም ደግሞ ከሀይማኖታዊ ምክንያት ጋር በተያያዘ 33 ቁጥር ማሊያን ለማጥለቅ የተዘጋጀው ታዳጊው ብራዚላዊ ኮከብ ጋብሪየል ጂሰስ በነገው የቶትነሀም ጨዋታ ለመሰለፍ ብቁ ሆኖ ተገኝቶለታል።

ከፔሌግሪኒ የተቀበለውን ጠንካራ ሲቲ በተለመደው መልኩ ማስቀጠል ያቃተው ጋርዲዮላ ኑሮ በኢትሀድ የከበደው ሲሆን በክረምት ያስፈረማቸው ተጫዋቾችም ወጥ አቋም ማሳየት ተስኗቸው ችግር ውስጥ ይገኛል።

ጆን ስቶንስና ክላውዲዮ ብራቮ ከባድ የአቋም መውረድ ውስጥ ሲገኙ፣ ኢካይ ጉንዶጋን የውድድር አመቱን ከጨዋታ ውጪ የሚያደርገው ጉዳት አጋጥሞታል፣ ኖሊቶ በመጀመሪያ አካባቢ የነበረው ተፅዕኖ እየወረደ ሲመጣ የሊሮይ ሳኔም አስደናቂ ብቃት ብልጭ ብሎ ጥፍት የሚል ሆኗል።

ስለዚህም ጂሰስ ከተሰለፈ ጋርዲዮላ የቶትነሀሙ ተከላካይ ጃን ቬርቶገንን በጉዳት በማይሰለፍበት ጨዋታ እድሉን በአግባቡ መጠቀምና ውጤታማ መሆን እንደሚችል ያምናል።3. የክሎፕ ከኦሪጊና ስቱሪጅ አንዱን የመምረጥ ፈተና

ሊቨርፑሎች አሁንም የሊጉ ባለብዙ ግብ ክለብ ናቸው። ነገር ግን ካለፋት ሳምንታት ጀምሮ የጎል ድርቅ የመታቸው ሲሆን በመጨረሻ ስድስት ጨዋታዎቻቸውም ያስቆጠሩት አምስት ጎሎችን ብቻ ነው። ከስድስቱ ጨዋታዎች ሁለቱ ክሎፕ ደካማ ቡድናቸውን ያሰለፋበት የኤፍካፕ ጨዋታዎች መሆኑ የሚታወስ ቢሆንም።

እነዚህ ጨዋታዎች ግን ከዚህ ጋር የሚፃረሩ አይደሉም። ምክንያቱም በሁለቱም የኤፍኤ ካፕ ጨዋታዎች ኦሪጊ ቋሚ ተሰላፊ የነበረ ሲሆን ዳንኤል ስቱሪጅም በሆም ፓርኩ ጨዋታ ለ 76 ተስፋ አስቆራጭ ደቂቃዎች በሜዳ ላይ ቆይቷል።

በዘጠኝ ግብ የሊጉ የዘንድሮ አመት የክለቡ ኮከብ ግብ አግቢ የሆነውን ሳዲዮ ማኔን በጋቦኑ የአፍሪካ ዋንጫ ምክንያት ማጣታቸው ቀያዮቹን ትልቅ የጎል ድርቅ ውስጥ የከተታቸው ሲሆን ሴኔጋል በውድድሩ የመቆየቷ እድል መስፋቱ ደግሞ ይበልጥ ይጎዳቸዋል።

ክሎፕ ቡድኑ ሲቲን በረታበት ግጥሚያ ኦሪጊና ስቱሪጅን ከምርጥ 11 ውጪ አርገዋቸው ነበር። ነገር ግን ሳይጠበቅ በፕሌይማውዙ ግጥሚያ ሁለቱንም በቋሚነት ጨዋታውን እንዲጀምሩ አድርገዋቸዋል። ነገር ግን ሁለቱ አጥቂዎች በጨዋታው ላይ መቀናጀት ሳይችሉ ቀርተዋል። ኦሪጊ ከዩናይትድ ጋር በነበረው ጨዋታም የመሰለፍ እድል ቢያገኝም የስምንት ተከታታይ የጎል ማግባት ድርቁ ቀጥሎ ታይቷል።

ስቱሪጅ በበኩሉ ከሰንደርላንድና ስቶክ ጋር በነበረው ጨዋታ የጎል መረቡን መድፈር ችሏል። ነገር ግን በአንፊልድ ቆይታው ዙሪያ ትልቅ ጥርጣሬ ሰፍኗል። ነገር ግን የተከላካይ ክፍሉ ደካማ የሆነውን ስዋንሲ በሚገጥሙበት የነገው ፍልሚያ ክሎፕ ከሁለት አንዱን የመጀመሪያ የፊት አጥቂ ተመራጭ አድርገው ወደ ቡድናቸው ምርጥ 11 ትክክለኛው ጊዜ የደረሰ ይመስላል።4. ቬንገር በቡድናቸው ውስጥ ስሜታዊነት እንዲጨምር መፍቀድ የለባቸው።  

ባሳለፍነው ሳምንት አርሰናል ስዋንሲን በሰፊ ጎል እየመራና ማሸነፋን ቀደም ብሎ ባረጋገጠበት ወቅት ነበር የሳንቼዝ ስም ያለበት የቅያሪ ሰሌዳ የታየው። ይህ ግን ቺሊያዊውን ተጫዋች በሚቀየርበት ወቅት በከፍተኛ ደረጃ ስሜታዊ ከመሆንና ውሳኔውን ከመቃወም አላገደውም።

ቬንገር ስለ ተጫዋቹ ሁኔታ ብዙም ትኩረት ባለመስጠት ይህ ሁኔታ የተከሰተው ከተጫዋቹ በእያንዳንዱ ደቂቃ ተሰልፎ ከመጫወት ፍላጎት እንጂ አሰልጣኙን በአደባባይ ለማንኳሰስ ፈልጎ አለመሆኑን አፅንኦት ለመስጠት ሞክረዋል። ነገር ግን እንደዚህ አይነት ያልተገቡ ስሜታዊነቶች ቡድኑን ነገ አመሻሽ በሚያደርገው የበርንሌይ ጨዋታ እንዲጎዱት ቬንገር መፍቀድ የለባቸውም።

እነዚህ ነገሮችም ከዚህ በፊት ያለውን የተጫዋቹን አጋጣሚ በማስታወስ ማረጋገጥ ይገባል። ቬንገር ከዚህ በፊት ተጫዋቹ ሰውነቱ በተደጋጋሚ ጨዋታዎች ዝሎ “ቀይ ዞን” ውስጥ እንደሆነ እየተናገሩ ባለበት ሰአት ሁሉ ተጫዋቹን ወደ ሜዳ አስገብተው አጫውተውታል።

ነገር ግን ማንም በሳንቼዝ ደረጃ የመጫወት ቁርጠኝነት ያለው ተጫዋች ቢሆን ገደብ አለው። ቬንገርም ከየካቲት መጀመሪያው የቼልሲ ጨዋታ በፊት ለምን ለአጥቂያቸው እረፍት መስጠት እንዳለባቸው ባሳለፍነው አመት እንዴት የውድድሩ መጨረሻ አካባቢ ከሊጉ ዋንጫ ፋክክር ሩጫ እንደቀሩ መለስ ብለው በማሰብ ከስህተታቸው ሊማሩ ይገባል።5. ኮስታ ወደ ቼልሲ ምርጥ 11 ለመመለስ መታገስ ሊኖርበት ይገባው ይሆናል

ለቼልሲ የህክምና አባላት ምስጋና ይግባና ኮስታ ባሳለፍነው ሳምንት ከሌስተር ጨዋታ ውጪ ያደረገው የጀርባ ህመም ተቀርፎለታል። ጣሊያናዊው አለቃ አንቶኒዮ ኮንቴም በሁኔታው ደስተኛ ሆነዋል።

ነገር ግን ተጫዋቹን ከሁል ሲቲ በሚደረገው ጨዋታ ዳግም ወደ ሜዳ ማስገባታቸው ወይም ደግሞ በሌስተሩ ጨዋታ እንደነበረው ኤደን ሀዛርድን በዘጠኝ ቁጥር ሚና ዳግም በጨዋታው ላይ ማስጀመራቸው ነገ የሚታይ ይሆናል። 

በሌስተሩ ጨዋታ ኮንቴ ከፔድሮ ዳርና ዳር ባሉት ክንፎች ፔድሮንና ዊሊያንን በማሰለፍ ድንቅ ጥምረት መፍጠር የቻሉ ሲሆን ጨዋታውንም 3-0 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል። በእለቱ የነበረው የፔድሮና ዊሊያን ብቃትም ኮስታ በቅያሪ ወንበር ላይ ሆኖ ወደ ቡድኑ ዳግም መመለሻው ትክክለኛ ጊዜ እስኪደርስ በትግስት እንዲጠብቅ ሊያስገድድው ይችል ይሆናል።

Advertisements

ሚኪያስ በቀለ View All

ይህን ዘገባ ያቀረብኩላችሁ የኢትዮአዲስ ስፓርት ኤዲተርና ፀሀፊ እኔ ሚኪያስ በቀለ ነኝ።

%d bloggers like this: