Skip to content
Advertisements

ጋዜጣዊ መግለጫ : ፈረንሳዊው አለቃ በብዙ ጉዳዮች ዙሪያ መልስ ሰጥተዋል። 

በሚኪያስ በ. ወርዶፋ | ሀሙስ ጥር 18, 2009

1. አዲስ ዜና በቡድናቸው ዙሪያ

“ምንም እንኳን ዣካን በቅጣት ብናጣም ዋልኮት ወደ ቡድኑ ተመልሷል። ሌላው ጥሩው ነገር ሜርትሳከርና ድቡቺ ነገ ወደ ተሟላ የልምምድ መርሀ ግብር ይመለሳሉ። እስካሁን ማን እንደሚሰለፍና ማን እንደማይሰለፍ ገና አልወንኩም። በአብዛኛው የዋናው ልምድ ያላቸው ተጫዋቾችን እጠቀማለሁ። ከዛ ውጪ አንድ ወይም ሁለት የወጣት ቡድን ተሰላፊዎችን ላካትት እችላለሁ።

2. በሳውዛምፕተን ዙሪያ

ሳወዝአምፕተኖች በትናንትናው ምሽት የሊቨርፑል ጨዋታ ከባድና በጣም አሪፍ የሚጫወቱ ነበሩ። ይህም ጨዋታችንን በጣም አስቸጋሪና አጓጊ ያደርገዋል።

3. በዣካ ዙሪያ

“በእሱ ዙሪያ ሁለት ነገሮች እንደተፈጠረ ተወርቷል። ድጋሚ ተመልከቱት ቀይ ካርዱ በጣም ከባድ ነው። እሱ በተፈጥሮ ታላቅ ሸርተቴ ወራጅ አይደለም። የሸርተቴ አወራረድ ክህሎት የለውም። ሌላኛውንና ከሜዳ ውጪ የተፈጠረውን አጋጣሚ ሙሉ ለሙሉ ክዷል። ስለሁኔታው አናግሬው ምንም እንዳልተፈጠረ ነግሮኛል። ትልቅ ቁርጠኝነትና የሚያምር ባህሪ አለው። የተወራበት ነገርም አለመፈጠሩን ነግሮኛል።”

4. በዝውውር ዙሪያ

“ምንም አይነት አዲስ ተጫዋች ለማስፈረም የተንቀሳቀስነው ነገር የለም።”

5. በድቡቺ ዙሪያ

“ጋብሪየል በቀኝ ክንፍ ላይ እራሱን ማስመስከር ችሏል። በሩን አልዘጋም አሁን ብቁ መሆን ስለቻለ ለጨዋታ ዝግጁ ነው።

6. በጄኪንሰን ዙሪያ

“ወደ ሌላ ክለብ ለመዘዋወር (ክሪስታል ፓላስ) የግል ጥቅማ ጥቅሞቹ ዙሪያ መስማማት ብቻ ነው የሚቀረው። እስከ አሁን ግን ስምምነት ላይ ሊደርስ አልቻለም።”

7. ስለ እገዳቸው

“ባለፋት 20 አመታት በእንግሊዝ አሳልፌያለሁ። በቅያሪ ወንበር ላይ ብዙ ነገር አይቻለሁ። ጥሩ ስንሆንም ሳንሆንም ከመቀመጫዬ ተነስቼ ለመቆም ከበቂ በላይ ነኝ። በጣም ስሜታዊ ሰው ነኝ። እንደማስበውም ለስራዬ ትልቅ ቦታ የምሰጥና ሁሉንም የፕሪምየር ሊግ አሰልጣኞች የምወድ ነኝ። በአካል ከቡድኔ ጋር በቅርበት መገኘት እፈልጋለሁ። የማደርገውም ነገርም ‘ልክ ነው’ ወይም ‘አይደለም ለማለት’ ከበቂ በላይ ነኝ። በዚህም ምክንያት የፈፀምኩት ነገር ስህተት መሆኑን ለመናገር በጣም በቂ ነኝ።

8. ስለሚጠብቃቸው ቅጣት

“በአደባባይ ምን ማለት እንዳለብኝ ያሰብኩትን ተናግሬያለሁ። ስለመቀጣቴና እንዴት ልቀጣ እንደምችል የማውቀው ነገር የለም።”

9. ስለ ቡድናቸው የመጨረሻ የመፋለም ብቃት

አርሰናል ከበርንሌይ ጋር አስገራሚ የመጨረሻ ደቂቃ ፍልሚያን ባሳለፍነው ሳምንት እሁድ አሳይቷል። ፈረንሳዊው አለቃ ስለ ጉዳዩ ሲናገሩም “ይህ ቡድን በጣም አስፈላጊ የሆኑ ብቃቶችን አሳይቷል። ድካም አልባና ሆነን ጉዟችንን ቀጥለናል። ከማንም በላይ በመጨረሻ የጨዋታ ደቂቃዎች ብዙ ጎሎችን ማስቆጠር ችለናል። በጣም ትልቅ አንድነት በዚህ ቡድን ውስጥ ይገኛል።” ሲሉ ቡድናቸውን አሞካሽተው ተናግረዋል።

10. በናብሪ ዙሪያ

ይህ ተጫዋች ወደ ኢምሬትስ እንደሚመለስ እየተወራ ይገኛል። ቬንገር ሲመልሱም “እሱን ለብሬመን ሸጠነዋል። በዚህ ሰአት እሱን ድጋሚ አላስፈረምነውም።” በማለት ተናግረው ጋዜጣዊ መግለጫቸውን አጠቃለዋል።

Advertisements

ሚኪያስ በቀለ View All

ይህን ዘገባ ያቀረብኩላችሁ የኢትዮአዲስ ስፓርት ኤዲተርና ፀሀፊ እኔ ሚኪያስ በቀለ ነኝ።

%d bloggers like this: