Skip to content
Advertisements

አጫጭር ወሬዎች : የአርብ አመሻሽ የአውሮፓ ጋዜጦች የዝውውርና ሌሎች አዝናኝና አጓጊ ወሬዎች

በሚኪያስ በ. ወርዶፋ | አርብ ጥር 19, 2009

የሲቲው አለቃ ፔፔ ጋርዲዮላ የአርሰናሉን ቀኝ ተከላካይ ሄክቶር ቤለሪንን ለማስፈረም አሁንም ይፈልጋል። (ታይምስ)

የዌስትሀሙ አማካኝ ዲሜትሪ ፓዬት ጉዳት ገጥሞት ከማርሴይ ዝውውሩ እንዳያስቀረው በማሰብ ከ 23 አመት በታች የቡድኑ ስብስብ ጋር መጫወቱን አቆመ። (ዘ ሰን)

ዌስትሀሞች በፓዬት ዙሪያ ያላቸው አቋም እንደተለሳለሰና ከፈረንሳዩ ክለብ የቀረበውን የተሻሻለውን 30 ሚሊዮን ፓውንድ ለመቀበል እያሰቡ ይገኛል። (ዴይሊ ሚረር)

ክሪስታል ፓላስ ከኮንትራት ውጪ የሆነውን የቀድሞውን የዩናይትድ ተጫዋች ጋብሬል ኦቤርታን ሊያስፈርም አስቧል። (ዘ ሰን)

የዩናይትዱ አለቃ ጆሴ ሞውሪንሆ በእሁዱ የዩናይትድ የኤፍኤ ዋንጫ ላይ መሰላቸት ውስጥ ለሚገኘው ታዳጊው አጥቂያቸው አንቶኒ ማርሻል የቋሚ ተሰላፊነት እድል ለመስጠት አስበዋል። (ሜትሮ)

የማድሪዱ አጥቂ አልቫሮ ሞራታ ከአሰልጣኙ ዚነዲን ዚዳን ጋር መቃቃር ውስጥ መግባቱ የተጫዋቹን ፈላጊዎች አርሰናልና ቼልሲን የዝውውር ጥያቄ ለማቅረብ አነሳስቷቸዋል። (ዘ ሰን)

የስፓርታክ ሞስኮ ክንፍ አማካኝ ኪዊንሲ ፕሮምስ በሊቨርፑል እንደሚፈለግ ቢወራም ስለ ሌሎች ክለቦች እንደማያስብ ተናግሯል። (ስፓርት ኤክስፕረስን ገልፆ ጎል እንደፃፈው)

ሪዮ ፈርዲናንድ የቀድሞ ክለቡ ዩናይትድ አንቶኒ ግሪዝማንና ጋሬዝ ቤልን እንዲያስፈርም ጠይቋል። ለዚህም የኦልትራፎርዱ ክለብ ለዝውውሩ በቂ ገንዘብ እንዳለው ጨምሮ ገልጿል። (ዘ ሰን)

ዩናይትድ የክለቡ አማካኝ ፓል ፓግባ ጓደኛነቱን ተጠቅሞ አንቶኒ ግሪዝማን ወደ ኦልትራፎርድ እንዲመጣ በማሳመን መልኩ እንደሚያግዘው ተስፋ አድርጓል። (ዴይሊ ሪከርድ)

አርሰናል በክለቡ ደስተኛ ያልሆነውን አሌክሲ ሳንቼዝን ለመተካት በውድድር ዘመኑ መጨረሻ ለዶርትሙንዱ አጥቂ ማርኮ ሩስ የ 51 ሚሊዮን ፓውንድ ጥያቄ ሊያቀርብ ነው። (ሁስኮርድ)

የዩናይትዱ አለቃ ጆሴ ሞውሪንሆ የማድሪዱ ፕሬዝዳንት ጥብቅ ወዳጅ መሆናቸውንና የስፔኑ ክለብ በውጤት መንሸራተቱ ከቀጠለ ዚዳንን ለመተካት ሊታጩ እንደሚችሉ ተነግሯል። (ዶንባሎንን ጠቅሶ ኤክስፕረስ እንደፃፈው)

ዋይኒ ሩኒ ከቻይናው ክለብ ሻንጋይ ሺንዋ አማላይ የ 600,000 ፓውንድ ሳምንታዊ ደሞዝ ቀረበለት። (ዘ ሰን)

በሞውሪንሆ እድሉን በአግባቡ መጠቀም እንደማይችል ትችት የደረሰበት የክለቡ አጥቂ አንቶኒ ማርሻል በፓርቹጋላዊው ስር ባለው ቆይታው ተስፋ ቆርጧል። (ታይምስ)

ሰንደርላንድ የ 26 አመቱን የቦርዶክስ ግራ ተከላካይ ዲያጎ ኮንቴንቶን ለማስፈረም የፈረንሳዩን ክለብ እያናገረ ይገኛል። (ስካይ ስፓርት)

ወደ ኢንተር ለማምራት መንገድ ላይ የሚገኘው የዩናይትዱ ቀኝ ተከላካይ ማቲው ዳርሚያን በሚላን ከተማ ቤት እየፈለገ ነው። (ዘ ሰን)

የቼልሲው ሰርቢያዊ ተከላካይ ብራኒስላቭ ኢቫኖቪች ወደ ዜኒት ሴንት ፒተርስበርግ ለማምራት በድርድር ላይ ነው። (ዴይሊ ሜይል)

በረኛ ለማስፈረም እየተንከራተተ የሚገኘው የሰማያዊዎቹ አለቃ አንቶኒዮ ኮንቴ የጄኖዋውን በረኛ ማቲያ ፔሪንን በግዢ አማራጩ ውስጥ አስገብቷል። (ዴይሊ ስታር)

ሮበርት ሶንድግራስ በ 10 ሚሊዮን ፓውንድ ከሁል ወደ ዌስትሀም ለመዘዋወር በዛሬው እለት የህክምና ምርመራውን እያደረገ ይገኛል። (ዘ ጋርዲያን)

ዌስትሀምና ሴልቲክ የፈነርባቼውን ተከላካይ ሀሰን አሊ ካልድሪምን ለማስፈረም ፉክክር ላይ ናቸው። (ያሆ ስፓርት)

የሳውዝአምፕተን ባለቤቶች ክለቡን ለመግዛት ከቻይና የቀረበውን 180 ሚሊዮን ፓውንድ ውድቅ አደረጉ። ባለቤቶቹ ለክለቡ ግዢ የቀረበው ገንዘብ ከሚጠብቁት ዋጋ በ 90 ሚሊዮን ፓውንድ ያነሰ መሆኑን ገልፀዋል። (ዘ ሰን)

የአርሰናሉ ቀኝ ተከላካይ ማቲው ደቡቺ የመድፈኞቹን ክለብ መልቀቅ እንደሚችል ከተነገረው በኃላ ወደ ሀገሩ የፈረንሳይ ክለቦች ለመመለስ ጥረት እያረገ ነው። (ዴይሊ ሚረር)

በመጨረሻም …

የዩናይትዱ አለቃ ጆሴ ሞውሪንሆ የ 54ኛ አመት ልደታቸውን ከትናንትናው ምሽት የሊግ ካፕ ጨዋታ በኃላ በክለቡ አውቶብስ ውስጥ ኬክ ቆርሰውና ሻምፓኝ ከፍተው አክብረዋል። (ዘ ሰን)

ፈርዲናንድ ባሳለፍነው ጥቅምት ገና 31ኛ አመት ልደቱን ያከበረው የቀድሞ የቡድን አጋሩ ዋይኒ ሩኒ ሲታይ የ 40 አመት ጎልማሳ እንደሚመስል ተናገረ። (ዴይሊ ስታር)

Advertisements

ሚኪያስ በቀለ View All

ይህን ዘገባ ያቀረብኩላችሁ የኢትዮአዲስ ስፓርት ኤዲተርና ፀሀፊ እኔ ሚኪያስ በቀለ ነኝ።

%d bloggers like this: