Skip to content
Advertisements

በራሂኖ ለመዝናኛ ብሎ በወሰደው አበረታች መድሃኒት ምክኒያት የስምንት ሳምንት “የጨዋታ ቅጣት” ተጥሎበት እንደነበር ማርክ ሂዩዝ ገለፁ

በ ወንድወሰን ጥበቡ | አርብ ጥር 26፣ 2009 ዓ.ም

ሳይዶ በራሂኖ “በእንግሊዝ እግርኳስ ማህበር የስነምግባር ጉዳይ” የስምንት ጨዋታዎች ቅጣት እንደተላለፈበት የስቶኩ አሰልጣኝ ማርክ ሂዩዝ ገልፀዋል።

በ12 ሚሊዮን ፓውንድ በተጠናቀቀው የጥር ወር የዝውውር መስኮት ከዌስት ብሮምዊች አልቢዮን ስቶክ ሲቲን የተቀላቀለው አጥቂ ቅጣቱ ተግባራዊ የሆነበት ከቤጊሶቹ ጋር በነበረው በዚህ የውድድር ዘመን መጀመሪያ ላይ ነበር።

ስካይ ስፖርት ምንጮቼ አረጋገጡልኝ ብሎ እንዳወጣው መረጃ ከሆነ ደግሞ በራሂኖ ለመዝናኛ ተብሎ የሚዋጥ አበረታች መድሃኒት መውሰዱ በደሙ ውስጥ ተገኝቷል።።

“ይህን በሚገባ እናውቃለን። በእግርኳስ ማህበሩ የስነምግባር ጉዳይ ላይ እንደነበረ እና ሳይዶ የስምንት ወራት ቅጣት እንደተጣለበት እናውቅ ነበር።” ሲሉም ማርክ ሂዩዝ ስለጉዳዩ ተናግረዋል።

“እሱን ከማስፈረማችን በፊትም ግንዛቤው ነበረን። ለተጨማሪ ማብራሪያ ግን ወደቀሞው ክለቡ ተመልሳችሁ ማረጋገጥ ትችላላችሁ። እኛ በሌለን ነገር ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ መስጠት የምንችልበት ሁኔታ ላይ አንገኝም።” ሲሉ ማርክ ሂዩዝ ገልፀዋል።

“እሱ በቀድሞው ከለቡ ውስጥ ለ18 ወራት ያህል ግልፅ የሆነ ችግር ነበረበት። ከማስፈረማችን በፊት እንደማምኛውም ተጫዋችም በእሱ ላይ የራሳችንን ጥናት አድርገናል። ነገር ግን ይህ ያለንን ሃሳብ ሊቀይር አይችልም።” ሲሉም አሰልጣኙ አክለው ገልፀዋል።

ሂዩዝ በራሂኖ የቀድሞ ክለቡን በሃውትሮን ቅዳሜ ሲገጥም በቡድናቸው ስብስብ ውስጥ እንደሚያካትቱትም ገልፀዋል።

የ23 ዓመቱ አጥቂ ረቡዕ ምሽት ከኤቨርተን ጋር 1ለ1 ሲለያዩ በሁለተኛው አጋማሽ ተቀይሮ በመግባት ለስቶክ የመጀመሪያ ጨዋታውን አድርጓል።

“በሚያደርግልን ነገር ደስተኞች ነን። እናም የነገርውን ጨዋታ ያደርጋል።” ሲሉ የስቶኩ አሰልጣኝ ገልፀው። ጨምረውም “ለምን አናጫውተውም? በቡድኑ ውስጥ ለመካተት ዝግጁ ነው። ረቡዕ ተቀይሮ በመግባት ጥሩ አስተዋፅኦ ተወጥቷል። እናም ነገ (ቅዳሜ) በቡድኑ ውስጥ የማይካተትበት ምክኒያት አይኖርም።” ብለዋል።

የዌስት ብሮሙ አሰልጣኝ ቶኒ ፑሊስ ግን በአርብ ዕለቱ ጋዜጣዊ መግለጫቸው ስለበራሂኖ ቅጣት ለማብራራርት ፈቃደኛ አይደሉም። ይልቁንስ የእንግሊዝ ከ21 ዓመት በታች ተጫዋቹ ለአቋሙ መውረዱ አብይ ምክኒያቱ የጨዋታ ጊዜ አለማግኘቱ መሆኑን ገልፀዋል።

“ሳይዶ እዚህ በነበረበት ወቅት የጨዋታ ቅጣት ተጥሎበት ነበር። ለምን እንደሆነ ግን አስተያየት አልሰጥም። ለእኔ አልተጫወተልኝም። ምክኒያቱም አቋሙ ጥሩ አልነበረም።” ሲሉ ፑሊስ ተናግረዋል።

“ሳይዶ ከዚህ በኋላ የአልቢዮን ተጫዋች አይደለም። አሁን ቀድሞ አሰለጥንበት የነበረው ክለብ ይገኛል። ይህን ደግሞ አከብራለሁ። እሱ በስቶክ እጅ ላይ ነው።” ሲሉ የቅጣቱን መንስኤ ከማብራራት ተቆጥበዋል። 

Advertisements
%d bloggers like this: