Skip to content
Advertisements

አጫጭር ወሬዎች : የአርብ አመሻሽ የአውሮፓ ጋዜጦች የዝውውርና ሌሎች አዝናኝና አጓጊ ወሬዎች

በሚኪያስ በ. ወርዶፋ | አርብ ጥር 26, 2009

ሙኒክ ለቶትነሀሙ የ 20 አመት አማካኝ ዴል አሊ የዝውውር ፍላጎት ያቀረበ አዲሱ የአውሮፓ ክለብ ሆኖ ብቅ ብሏል። (ታይምስ)

ራፋ ቤኒቴዝ በክለባቸው ደካማ የጥር የዝውውር መስኮት ምክንያት በመሰላቸታቸው በኒውካስትል ለመቆየት ማረጋገጫ እንዲሆናቸው የክለቡን የወደፊት እቅድ ማወቅ ፈልገዋል። (ኒውካስትል ክሮኒክል)

ዌስትሀም ረቡዕ እለት በሲቲ 3-0 ከተረታ በኃላ ስላቪያን ቢሊች በመጪዎቹ ጊዜያት የክለቡን አቋም ማሻሻል ካልቻሉ ሮቤርቶ ማንቺኒ እንዲተኳቸው በተጠባባቂነት ተይዘዋል። (ዴይሊ ሚረር)

ዩናይትድ የቤኔፊካውን ቀኝ ተከላካይ ኔልሰን ሴሜዶን ለማስፈረም ከስምምነት ላይ ደርሷል። (ዴይሊ ኤክስፕረስ)

ማድሪድ የሲቲውን አጥቂ ሰርጂዮ አግዌሮን ለማስፈረም አስቧል። የ 28 አመቱ አጥቂ ባሳለፍነው ረቡዕ ጨዋታ ተጠባባቂ የተደረገ ሲሆን ካሪክ ቤንዜማንና አልቫሮ ሞራታን በመጪው ክረምት ሊያጣ እንደሆነ የተሰማው የስፔኑ ክለብ አርጀንቲናዊውን ተጫዋች የሁለቱ አጥቂዎች ምትክ ሊያደርገው አስቧል። (ዴይሊ ሚረር)

ዌስትሀም በመጪው ክረምት ውሰት ቶሪኖ የሚገኘውን የሲቲውን የ 29 አመት በረኛ ጆይ ሀርትን ለማስፈረም ትልቅ እቅድ ይዟል። (ዘ ሰን)

አርሰን ቬንገር በቀድሞው የአርሰናል ዝነኛ ተጫዋች ቲየሪ ሄነሪ ተይዞ የነበረውን ሪከርድ የሰበረውንና የፈረንሳይ ባለትንሽ እድሜ ጎል አስቆጣሪ የሆነውን የሞናኮውን አጥቂ ካይሊያን ምባፔን ለማስፈረም ጥረት አድርገው እንደነበር ይፋ አደረጉ። (ለንደን ኢቭኒንግ ስታንዳርድ)

የፓርቹጋሉ ቤኔፊካ ቪክተር ሊንድሎፍን ሲሸጥ ለቀድሞ ክለቡ የሚከፍለውን ገንዘብ በሚመለከት የነበረውን አንቀፅ ከተጫዋቹ ውል ማፍረሻ ላይ በማስወገዱ ዩናይትድ ተጫዋቹን ለማስፈረም ያለው ፍላጎት ይበልጥ ጨምሯል። (ማንችስተር ኢቭኒንግ ኒውስ)

ዩናይትዱ ጆሴ ሞውሪንሆ ሊንድሎፍንና የአትሌቲኮውን አጥቂ አንቶኒ ግሪዝማን እንዲያስፈርሙ በመጪው ክረምት 130 ሚሊዮን ፓውንድ ይመድብላቸዋል። (ዴይሊ ሜይል)

የ38 አመቱ የቀድሞው የእንግሊዝ አማካኝ ፍራንክ ላምፓርድ ከሄቢ ቻይና የቀረበለትን የ 450,000 ፓውንድ ሳምንታዊ ደሞዝ ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ጫማውን መስቀል መርጧል። (ዴይሊ ስታር)

የእንግሊዝ እግር ኳስ ማህበር ለላምፓርድ የአሰልጣኝነት ስራ እድልን እያመቻቸለት ቢሆንም ቼልሲ የቀድሞው አማካኙ በክለቡ የአሰልጣኝነት ስብስብ ውስጥ እንዲካተት ፈልጓል። (ዴይሊ ሜይል)

የመድፈኞቹ አለቃ አርሰን ቬንገር በነገው የቼልሲ ግጥሚያ በስታዲየሙ ውስጥ ከፀጥታ አስከባሪዎች ጋር እንደሚቀመጡ ታውቋል። የነገው ጨዋታ የአራት ጨዋታ እገዳ ከሚያርፍባቸው ጨዋታዎች ሶስተኛው ነው። (ለንደን ኢቭኒንግ ስታንዳርድ)

የ35 አመቱ የዩናይትዱ አማካኝ ማይክል ካሪክ በኦልትራፎርዱ ክለብ አዲስ ኮንትራት መፈራረም ከፈለገ ሳምንታዊ ደሞዙ ወደ 70,000 እንዲወርድ በክለቡ ተጠይቋል። (ዘ ሰን)

የሪያል ማድሪዱ አጥቂ ጄሴ ሮድሪጌዝ ወደ ሚድልስብራ ከመጓዝ ይልቅ ለምን ላስ ፓልማስን እንደመረጠ ተናግሯል። ለስፔኑ ክለብ ፕሬዝዳንት እንደሚመጣ ቃል በመግባቱ ላስ ፓልማስን ማስቀደሙን ይፋ አድርጓል። (ጋዜቲ ላይቭ)

የቀድሞው የዩናይትድ አማካኝ ሪዮ ፈርዲናንድ እንደተናገረው ክሎፕ ፈረንሳዊውን ማማዱ ሳኮን ወደ ክሪስታል ፓላስ በመሸኘታቸው የምርጡን ተከላካያቸውን ግልጋሎት እንዳጡት ገለፀ። (ለንደን ኢቭኒንግ ስታንዳርድ)

ነገርግን ክሎፕ ፈረንሳዊውን ተጫዋች ከመሸጥ ይልቅ በውሰት በመስጠት የወደፊቱ የአንፊልድ ፕሮጀክት አካል እንደሆነ ተስፋ ሰጥተውታል። (ሊቨርፑል ኤኮ)

የአርሰናሉ ዝነኛ ተጫዋች ሮበርት ፔሬዝ እንደተናገረው በነገው እለት አርሰናል ለሊጉ መሪ እጁን የሚሰጥ ከሆነ የዋንጫ ሩጫው እንደሚገታ ገለፀ። (ፎርፎርቱ)

ሰርጂዮ አግዌሮ ኢትሀድን ለቆ ወደ ሌሎች ክለቦች ከማምራት ይልቅ በእንግሊዙ ክለብ ቆይቶ ከአዲሱ ፈራሚ ጋብሬል ጂሰስ ጋር ለመፋለምና ቦታውን ለማስከበር ቆርጧል። (ዘ ሰን)

በመጨረሻም …

የፊፋ ምክር ቤት በሩሲያው አለም ዋንጫ ቴክኖሎጂ የመጠቀም ውሳኔን ካሳለፈ በቀጣዩ አመት አለም ዋንጫ ላይ ጨዋታውን በቴሌቪዥን እየተከታተሉ ዳኞችን የሚያግዙ የቴሌቪዥን ዳኞችን ልንመለከት እንችላለን። (ታይምስ)

የቀድሞው የቼልሲ እና እንግሊዝ አማካኝ ፍራንክ ላምፓርድ ከእግር ኳስ ከተገለለ በኃላ ወደ ሆሊውድ በመቀላቀል በፊልም ስራ ውስጥ ለመሳተፍ አስቧል። (ዴይሊ ሚረር)

አንድ ዛሬ ይፋ የሆነ የኮምፒውተር ግምታዊ ውጤት እንደተነበየው ከሆነ ቼልሲ ቶትነሀምን በሁለት ነጥብ በመብለጥ የሊጉ አሸናፊ እንደሚሆንና ሁል ሲቲ የሊጉን ግርጌ ይዞ እንደሚያጠናቀቅ ተገለፀ። (ሁል ዴይሊ ሜል)

Advertisements
%d bloggers like this: