ሊቨርፑል እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ

ቢል ጌትስ አንድን ትልቅ የፕሪሚየር ሊግ ክለብ እንዲገዛ ጥያቄ ቀርቦለት ነበር


የዓለማችን የናጠጠ ባለሀብት የሆነው ቢል ጌትስ ሊቨርፑልን ለመግዛት ቀርቦለት የነበረውን ዕድል ሳይቀበል ቀርቷል።
መሰረቱን በሊቨርፑል ከተማ ያደረገው የሊቨርፑል ኢኮ ጋዜጣ እንደዘገበው ከሆነ ቀዮቹ አሜሪካውያኑን ባለሃብቶቹን ቶም ሂክስና ጆርጅ ጂሊየትን ከአንፊልድ ለማስወገድ ሙከራ ባደረገበት ወቅት የማይክሮሶፍት አጋር መስራች የሆነው ቢል ጌትስ ክለቡን እንዲገዛ ጥያቄ ቀርቦለት ነበር።

በሚል የፋይናንስ ተቋም፣ በጂሌት እና በስኮትላዱ ሮያል ባንክ መካከል ተፈጥሮ በነበረው የፍርድ ቤት ክርክር ህጋዊ ሰነድ እንዳመለከተው ከሆነ የተጣራ ሃብቱ 68.3 ቢሊዮን ፓውንድ የሆነው ቢል ጌት ክለቡን እንዲገዛ ጥያቄ ቢቀርብለትም ባለሃብቱ ግን ለጥያቄው ምላሽ ሳይሰጥ ቀርቷል።

በዚህ ሳምንት ሂክስና ጂሌት ሊቨርፑልን የያዙበት 10ኛ ዓመት ተከብሯል።

ሁለቱ አሜሪካውያን ባለሃብት ክለቡን በ2010 ለመሸጥ ተስማምተው ባርክሌይስ ባንክን ሁነኛ ገዢ እንዲያፈላልግ ቀጥረውት ነበር።

ቢል ጌትስ ሊቨርፑልን እንዲገዛ ጥያቄ የቀረበለትም ባርክሌይስ ባንክ አለም አቀፍ ገዢ ያፈላልግ በነበረበት ወቅት ነበር።

Advertisements