Skip to content
Advertisements

የጀርባ ገፅ / የዕለተ አርብ አጫጭር የዝውውር እና ሌሎች አዝናኝ ወሬዎች

daily mirror

 • የሚድልስቦሮው አሰልጣኝ ጋሪ ሞንክ የዌስትሃሙን ተጫዋች አሽሊ ፍሌቸርን 6.7 ሚ.ፓ በሆነ የዝውውር ዋጋ በአራት ዓመት ኮንትራት አስፈረሙ።
 • ማንችስተር ዩናይትድ የሪያል ማድሪዱ አሰልጣኝ ዚነዲን ዚዳን ዌልሳዊው ተጫዋች በዚህ ክረምት በበርናባው ለመቆየቱ ማስተማመኛ ሊሰጠው እንደማይችል መግለፁን ተከትሎ በዝውውሩ ላይ ለረጅም ጊዜያት ይፈልገው የነበረውን ጋርዝ ቤልን ለማስፈረም በአዲስ መንፈስ ተነስቷል።
 • አርሰን ቬንገር ለሶስተኛ ጊዜ 45 ሚ.ፓ የዝውውር ዋጋ ማቅረባቸውን ተከትሎ አርሰናል የሞናኮውን ኮከብ ቶማስ ለማዛቀር ተቃርቧል።
 • ሊቨርፑል ናቢ ኪካታን ከጀርመን ለመውሰድ የመጨረሻውን ዕድል ለመሞከር ተዘጋጅቷል።
 • ባርሴሎና ተፅእኖ ፈጣሪውን አማካኝ ኢቫን ራኪቲችን የዝውውር አካል በማድረግ ፊሊፔ ኮቲኒሆን ለዝውውር ሊጠይቅ ይችላል።
 • ኤሲ ሚላን የዲያጎ ኮስታን ወኪል በዚህ ክረምት ቢያናግርም የክለቡ ኃላፊ ማርኮ ፋሶሜ ግን የቼልሲውን አጥቂ ስለማዛወር ከመናገር ተቆጥበዋል።
 • ቼልሲ አሁንም ድረስ በአርሰናሉ አማካኝ አሌክስ ኦክስሌድ-ቻምበርሌን እና በጁቬንቱሱ የመስመር ተከላካይ አሌክስ ሳንድሮ ላይ ፍላጎት እንዳደረበት ነው።
 • ማንችስተር ዩናይትድ አርብ ምሽት በሚጀመረው የውድድር ዘመን ጅማሮ ላይ የአንደርሌክቱን ሊአንደር ደንዶከርንን እንዲመለከቱ መልማዮቹን ወደቤልጂየም ልኳል።
 • ሮማ ከሌስተር ለመልቀቅ በቋፍ ላይ ለሚገኘው የክንፍ ተጫዋች ሪያድ ማህሬዝ ከዚህ በፊት ያቀረበው 20 ሚ.ፓ የዝውውር ጥያቄ በኋላ አዲስ የ32 ሚ.ፓ የዝውውር ጥያቄ ይዞ ሊመለስ ነው።
 • ብራይተኖች በዚህ ክረምት የዝውውር ክብረወሰናቸውን ዳግም በሚሰብር ዋጋ 8 ሚ.ፓ ዋጋ ላለው የሌስተር የፊት ተጫዋች ቶም ላውረንስን ለማዛወር እንቅስቃሴ ጀምረዋል።
 • አለን ሁቶን በሼፍልድና በሰንደርላንድ የሚፈለግ ተጫዋች ሆኗል።

the sun

 • የቼልሲው አለቃ አንቶኒዮ ኮንቴ ለእንግሊዛውያኑ ከዋክብት ሮዝ ባርክሌይ እና አሌክስ ኦክስሌድ-ቻምበርሌይን ዝውውር 50 ሚ.ፓ የዝውውር ዋጋ ዋጪ ለማድረግ አቅደዋል።
 • ኢቫን ፐሪሲች ኢንተር ሚላኖች ከሱ ፈቃድ ውጪ በክለቡ ሊያቆዩት እንደማይችሉ ማመናቸውን ተከትሎ ማንችስተር ዩናይትድን ለመቀላቀል ተቃርቧል።
 • ማንችስተር ሲቲ ቤንጃሚን ሜንዲ ለስምንት ወራት የቆየ ጉዳት እንዳለበት መግለፁን ተከትሎ ፕሪሚየር ሊጉን ያለአዲስ ፈራሚ ተጫዋቹ የሚጀምር ይሆናል።
 • የባርሴሎና የዝውውር ዒላማ የሆነው ፓውሎ ዲባላ በጁቬንቱስ ደስተኛ መሆኑ  መግለፁን ተከትሎ የካታላኑ ክለብ ተጫዋቹን ሊያስፈርም እንደሆነ በሚናፈሰው ወሬ ላይ ቀዝቃዛ ውሃ ቸልሶበታል።
 • ቶተንሃም በኋይት ሃርት ሌን ሰሜናዊው የስታዲየሙ ክፍል በስታዲየም የማስፋፊያው ግንባታው ላይ የደህንነት መጠበቂያ ያለው መቆሚያ ቦታ በመስራት የመጀመሪያው የፕሪሚየር ሊግ ክለብ ሊሆን ነው።
 • የቦርንማውዙ የክንፍ ተጫዋች ጁኒየር ስታኒስላስ በገጠመው የብሽሽትና የዳሌ ጉዳት የውድድር ዘመኑ የመጀመሪያ ጨዋታ ያልፈዋል።
 • የፕሪሚየር ሊጉ የክለብ መልማዮች የሴልታ ቪጎውን የ19 ዓመት ኮከብ ቺክ ዲዩፕን እንቅስቃሴ ለመመልከት ወደስፔን ሊተሙ ነው።

daily mail

 • የኢንተር ሚላኑ አሰልጣኝ ሉቺያኖ ስፓሌቲ በባየር ሙኒክ 2ለ0 በሆነ ውጤት በተሸነፉበት ጨዋታ የኢቫን ፐሪሲችን ድንቅ ብቃት በተለየ ሁኔታ ቢመለከቱትም በተጫዋቹ የወደፊት እጣ ፈንታ ላይ ግን እርግጠኝነት የላቸውም።
 • ሪያል ቤቲስ በ4 ሚ.ፓ ከዝውውር ስምምነት የሚድልስብሮውን ጋስተን ራሚረዝን ለማስፈረም ተስፋ አድርገዋል።
 • የኤሲሚላኑ ኃላፊ ማርኮ ፋሶኔ ለሬናቶ ሳንቼዝ ባየር ሙኒክ የጠየቀው የዝውውር ዋጋ ውድ እንደሆነ ቢያምኑም ክለባቸው ፓርቱጋላዊውን ተጫዋች ለማስፈረም ተዘጋጅቷል መባሉን ግን አስተባብለዋል።
 • ኒውካሰሎች ዌስት ሃሙን ስፔናዊ ግብ ጠባቂ አድሪያንን የማስፈረም ከፍተኛ ፍላጎት አላቸው።

the times

 • ማውሪሲዮ ፖቸቲኖ ሮዝ ባርክሌይን ወደመኃል አማካኝ ተጫዋችነት አንደሚቀይሩት በማመን እንግሊዛዊውን ተጫዋች ለቶተንሃም ማስፈረም ፈልገዋል።

the independent

 • ጁቬንቱስ በዩናይትድ የሚፈለገው ኒማኒያ ማቲች የዝውውር ጉዳይ እርግጥ ባለመሆኑ ትኩረታቸውን ወደፒኤስጂው ብላይስ ማቲዩዲ አዙረዋል።

  daily star

  • ሰንደርላንድ የአስቶንቪናውን ኮከብ ቶሚ ኤልፊክን ለማዛወር የሚደረገውን ፉክክር እየመሩ ቢገኙም፣ ሊድስ ዩናይትድም ተጫዋቹን እያደነ ይገኛል።

  daily express

  • ሊቨርፑል ፊሊፔ ኮቲኒሆን በዚህ ክረምት ከባርሴሎና እይታ እንደሚያርቁት ተስፋ አድርገዋል።
  • በመጨረሻም
  • ዝላታን ኢብራሂሞቪች በግል የኢንስታግራም ገፁ እንዲህ አስገራሚ ንፅፅር ፈጥሯል

  • ባርሴሎናዎች ማንችስተር ዩናይትድን በአሜሪካ በረቱበት ጨዋታ ከቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ጋር መገናኘታቸውን በክለቡ ይፋዊ የትዊተር ገፅ ገልፀዋል።

  Advertisements

  ወንድወሰን ጥበቡ View All

  የኢትዮአዲስ ስፖርት አዘጋጅና ፀኃፊ

  Leave a Reply

  Fill in your details below or click an icon to log in:

  WordPress.com Logo

  You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

  Google+ photo

  You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

  Twitter picture

  You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

  Facebook photo

  You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

  w

  Connecting to %s

  %d bloggers like this: