Skip to content
Advertisements

ራሺያ 2018 /  ከ ሰርዶቪች ሙሉቲን “ሚቾ” በኋላ ዩጋንዳዎች ጠንካራ ፈተናቸውን እንዴት ይወጡት ይሆን?

 ለ2018 የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ዛሬ በካምፓላ ናምቦሌ ስታድየም “ክሬንሶቹ” በአርጀንቲናዊው አሰልጣኝ ሄክቶር ኩፐር ከሚመሩት ግብጾች ጋር የሞት ሽረት ፍልሚያ ያደርጋሉ።

ዩጋንዳዎች ሰርዶቪች ሙሉቲን ሚቾ ከሀላፊነታቸው መልቀቃቸው እስካሁን ድረስ ሊቀበሉት ያልቻሉት እውነታ ሆኖባቸው ታላቁን ጨዋታ ለማስተናገድ ተዘጋጅተዋል።

ከግንቦት 2013 ጀምሮ የ”ክሬንሶቹ” አለቃ የነበሩት ሚቾ የ ስድስት ወራት ደሞዝ ሳይከፈለቸው በመቅረቱ ከዩጋንዳ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጋር በተፈጠረው ውዝግብ ብሔራዊ ቡድኑን እየወደዱትም ቢሆን ተለይተውታል።

ሚቾ ዩጋንዳን ከ 39 አመት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ በመመለስ ዩጋንዳዊያንን የደስታቸው ጥግ ላይ በማድረስ ስማቸው ላይፋቅ በወርቅ መዝገብ ላይ ቢተክሉም ትዝታቸው ግን በደጋፊዎች ዘንድ አሁንም እየታወሰ ይገኛል።

ቡድኑን ጠንካራ አድርገው ገንብተው ከትንሽ የምስራቅ አፍሪካ ቡድን ወደ ታላላቆቹ ጎራ ለማሸጋገር የፈጀባቸው የአራት አመት ቆይታ ብቻ ማድረግ ነበር።

አገራችን ኢትዮጵያ ላይ ተዘጋጅቶ የነበረው የ2015 የምስራቅና መካከለኛው የዋንጫ ውድድር ላይ አሸናፊ ሆነው ዋንጫ ሲያነሱ ይዘዋቸው የመጡት ወጣት ተጫዋቾች ዛሬ የብሔራዊ ቡድኑ ምሰሶ ሆነዋል።

ይህ ብቻም አይደለም ለዛሬ ለቁጥር የሚታክቱ የዩጋንዳ ተጫዋቾች በአፍሪካ፣በአውሮፓና በተለያዩ የአለማችን ክፍል እንዲጫወቱ በማብቃት ሚቾ የአምበሳውን ድርሻ ይወስዳሉ።

2015 ላይ የዩጋንዳ የሴካፋ ቡድን ተጫዋቾች የነበሩት ጆሴፍ ኦቻያ እና ፋሩክ ሚያ አይነት ተጫዋቾች አሁን አገራቸውን ለቀው በተለያዩ አገራት ላሉ ክለቦች ለመጫወታቸው ምክንያት ሚቾ ናቸው።

የአሰልጣኙ ሌላው ስኬት ለ 2019 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ጠንካራውን ኬፕ ቨርዴን በማሸነፍ ጥሩ ጅማሮ አድርገዋል።

ስኬታቸው በዚህ አላበቃም ለ2018 የአለም ዋንጫ ማጣሪያ በምድብ አምስት ዩጋንዳ ከጠንካራዎቹ ጋና፣ግብጽ እና ኮንጎ ጋር ተደልድላ ዝቅተኛ ግምት(Under dog) ተሰጥቷት የነበረ ቢሆንም በማጣሪያው የተመዘገበው ውጤት ግን ሚቾ ዩጋንዳን ጠንካራ ተፎካካሪ አድርገውታል።

ሁለት ጨዋታዎች በተደረጉበት ምድብ ከሜዳቸው ውጪ ከጋና ጋር አቻ ሲወጡ በሜዳቸው ደግሞ ኮንጎን በማሸነፍ ከምድባቸው ግብጽን ተከትለው በሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

“ክሬንሶቹን” በዚህ ሁሉ ጣፋጭ የውጤት ጎዳና ደረታቸውን ነፍተው እንዲሄዱ ያደረጉት ሰርዶቪች ሙሉቲን “ሚቾ” ዛሬ ከቡድኑ ጋር ባይኖሩም ብሔራዊ ቡድኑ ለአለም ዋንጫው ማጣሪያ የምድቡን ሶስተኛ ጨዋታ ለማድረግ ተዘጋጅቷል።

ሞሰስ ባሴና ሚቾ ከሀላፊነታቸው ከለቀቁ ቦሀላ ብሔራዊ ቡድኑን በጊዚያዊነት ተረክበው እያሰለጠኑ የሚገኙ ሲሆን ጠንካራውን ጨዋታ ለማሸነፍ አቅም እንዳላቸው ተናግረዋል።

የክሬንሶቹ ግምታዊ አሰላለፍ

ዩጋንዳዎች እጅግ ወሳኝ የሆነው በሜዳቸው ናምቦሌ ወይንም የማንዴላ ብሔራዊ ስታድየም የሚያደርጉት ጨዋታ በሄክቶር ኩፐር የሚመሩትን ግብጾችን ያስተናግዳሉ።

እግርኳሳቸው በሀገራቸው በተፈጠረው ቀውስ ከቀዘቀዘበት ለማንሳት እየዳከሩ የሚገኙት ግብጾች ለአለም ዋንጫ ከ 26 አመት በኋላ ለመመለስ ወርቃማ እድል አግኝተዋል።

የምድባቸውን ሁለት ጨዋታ አድርገው ሁለቱንም በመርታት ስድስት ነጥብ ይዘው ዩጋንዳ፣ጋናን እና ኮንጎን ቁልቁል እየተመለከቱ ሲሆን የምድባቸውን ሶስተኛ እና አራተኛ ጨዋታቸውን ዩጋንዳን በደርሶ መልስ ማሸነፍ ከቻሉ ርቋቸው የነበረው የአለም ዋንጫ ተሳትፎ በቅርበት እንዲያስቡ ያደርጋቸዋል ።

ለዚህ ደግሞ ዛሬ ከሰአት በማንዴላ ብሔራዊ ስታድየም በአዲስ አሰልጣኝ ሞሰስ ባሴና የሚሰለጥኑት “ክሬንሶቹን”ማንበርከክ ይጠበቅባቸዋል።

ይህን ጣፋጭ ስኬት ለማጣጣም ግን ሄክቶር ኩፐር በብሔራዊ ቡድኑ እያሳዩት የሚገኙት ጥብቅ የመከላከል መንገድ ትተው ቡድኑ በማጥቃት መጫወት እንደሚገባው አስተያየት የሰጡ አልጠፉም።

ሄክቶር ኩፐር

ኩፐር ስለ ጨዋታው “የዩጋንዳዎችን ጥንካሬ እና ድክመት በደምብ እናውቃለን አነሱም እኛን ያውቁናል ስለዚህ ጨዋታውን ለማሸነፍ ልምዳችን እና የራስ መተማመናችን እንጠቀማለን።

“ውጪ ያሉት ተጫዋቾቻችን ዘግይተው ስለተቀላቀሉት ትንሽ ሀሳብ ሆኖብኛል ነገርግን ያላቸው ልምድ እና ችሎታ ጨዋታውን እንድናሸንፍ እንደሚጠቅመን አስባለው።

አሊ ጋብር እና ሙስጠፋ ፋቲን በጉዳት ያጡት አርጀንቲናዊው ሄክቶር ኩፐር ደስተኛ አለመሆናቸውን ቢገልጹም “ይህን እውነታ መቀበል አለብን እነሱን ለመተካት ጥሩ ጥሩ ተጫዋቾች አሉን።” በማለት ሀሳባቸውን ሰጥተዋል። 

ዩጋንዳ እና ግብጽ ለመጨረሻ ጊዜ የተገናኙት በ2017 የጋቦኑ የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ጨዋታ ላይ ሲሆን በወቅቱ ጠንካራ ፈተና ገጥሟቸው የነበሩት ግብጾች በአብደላ ኤል ሰይድ ጎል 1-0 ማሸነፍ ችለው እንደነበር ይታወሳል።

ሁለቱ ቡድኖች ዛሬ 10:00 ላይ ከሚያደርጉት ጨዋታ በመቀጠል ማክሰኞ በአሌክሳንድሪያ ቦርግ አረብ ስታድየም የምድባቸውን አራተኛ ጨዋታ በድጋሚ እርስበርስ የሚያደርጉ ሲሆን ግብጾቹ ለዚህ ጨዋታ 60,000 ተመልካች በስታድየም ተገኝቶ ጨዋታውን እንዲከታተል ፈቃድ ሰጥተዋል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: