Skip to content
Advertisements

የዝውውር መስኮቱ የመጨርሻ ቀን ቀጥታ የዝውውር መረጃዎች


ላለፉት ሁለት ወራት ተጫዋቾችን ለማዛወር የደራ የገበያ እንቅስቃሴ ሲደረግበት የቆየው የአውሮፓ የዝውውር መስኮት ዛሬ ከእኩለ ለሊት በኋላ በይፋ ይዘጋል። የእርስዎ ትኩስ እና አስተማማኝ የስፖርት መረጃዎች ምርጫ የሆነችው ኢትዮአዲስ ስፖርትም ከዚህ ቀደም እንደምታደርገው ሁሉ በመጨረሻው ቀን የሚደረጉትን አስገራሚ እና ያልተጠበቁ ዝውውሮችን እየተከታተለች በማንኛውም ሰዓት በቀጥታ ወደእናንተ ታደርሳለች።

እርስዎም የኢንተርኔት ብሮውዘርዎ ላይ ይህን ገፅ በማስቀመጥ እና በየጊዜው ሪፍሬሽ በማድረግ መረጃዎቹን በማንኛውም ሰዓት መመልከት ይችላሉ።


የዝውውር መስኮቱ በይፋ ተዘግቷል አብራችሁን ስለነበራችሁ እናመሰግናለን።

ተጠብቀው ያልተሳኩ ዝውውሮች

ሳንቼዝ ወደ ሲቲ ✘

ኩቲንሆ ወደ ባርሴሎና ✘

ማህሬዝ ወደ ቼልሲ ✘

ሌማር ወደ አርሰናል ✘

7:00′ የኢንተሩ ጋብርኤል ባርብሮሳ በውሰት ቤኒፊካን ተቀላቀለ

7:00′ ዊልፍሬድ ቦኒ ስዋንሲን በድጋሚ ተቀላቀለ።

7:00′ ሰንደርላንዶች ማክማነማንን ከዌስትብሮም አስፈረሙ።

7:00′ ጆኒ ዊልያም በአንድ አመት የውሰት ውል ሰንደርላንድን ተቀላቀለ።

7:00′ ሰንደርላንድ የቦርንማውዙን ተከላካይ ማርክ ዊልሰንን በቋሚነት አስፈረመ።

7:00′ ዳኒ ድሪንክ ወተር ሌሲስተርን ለቆ ቼልሲን ተቀላቀለ።ቼልሲ ለዝውውሩ እስከ 35 ሚሊየን ፓውንድ አውጥቷል።

7:00′ ቼልሲ የቶሪኖውን የመስመር ተከላካይ ዛፓኮታን ማስፈረሙን አሳወቀ።

7:00′ ብራይተን የኒውካስትሉን ቲም ክሩልን በውሰት ውል አስፈረመ።

6:55′ ራፋ ቤኒቴዝና ሪያል ባብል በድጋሚ በኒውካስትል መገናኘታቸው እርግጥ ሆኗል።

6:40′ ሌሲስተር ሲቲ  ከሊቨርኩሰን አሌክሳንደር ድራጎቪችን በውሰት አስፈረመ።

6:25′የጁቬንትሱ ወጣት ተጫዋች የሆነው ሞይሴ ኪን በውሰት ሄላስ ቬሮናን ተቀላቀለ።

6:15′  ዩጋንዳዊው ቲኒ ማውጄ ለአልባኒያው ኬ ኤፍ ቲራና ፈረመ።

6:00′ ዳኒ ድሪንክወተር ወደ ቼልሲ ለመቀላቀል የህክምና ምርመራ ለማድረግ ኮብሀም ደረሰ።

5:45′ የአርሰናሉ ካምቤል ሪያል ቤቲስን በውሰት ውል ተቀላቀለ።

5:25′ ዋሀቢ ካዛሪ በአንድ አመት የውሰት ውል ከሰንደርላንድ ወደ ሬኔስ ተዘዋወረ።

5:00′ አያክስ አምስተርዳም የአያክስ ኬፕታውን የማሰልጠኛ ኮከቦቹን ዲን ሶሎሞን እና ሊዮ ቲታኒን አስፈረመ።

4:45′ ፈርናንዶ ሊዮረንቴ ወደ ስፐርስን ተቀላቀለ።

4:35′ ኒስ የሌሲስተሩን አማካይ ናምፓልስ ሜንዲን ለአንድ አመት የውሰት ውል አስፈረመ።

4:20′ ሲቲ ሳንቼዝን፣አርሰናል ደግሞ ሌማርን ለማስፈረም ያደረጉት ጥረት አልተሳካም።

4:15 ኤቨርተን ኒኮላ ቭላሲችን ከ ሀጁክ ስፕሊት ለ አምስት አመት አስፈረመ።ለዝውውሩም አስር ሚ ፓውንድ ወጪ አድርጓል።

4:00′ ዋትፎርዶች ሌላ አዲስ ፈራሚ አግኝተዋል።ሞላ ዋጉ ክለቡን በውሰት መቀላቀል ችሏል።

3:35′ የተረጋገጠ/ የስፔኑ ክለብ አላቬስ ስፔናዊውን የቀድሞ የባርሴሎና ተጫዋች ቦዣን ኪርኪችን በአንድ ዓመት የውሰት ስምምነት ከስቶክ ሲቲ አስፈርሟል።


3:15′ የተረጋገጠ/ ስፔናዊው የአርሰናል አጥቂ ሉካዝ ፔሬዝ የስፔኑን የቀድሞ ክለቡን ዲፖርቲቮ ላካሮኛን ለአንድ የውድድር ዘመን በውሰት መቀላቀሉን ሁለቱም ክለቦች በይፋዊ የትዊተር ገፃቸው ገልፀዋል።

2:50′ የተረጋገጠ/ የፈረንሳዩ ክለብ ፓሪስ ሴንት ዠርሜን በክረምቱ የዝውውር መስኮት ከፍተኛ የዝውውር ወሬ የነበረውን የሞናኮውን የፊት ተጫዋች ኪሊያን ምባፔን ባልተገለፀ የዝውውር ክፍያ ማስፈረሙን በይፋዊ ትዊተር ገፁ ገልፅዋል።

1:50′ የተረጋገጠ/ የጣሊያኑ ክለብ ቶሪኖ የኤሲሚላኑን ምባዬ ኒያንግን በ20 ሚ.ዩሮ መግዛት በሚያስችል ተጨማሪ ስምምነት ለአንድ የውድድር ዘመን በውሰት ማስፈረሙን ገልፅዋል።

12:35′ የተረጋገጠ/ ዶርትሙንድ የማንችስተር ሲቲውን ወጣት ተጫዋች ጃዶን ሳንቾን አስፈረመ።

11:50′ የተረጋገጠ/ ናኒ ለአንድ የውድድር ዘመን ላዚዮን በውሰት መቀለቀሉን የጣሊያኑ ክለብ በይፋ ገልፅዋል።

11:25′ የተረጋገጠ/ የፈረንሳዩ ክለብ ዲዮን የሰንደርላንዱን ተከላካይ ፓፒ ጂሎቦጂን ለአንድ የውድድር ዘመን በውሰት ማስፈረሙን ገልፅዋል።

11:05′ የተረጋገጠ/ የሊቨርፑሉ አጥቂ ዲቮክ ኦሪጊ 6 ሚ.ፓ ይሆናል ተብሎ በታመነ የዝውውር ክፍያ የጀመርኑን ክለብ ዎልፍስበርግን ለአንድ የውድድር ዘመን በውሰት መቀላቀሉን ክለቡ ይፋ አድርጓል።

10:50′ የተረጋገጠ/ ሚድልስቦሮ የክንፍ ተጫዋቹን ማርቪን ጆንሰንን ከሌላው የእንግሊዝ ክለብ ኦክስፎርድ ዩናይትድ በሶስት ዓመት የኮንትራት ስምምነት ማስፈረሙን አረጋግጧል።

10:50′ የተረጋገጠ/ በርንሌይ ባልተገለፀ የዝውውር ዋጋ ናክሂ ዌልስን በሶስት ዓመት የቆይታ ስምምነት አስፈረመ።

10:35′ የተረጋገጠ/ የስቶክ ሲቲው አማካኝ ተጫዋች ጂያነሊ ኢምቡላ የፈረንሳዩን ክለብ ቱሉስን ለእንድ የውድድር ዘመን በውሰት ተቀላቀለ።

10:25′ የተረጋገጠ/ የባየር ሙኒኩ አማካኝ ሬናቶ ሳንቼዝ በ8 ሚ.ፓ ክፍያ እና በሚቀጥለው የውድድር ዘመን የመግዛት አማራጭን በያዘ ስምምነት ስዋንሲን ለአንድ የውድድር ዘመን በውሰት መቀላቀሉን የዌልሱ ክለብ በይፋዊ የትዊተር ገፁ ገልፅዋል።

10:0′ የተረጋገጠ / የ19 ዓመቱ ደቡብ ኮሪያዊ የባርሴሎና ተጫዋች የሆነው ሱንግ-ዉ ሊ የጣሊያኑን ክለብ ሄላስ ቬሮናን በአራት ዓመት የኮንትራት ስምምነት ባለተገለፀ ዋጋ መቀላቀሉ ተረጋግጧል።

9:45′ የተረጋገጠ / ዋትፎርድ የ32 ዓመቱን ግሪካዊ ግብ ጠባቂ ኦረስቲስ ካርነዚስን ለአንድ የውድድር ዘመን በውሰት ከጣሊያኑ ክለብ ዩዴኔዚ ማስፈረሙን ይፋ አደረገ።

9፡20 ስዋንስ ቀድሞ አጥቂውን ዊልፍሬድ ቦኒን ለማስፈረም ከማንቸስተር ሲቲ ጋር ከስምምነት ላይ ደረሰ፡፡

9:15′ ሪያድ ማህሬዝ ባርሴሎና አውሮፕላን ማረፊያ መድረሱን ከስፔን የወጡ ዘገባዎች አመልክተዋል።

8:40 ቨርጂል ቫንዳይክ የሳውዝሀምፕተንን ካምፕ በጥቁር መኪና ሲለቅ ታይቷል፡፡

8:30 ቶተንሀም የፒኤስጂውን የቀኝ መስመር ተከላካይ ሰርጂ ኦውሪርን በክለቡ ለአምስት ዓመት በሚያቆየው የኮንትራት ስምምነት ማስፈረሙን በይፋ ገልፅዋል።

2.jpg

8፡07  ሊቨርፑል አሌክስ ኦክስሌድ ቻምበርሌይንን ማስፈረሙን በይፋ ገለፀ

1.jpg

7፡20 – ባየር ሊቨርኩሰን ሬስቶስን አፈረመ

የጀርመኑ ክለብ ባየር ሊቨርኩሰን በ22 ሚ.ዩሮ ፔናጎቲ ሬስቶስን በአምስት ዓመት የዝውውር ኮንትራት ማስፈረሙን ገልፅዋል።

7፡20′ – አርቢ ሌፕዚግ የባየር ሊቨርኩሰኑን ተጫዋች አስፈረመ

የጀርመኑ ክለብ አርቢ ሌፕዚግ ኬቨን ካምፕልን 20 ሚሊዮን ዩሮ ይሆናል ተብሎ በተገመተ የዝውውር ዋጋ ከሌላው የጀርመን ክለብ ባየር ለቨርኩሰን በአራት ዓመት ኮንትራት አስፈርሟል።


7፡20′ – የማንችስተር ሲቲው ተጫዋች በጋላታሳራይ የተደረገለትን የህክምና ምርመራ አጠናቀቀ

የ22 ዓመቱ ቤልጂየማዊ ተጫዋች ጄሰን ደናየር ከማንችስተር ሲቲ ወደቱርኩ ክለብ ጋላታሳራይ ለመዛወር የተደረገለትን የህክምና ምርመራ አጠናቋል።

6፡30′ – የዩናይትዱ ታዳጊ ዊሎክ የሆላንዱን ክለብ በውሰት ተቀላቀለ
የማንችስተር ዩናይትድ ታዳጊ ማቲ ዊሎክ የሆላንዱን ክለብ ዩትረችርን በአንድ ዓመት የውሰት ቆይታ ስምምነት ተቀላቅሏል።

6፡15′ – የስቶኩ አምበል ሾውክሩዝ አዲስ ስምምነት ፈረመ

የ29 ዓመቱ የስቶክ ሲቲ አምበል ሪያን ሾውክሩዝ በክለቡ ለተጨማሪ አራት ዓመታት የሚያቆየውን አዲስ የኮንትረት ስምምነት ፈርሟል።

6፡05′ – ኦክስሌድ-ቻምበርሌን በሊቨርፑል የህክምና ምርመራ እያደረገ ነው
የአርሰናሉ አማካኝ አሌክስ ኦክስሌድ-ቻምበርሌን ወደሊቨፑል የሚያደርገውን ዝውውር ለማጠናቀቅ በአንፊልድ የህክምና ምርመራ እያደረገ እንደሚገኝ ምንጫቸው ያልታወቁ በፎቶግራፍ የተደገፉ መረጃዎች ወጥተዋል። ሙሉ ዝርዝሩን ቆይተን የምናቀርብ ይሆናል።

5፡25′ – የተረጋገጠ

የጀርመኑ ክለብ ሃኖቨር ከሌላው የጀርመን ክለብ ፎርቱና ደስልዶርፍ የ23 ዓመቱን ቶጓዊ ተጫዋች ኢህላስ ቤቡን በአራት ዓመት የኮንትራት ስምምነት አስፍርሟል።

 

4.jpg

5፡00′የተረጋገጠ

የዌስትብሮሙ ኬን ዊልሰን በውሰት ውል እስከ ጥር ድረስ ኤክስተር ሲቲን ተቀላቀለ፡፡

4፡50′ ሲቲዎች ለሳንቼዝ መጀመሪያ ላይ ካቀረቡት 50 ሚሊየን ፓውንድ ውጪ ተጨማሪ ጥያቄ ባያቀርቡም ተጫዋቹን ለማስፈረም ካላቸው ጽኑ ፍላጎት የተነሳ የዝውውር ሂሳቡን አሻሽለው እንደሚመለሱ ይጠበቃል፡፡

4፡40′ ካሪንግተን የተገኘው የስካይ ስፖርት ጋዜጠኛ ዩናይትዶች በዛሬው እለት ምንም አይነት ዝውውር የሚያደርጉ እንደማይመስሉ አሳውቋል፡፡ዩናይትዶች የመስመር ተጫዋች ለማስፈረም ፈልገው የነበሩ ቢሆንም በሲዝኑ መጀመሪያ ያሳዩት ምርጥ ብቃት እምነታቸውን በማርሻል እና ራሽፎርድ ላይ ማድረጋቸው ነው፡፡

4፡39′ ባርሴሎናዎች ሊቨርፑሎች ቻምበርሊንን ማስፈረማቸው ተረድተዋል በሌማር እና ቫንዳይክ ዝውውር ላይም ፍላጎት እንዳላቸው በማጤናቸው ለኩቲንሆ የሚቀርበውን የተሻሻለ የዝውውር ሂሳብ ሊቀበሉ እንደሚችሉ ሀሳቡ አላቸው፡፡ሂሌም ባላጉ

4፡35′ የስፔኑ አላቬስ ቦያን ክሪክችን ለስቶክ ሲቲ በውሰት ለመውሰድ ተቃርቧል፡፡

2፡40′ ሪያድ ማህሬዝ በዝውውር ምክንያት ከአልጄሪያ ካምፕ ፈቃድ ተሰጠው(ስካይ ስፖርት)

3

 

2.jpg

2፡30′ ኤቨርተን ከቼልሲ በመጨረሻ እለት የዝውውር መስኮት ሚኪ ሚትሽዋይን ለማዘዋወር እቅድ ይዟል፡፡(ዴይሊ ኤክስፕረስ)

 

2፡28′ የቀድሞ ማንቸስተር ዩናይትድ ተጫዋች የነበረው ናኒ ወደ ላዚዮ ለመዘዋወር ሮም ደረሰ፡፡(ካልቺዮ መርካቶ)

1.jpg

Advertisements

ወንድወሰን ጥበቡ View All

የኢትዮአዲስ ስፖርት አዘጋጅና ፀኃፊ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: