መገፋት / ዲያጎ ኮስታ 25 አባላት ካሉት የቼልሲ የቻምፒዮንስ ሊግ ስብስብ ውጪ ተደረገ

በተጠናቀቀው የዝውውር መስኮት ረጅም ጊዜውን ከክለቡ ጋር በገባው እሰጣ ገባ ሲታመስ የቆየው ዲያጎ ኮስታ ከቼልሲ የቻምፒዮንስ ሊግ ስብስብ ውጪ ተደርጓል። 

ኮስታ በፕሪምየር ሊጉ የ 2017/18 የሰማያዊዎቹ ስብስብ ውስጥ ስሙ ቢካተትም ከሰአታት በፊት ይፋ በተደረገው የምዕራብ ለንደኑ ክለብ የቻምፒዮንስ ሊግ 25 ተጫዋቾች ስብስብ ውስጥ ስሙ ሳይካተት ቀርቷል።

የ 28 አመቱ አጥቂ ወደ አትሌቲኮ ማድሪድ ለማምራት ጥረት ሲያደርግ ከመቆየቱ ጋር በተያያዘ ገና ወደ ስታምፎርድ ብሪጅ ያልደረሰ ሲሆን የስፔኑ ክለብ እስከ መጪው ጥር የተጣለበት የዝውውር እቀባም ስፔናዊውን አጥቂ በቼልሲ እንዲቆይ አስገድዶታል።

የቀድሞው የአትሌቲኮ ተጫዋች ቼልሲ “የወንጀለኛ” አይነት መንገድ አያያዝ እንደተፈፀበት ገልፆ ወደ ቼልሲ እንደማይመለስ ገልፆ የነበረ ቢሆንም ጣሊያናዊው የቡድኑ አለቃ እቶኒዮ ኮንቴ ስለሁኔታው ሲጠየቁ የኮስታን ንግግር በሹፈት ሳቅ እንዳለፉት ይታወሳል።

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ በዝውውሩ መጠናቀቂያ ሊያስፈርማቸው ያሰባቸው ፈርናንዶ ሎረንቴ፣ አሌክስ ኦክስሌንድ ቻምበርሊን እና ሮዝ ባርክሌይን በእጁ ማስገባት አለመቻሉ የስብስቡን ጥልቀት ሊያሰፋለት ባለመቻሉ ኮስታን ለሀገር ውስጥ ውድድር ይፈልገዋል።

በሌላ በኩል በምድብ ሸ ሪያል ማድሪድ፣ ቦሩሲያ ዶርትሙንድ እና አፖል በሚገኙበት ምድብ የሚገኘው ቶትነሀም ሆላንዳዊውን አጥቂ ቪንሰንት ጃንሰን እና አርጀንቲናዊውን አጥቂ ኤሪክ ላሜላ በሚያስገርም ሁኔታ ከቻምፒዮንስ ሊግ ስብስቡ ውጪ አድርጓቸዋል።

እንግሊዛዊው የሊቨርፑል ተከላካይ ናትናኤል ክላይን በበኩሉ ከቀዮቹ የቻምፒዮንስ ሊግ ስብስብ ውጪ የተደረገ ሌላኛው ተጫዋች ሆኗል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s